TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹ከከሰልና #እንጨት ጋር አብረን እንድንጓዝ ተገደናል፡፡›› ነዋሪዎች
.
.
በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከከሚሴ በደዌ ሃረዋ በሚወስደዉ መንገድ ነዋሪዎች በትራንስፖርት ችግር #እንግልት እየደረሰባቸዉ ነዉ፡፡ የሚመደቡ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶች በቂ ባለመሆናቸዉ በአንድ አዉቶብስ ከ100 እስከ 120 ሰዎች እንደሚጓጓዙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የአካባቢዉ ህብረተሰብ እንደ አማራጭ #የጭነት መኪኖችን ለመጓጓዣነት እየተጠቀመባቸዉ ነዉ፡፡ የአካባቢዉ የትራንስፖርት ችግር ነዋሪዎችን በአይሱዙ መኪኖች ከከሰልና እንጨት ጋር አብረዉ እንዲጓዙ አስገድዷቸዋል፡፡ ለትራፊክ አደጋ #እያጋለጣቸዉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ለአብነት በቅርቡ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተሰምቷል፡፡ የደዌ ሃረዋ ትራፊከ ፖሊስ ምክትል ሳጅን መሃመድ ጀማል ህብረተሰቡ የሚያስፈልገዉን የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑ ይታወቃል በተደጋጋሚ ትርፍ የሚጭኑትን አሽከርካሪዎች እየቀጣን ነዉ፣ ሆኖም መፍትሄ አልመጣም ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሃሰን በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚታየዉን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia