TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MinT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሠላምይሁን አደፍርስ ተከታዩን ብለዋል ፦

" ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው።

አሁን ላይ ደግሞ ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ መሆን እንዲችሉ ማበረታቻዎችን የያዘ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው።

አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ውጤታማ የሚያደርግ ነው።

ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን አዋጁ ለመጽደቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል።

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያወዳደረ ይገኛል፤ ተወዳድረው ያሸነፉ ፈጣሪዎች የገንዘብ፣ የቴክኒክና የሥልጠና ድጋፎችን እያገኙ ነው።

የልማት አጋሮች አሸናፊ ለሆኑ ኃሳቦች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።

ሚኒስቴሩ አዳዲስ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ልጆች ከመደገፍ ባሻገር ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆችም የሚወጡበት ሥርዓት እየዘረጋ ነው "

#ENA

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF

(ኢትዮ ቴሌኮም)