TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ? የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል። በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።…
🔈#የተማሪዎችድምጽ

ባለፈው ወር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከፈተናው ጋር ተያይዞ ያላቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ፦

- የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ፈተናውን ወስደው፣ ውጤት ለምን በተለያየ ጊዜ ተገለፀ ?

- የመንግሥት ተፈታኞች በብዛት ሲያልፉ በርካታ የግል ተቋማት ተፈታኞች ለምን ወደቁ?

- እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ነጥብ ያላቸው መቶ ጥያቄዎች ተፈትን 37.92 አይነት ውጤት እንዴት ተመዘገበ ? የAI ስህተት ካለ ይነገረን።

- በጣም ተዘጋጅተን የተፈተንን ሰዎች በዚህ ትኩረት ሳይሰጠው በተፈተነው ፈተና ምክንያት ሞራላችን እንዲነካ እና ተስፋም እንድንቆርጥ ተደርገናል።

- ፈተናው ላይ ትልቅ ውጤትን ያመጣሉ የተባሉ ብዙ ጎበዝ ልጆች እንደተጠበቀው አልሆነም።

- ውጤታችን እንደገና ሊታይልንና የተፈተነው ጥያቄ ከነመልሱ ይፋ ሊደረግልን ይገባል።

... የሚሉ ቅሬታዎች በተፈታኞቹ ተነስቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ የሆኑትን እዮብ አየነው (ዶ/ር) ጠይቋል።

ከውጤት ነጥብ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ኃላፊው ተከታዩን ብለዋል ፦

1ኛ. የጤና ትምህርት ዘርፍ ሁለት ፈተና (ጠዋት ከ100 ከሰዓት ከ100 በድምሩ ከ200) ስለሚፈተኑና ለማለፊያ የሁለቱ ፈተናዎች ውጤት ተደምሮ አማካኝ ውጤት ስለሚያዝ ውጤታቸው በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

2ኛ. አንዳንድ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ለምሳሌ ፦ ሒሳብ እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት በተለያዩ ምክንያቶች ተማሪዎች የተፈተኑት ጥያቄ ቁጥር ከመቶ ያነሰ ስለነበር ያገኙት ውጤት ወደ መቶ ሲቀየር በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

" ውጤት ሲገለፅ የጊዜ መቀዳደም ካልሆነ በስተቀር በሲሰተሙ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበረ " ኃላፊው ገልጸዋል።

የማለፍ ምጣኔን በተመለከተም ፥ " ተፈታኞቹ የተማሩባቸውን ተቋማት እንዲሁም የራሳቸውን ብቃት መመልከት " አለባቸው ብለዋል።

ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች 100% ያሳለፉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ኃላፊው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።


ይህንን ምላሽ የተመለከቱ ተማሪዎች ፥ " ለቅሬታችን የተሰጠው ምላሽ ተገቢ አይደለም ፤ አሁንም ቢሆን ውጤታችን እና የሰራነው በድጋሚ ይታይ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የፋርማሲ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ፥ " ከዚህ በፊት እንደነበረው የጠዋት እና የከሰአት አማካይ (Average) የሚያዝ እንደሆነ በምላሹ ላይ ሰምተናል " ብለዋል።

" ግን ፈተናውን ከጨረስን ከአንድ ቀን በኋላ ፈተናው ችግር አለበት / ተሰርቋል ተብለን በአንድ ቀን ልዩነት እንደገና ፈተና ተቀምጠናል፤ ስንቀመጥም የጠዋቱን ብቻ ነበር አንዴ የተፈተንነው እንጂ የከሰአቱን ሌላ ጊዜ ነው የተባልነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ በጠዋቱ ፈተና ብቻ ነው pass and fail የሆነው። ስለዚህ ትምህርት ሚኒስቴር ቃሉን አክብሮ የከሰአቱን ፈተና ከተፈተንን በኋላ ነው አማካይ መያዝ ያለበት " ብለዋል።

ተማሪዎቹ አለን ያሉትን ቅሬታ ይዘን የሚመለከተውን አካል የምናነጋግር ይሆናል።

Via @tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
🔈#የተማሪዎችድምጽ

° “ ሳንመረቅ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው መቼ እንደሚጠራን ያሳውቀን ” - ተመራቂ ተማሪዎች

° “ መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ


ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ጭምር የመመረቂያ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመመረቅና ድግሪ ለመያዝ አመታትን እንደጠበቁ ፣ አሁንም ዩኒቨርሲቲው እንዳልጠራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ምን አሉ ?

- ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ስለጉዳዩ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቀን ነበር። የመውጫ ፈተና እንደምንፈተን እና ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ላይ እንደምንመረቅ ነበር ስኬጁል የወጣው።

- የመውጫ ፈተናውን ብንወስድም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ወጥተናል። ከዚያ ነሐሴ 2016 ዓ/ም ትጠራላችሁ ተባልን፡፡ አሁን የክረምት ተማሪዎችም ተጠርተዋል፡፡ እስካሁን የኛ ግን ምንም ነገር የለም። ዝም ጭጭ ብለዋል።

- የፌደራል መንግስትም በጦርነነቱ ጊዜ የነበሩ ተማሪዎች በዓመት 3 ሴሚስተር ማካካሻ ጊዜ ፈቅዶልን ነበር፡፡ ያኔ የተፈቀደልንን ማካካሻ በአግባቡ ያስተናግዱን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፤ “ ተማሪዎቹ እያነሱት ያለው ቅሬታ ትክክል ነው ” ብሏል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ተከስተ ብርሃን (ዶ/ር) ምን አሉ ?

በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉን።

ክረምቱን እንዲማሩ ነበር በዩኒቨርሲቲው ማኔጀመንት የወሰነው። ነገር ግን በአገር ደረጃ በተሰጠው ዳይሬክሽን መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲፈተኑ መደበኛ ተማሪዎቹ ማስወጣት የግድ ነበር።

በኮረና እና በነበረውም ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ የክረምት ተማሪዎች ነበሩ። እነርሱንም ተቀበልን፡፡ ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና አለ፡፡ እነርሱንም ተቀብለን እያሰለጠንን ነው።

በእነዚህ ምክንያቶች መደበኛ ተማሪዎቻችንን መጥራት አልቻልንም።

አሁን እንደ አቅጣጫ የያዝነው መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ጠርተን ማካካሽ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ባለፉት ዓመታት ሊመረቁ ለነበሩ ተማሪዎች ብቻ ካላንደር አዘጋጅተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ነው።

መስከረም ስንት ቀን ይጠራሉ ? ቁርጥ ያለውስ ቀን መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ተከሰተ (ዶ/ር)፣ " የክረምት ተማሪዎቹ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ብለናል፡፡ ስለዚህ ካላንደሩ ገና አልጸደቀም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#TIkvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች

° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት ቢያቀርቡም መፍትሄ በማግኘት ፋንታ " እናባርራችኋለን " የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው አስረድተው፣ "  ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉት 2010 ዓ.ም እንደሆነ ፤ በተለያዩ ችግሮች ሁለት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ እንደባከነባቸውና እንዳልተካካሰላቸው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ሳለ እነርሱ ህክምና መከልካላቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚደንት ዶክተር መንገሻ አየነን አናግሯል።

ዶክተር እሳቸው ጋር ምንም አይነት የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ ገልጸው፣ ለማን ቅሬታ እንዳቀረቡ ኢንተርን ሀኪሞቹ በድጋሚ እንዲጠየቁ አሳስበዋል፡፡

እሽ በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አሳውቃችሁ ነበር ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ "ለዶክተር መንገሻ አልደረሰም። ለተማሪዎች አገልግሎት አቅርበናል። ለዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ አቅርበናል" ብለዋል።

ለምን ለዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አካላት እንዳላቀረቡ ሲያስረዱም፣ " የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ 'ይሄ ጉዳይ ከእኔ አልፎ ወደ ላይ ቢሄድ አውቶማቲካሊ ሴኔት ሰብስቤ ፈርሜ  አባርራችኋለሁ' አለን " ብለዋል።

" ቅሬታችንን ለዶክተር መንገሻም አላሳወቁትም ከታች ነው ያስቀሩት " ሲሉም አክለዋል፡፡

ቅሬታው ደርሷቸዋል የተባሉት አካላት ለጊዜ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቅሬታ ያቀረቡበትን ክፍል በመግለጽ በድጋሚ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ መንገሻ (ዶ/ር)፣ የኢንተርን ሀኪሞቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ያላወቀው ቅሬታ እንደሆነ አስረድተው፣ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

" ፕሮፌሰር የሺጌታ የሚባል ሲኢድ አለን ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ሙሉውን የሚመራ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ነው እዚያ ግቢ " ያሉት መንገሻ (ዶ/ር)፣ ' ፕሮፌሰሩን ይጠይቁ፡፡ እሱ ካልፈታላቸው ወደ እኔ ይመጣሉ ወይም ደብዳቤ ካላቸው ያምጡ " ብለዋል፡፡

" ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " ሲሉ አክለዋል፡፡

(ጉዳዩ ከምን እንደደረሰ ተከታትለን መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የተማሪዎችድምጽ ° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች ° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን…
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

“ በህግ የሚገባቸው መሆኑን አረጋግጠን እናስተናግዳለን ” - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ኢንተርን ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሆነ እያለ፣ ምግብና ነጻ ህክምና መከልከላቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወቃል።

ቅሬታቸው ሰሚ እንዳታጣ ይባስ ብሎ ዛቻ እንደደረሰባቸው ገልጸው፣ “ ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል ” ነበር ያሉት።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ቅሬታ እንዳልደረሳቸው ገልጸው፣ “ ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል ” ማለታቸውን አሳውቀናችሁ ነበር።

ዛሬስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?

ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደገለጹት ለሚመለከታቸው ሁሉ ደብዳቤውን ቢያቀርቡም ምላሽ ባለማግኘታቸው ሳይመገቡ መስራት ፈተና እንደሆነባቸው ነው።

ቅሬታቸውን በደብዳቤ አስደግፈው ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት እንዳስገቡ፣ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈርሞ ቢልክም ኮሌጁ ለቅሬታቸው ምላሽ እንዳልሰጣቸው አስረድተዋል።

ቲክቫህም፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሥራ አስፈጻሚ የሺጌታ ገላው (ፕ/ር)ን የጠየቀ ሲሆን፣ ስልክ ለማንሳትም ሆነ ለተላከላቸው የፅሑፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ካቀረቡና ፍትሃዊ ከሆነ እንደሚታይላቸው የገለጹ እንደመሆኑ መጠን ጉዳዩን ከምን እንደደረሰ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት መንገሻ (ዶ/ር)ም ጥያቄ አቅርበንላቸዋል።

በምላሻቸው፣ “ኢንተርን ላይ ያሉ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ደሞዝተኞች ናቸው። ጥያቄው መንግስት ከሚከፈለን ደሞዝ በተጨማሪ በተለዬ የቀረበ ፍላጎት ነው። በህግ የሚገባቸው መሆኑን አረጋግጠን እናስተናግዳለን” ብለዋል።

“ ለተማሪዎቻችንም አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ” ያሉት ፕሬዜዳንቱ፣ “ወጭ መጋራት ላይ ለተነሳው ነጥብ ኮሌጅ አብሮ እንዲመለከተው ኃላፊነት ተሰጥቶታል” ብለዋል።

“ከህግ ውጭ ተማሪዎቹ ያልተጠቀሙት ነገር ወጭ መጋራት ውስጥ ተካቶ ከሆነም ኮሌጁ ያርማል” ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህ መዘለለ ላሉት ጥያቄዎች ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስራ አስፈፃሚ ፕ/ር የሺጌታ ምላሽ እንዲሰጡ ያመላከቱ ሲሆን ፕሮሰሩ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም።

(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የተማሪዎችድምጽ

🔴 " ስኮላርሺፕ እና የውጭ ስራ እድሎች ኦርጅናል ዲግሪ ባለመስጠታቸው ምክንያት እያመለጠን ነው " - ተመራቂ ተማሪዎች

🔵 " ዲግሪያቸውን መስጠት ያልተቻለው ዩኒቨርሲቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው " - የዩኒቨርሲቲው አመራር


የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተበት 1999 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት አመታት ላስመረቃቸውን ተማሪዎች ኦርጂናል ዲግሪ ባለመስጠቱ በርካታ ተመራቂ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ እና የውጭ የስራ እድሎች እያመለጧቸው መሆኑን ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ ሲመረቁ የወሰዱት ጊዜያዊ (Temporary) ዲግሪ ሲሆን አስፈላጊውን የኮስት ሼሪንግ ክፍያ እና የአገልግሎት ጊዜያቸውን በመፈጸም ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲው ቢጠይቁም በየጊዜው " ይሰጣችኋል " ከማለት ውጪ ምንም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።

" ኦርጅናል ዶክመንት አሳትሙልን ስንል ' ይታተማል ' ይባላል ግን መቼ የሚለው አይመለስም " ሲሉ ነው የገለጹት።

አክለውም " በቅርብ የተመሰረቱ ዩኒቨርሲቲዎች እየሰጡ ነው ለሚዛን ቴፒ ከባድ ያደረገው ምንድነው?በቂ የሚሉት ምክንያት የላቸውም ምክንያታቸው ለእኛም ግራ አጋብቶናል " ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች የቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት እና ፊርማ በማሰባሰብ ዩንቨርስቲውን በተደራጀ መልኩ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ እያሰቡ መሆኑን ነግረውናል።

የዩንቨርስቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?

ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ለተመራቂዎች አሳትሞ መስጠት ያልተቻለው በዩኒቨርሲቲው ከባድ የሚባል የበጀት እጥረት በመኖሩ መሆኑን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት እስከ 2002 የተመረቁ ተመራቂዎችን ዲግሪ ለመስጠት ማቀዱን እና በ2018 በጀት አመት ደግሞ የቀሪ ተማሪዎችን ለመስጠት በእቅድ መያዙን ገልጸዋል።

ወደማተሚያ ቤት የተላከው እስከ 2002 ከተመረቁት መካከል የግማሹ ተመራቂዎች ብቻ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" ከሁለት ወይም ሦስት ወር በኋላ እስከ 2002 ያሉ የመደበኛ፣የማታ እና የክረምት (Summer) ተመራቂዎች ይወስዳሉ ብዬ አስባለሁ እስካሁን ያልተሰጣቸው ዩኒቨርስቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው አሁን ለማተሚያ ቤት ከ175 ሺ ብር በላይ ቅድመ ክፍያ ከፍለን እንዲታተምላቸው ተልኳል " ብለዋል።

ቀሪ ተማሪዎች በምን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " አለን በምንለው በጀት አጣበን የሚቀሩትን እንሰጣለን ብዬ አስባለሁ የሚከብደን አይመስልኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሃላፊው ዩኒቨርስቲው ኦርጂናል ዲግሪ ያልሰጣቸው አጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ቁጥር ምን ያህል መሆኑን ከመናገር ተቆጥበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

" በዩኒቨርሲቲው አመራር ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ተብለናል "- ተማሪዎች

በቁጥር 1,300 አካባቢ ይሆናሉ የተባሉ የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ 5 ኪ/ሜ ያህል ርቆ ወደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ትዘዋወራላችሁ መባላቸው ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩበት ግቢ " በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ የሚደረግበት አካባቢ ነው " ያሉ ሲሆን " በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች እየለቀቁ ባለበት ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ብሎናል " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረማርቆስ ከተማ በ5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2015 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ ለ7ወር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በክልሉ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከየካቲት 7/2016 ዓም ጀምሮ ተማሪዎቹን ወደ ዋናው ግቢ በማዘዋወር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አደርጎ ነበር።

እስከ አሁን በዋናው ግቢ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የጤና ተማሪዎች " ከሚመጣው ቅዳሜ 10/05/17 ዓም ጀምሮ ወደ ቀድሞ ግቢ እንደምንዘዋወር ተነግሮናል " ብለዋል።

ተማሪዎቹ ትዘዋወራላቹ የሚል ውሳኔ ከሰሙበት ቀን ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

በ 02/05/2017 ዓም የጤና ኮሌጅ ዲን አና ሌሎች የጤና ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት ባደረጉት ስብሰባም " ለሚደርስባቹ የህይወት አደጋ ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም እርስ በእርሳቹ ተጠባበቁ አናንተ ስትሄዱ የቦታዉ ሰላም ይረጋገጣል " መባላቸውን ተናግረዋል።

በትላንትናው ዕለት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ የሚመለከታቸው የክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት በድጋሚ ባደረጉት ስብሰባ ተማሪዎች ውሳኔያቸውን እስከ አርብ እንዲያሳውቁ እና ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚዘዋወሩ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ዝርዝር
ማብራሪያ ጠጥተዋል።


ምን አሉ ?

" እንዲሄዱ የሚደረግው የቦታ ጥበት በመኖሩ ነው ተማሪዎቹ መጀመሪያ ግቢያቸው ይህ አልነበረም ተደርበው ነው ያሉት።

የትምህርት ማቴሪያሎቻቸው በሙሉ እዛ ነው የሚገኙት ዩኒቨርሲቲውም የሚቀበላቸው አዳዲስ ተማሪዎች አሉ ይሄ ሁሉ ተጨማምሮ የመማሪያ ክፍል እጥረት ስላለ እና ጸጥታውም በአንጻራዊነት መሻሻል ስለሚያሳይ ነው እንዲሄዱ የተወሰነው።

ተማሪዎቹ ' እንሂድ ' ብለው ሰኔ ወር ላይ ጠይቀው ነበር እንዲዘገዩ ያደረግነው እኛ ነን በወቅቱ ጸጥታው ይህንን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ አሁን እንሂድ ስንል ነው ቅሬታ የተፈጠረው " ብለዋል።

በአካባቢው በሚታየው የጸጥታ ችግር አካባቢያቸውን የሚለቁ ሰዎች እንዳሉ ተሰምቷል ምን አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታዎች ኖረው ነው ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አመራሩን ጠይቋል።

እሳቸውም ፦

" አካባቢውን እየለቀቀ ያለ ሰው አለ የሚለው ውሸት ነው የሚለቅ ሰው ሊኖር ይችላል ክረምት እና ከክረምት በፊት በፍርሃት የሚወጡ ነዋሪዎች ነበሩ አሁን ግን ነዋሪውን በአካል አወያይተናል ነዋሪውም መምጣታቸውን ይፈልጋል።

ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ነው ልል አልችልም ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንፃር አሁን ያለንበትም ተቋም ቤቱም ሆነ ከተማው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም ግን የተለየ ስጋት የለም የሚል ድምዳሜ ነው ያለው " ብለዋል።


በዋናው ግቢ ቆይተው ቢማሩ ለደህንነታቸው የበለጠ አስተማማኝ አይሆንም ወይ ? ስንል ጥያቄ አንሰተናል።

" እዚህም ቢሆኑ እዛም ቢሄዱ ችግር የሚመጣ ከሆነ ሊደርስባቸው ይችላል ' ያኛው ግቢ የበለጠ ለአደጋ ተጋላጭ ያደርገናል ' ብለው ቢያስቡ እንኳ በአሁኑ ሰዓት በዋናው ግቢ ትምህርቱን ለማስቀጠል የማያስችሉ ሁኔታዎች አሉ ትምህርቱ እየተጎዳ ስለሆነ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM