TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ዐብይ ድሬዳዋ ለምን ቀሩ??

ከሳምንታት በፊት ጠ/ሚር #አብይ_አህመድ በድሬዳዋ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመመረቅ አስበው በመጨረሻ ሰአት ጉዟቸውን #የሰረዙበት ምክንያት ከፀጥታ ችግር ጋር የተያያዘ መሆኑን የከተማዋ ሁለት ሀላፊዎች በተለይ ለEthio NewsFlash ገልፀዋል። አንዱ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሀላፊ እንዳመለከተው ወደ ፕሮጀክቶቹ ከሚወስዱት መንገዶች አንዱ የመልካ መንገድ ዙርያ #የጦር_መሳርያ በብዛት በወቅቱ #እንደተገኘ ሲገልፅ ሁለተኛው ሀላፊ ደግሞ ሌሎች የመንገድ አማራጮችን ጠ/ሚሩ ተጠቅመው መሄድ ቢችሉም የፀጥታው ሁኔታ #አስተማማኝ ስላልነበር ሙሉ ለሙሉ ጉዞው ተሰርዟል ብለዋል። ነገር ግን ሁለቱም ሀላፊዎች ጠ/ሚሩ በወቅቱ ኢላማ ውስጥ እንደነበሩ ተጠይቀው በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።

via ETHIO NEWSFLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia