TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ገንደ ውሃ‼️

የገንደ ውሀ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ #አራጋው_ሰንታ ዛሬ ጠዋት ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በስልክ የተናገሩት፦

•እንደተባለው የህብረተሰቡ አቋም የሱር ኮንስትራክሽን መኪኖች ይፈተሹልን ነበር ምክንያቱም በህብረተሰቡ ዘንድ ድርጅቱ ትልልቅ የጦር መሳርያዎችን ከሱዳን ወደሌላ ክልልሎች ያስተላልፋል የሚል ጥርጣሬ ነበር። እነሱ ግን ይባስ ብለው በመከላከያ ታጅበው መጡ።

•በመሀል መከላከያዎች ህዝቡ ላይ መተኮስ ጀመሩ። አንድ ህፃን እና ሎሎች ሁለት ሰዎች እኛ ከተማ ላይ ሞተዋል። ኮኪት ከተማ ላይም የሞቱ ሰዎች አሉ። እነዚህ በሙሉ ንፁሀን ዜጎች እና ምንም መሳርያ ያልታጠቁ ነበሩ። ኮኪት ከተማ ላይ ግን የሞቱ የመከላከያ አባት እንዳሉ ሰምቻለሁ።

•ትናንት በተካሄደ ሰልፍ ህዝቡ ሱር ይፈተሽልን፣ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ እና ሰላም ይስፈን ብለው ጠይቀዋል።

በተጨማሪ...

የኮኪት ከተማ ነዋሪው ይመር ስለ ማክሰኞው ግድያ ለጋዜጠኛ ኤልያስ በስልክ የተናገረው፦

•የሱር መኪናዎች ገንደ ውሀ ላይ ህዝቡን አዘናግተው እንዳለፉ ሲወራ ህዝቡ ኮኪት ከተማ ላይ ሆኖ ጠበቃቸው። ይህ የሱር አካሄድ ጥርጣሬን ጫረ።

•ኮኪት ከተማ አቅራቢያ አንድ ድልድይ አለ። መከላከያዎች ድልድዩን አልፈው ብቅ እንዳሉ እና ህዝቡን እንዳዩት መተኮስ ጀመሩ። በዚህም ከአንድ ቤት ሶስት ሴቶች ተገድለዋል። በአጠቃላይ እኛ ከተማ ብቻ አምስት ሰው ሞቶ ስምንት ሰው ቆስሏል።

•ከከተማው አንድ ወይም ሁለት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለ እና አንደኛ ጎራ በተባለ ተራራ ላይም ከባድ መሳርያ ተተኩሶ ሲነድ ነበር።

•ህዝቡ በመጀመርያ ድንጋይ ሲወረውር ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን አስፓልት ላይ የቆመ ሰው ሲመታ አንድ ሁለት ጥይቶች ወደ መከላከያ ተተኩሰዋል። የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ ግን አልሰማንም።

•በመጨረሻ መኪኖቹን ኑ ፈትሹ ተብሎ ሲፈተሹ የተባለው መሳርያ አልተገኘም። አዳር ላይ ምን ሲሰሩ እንዳደሩ ግን አይታወቅም። አሁን መከላከያዎች #ወጥተዋል፣ ድባቡም #የተሻለ ነው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia