TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ '

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር #ዕዳ እንዳለበት ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይልን የ9 ወራት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ነው።

የተቋሙ የብድር ጫና በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ  ባቀረቡት ሪፖርት ፤ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳለበት ተናግረዋል።

የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አስረድተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ካለበት የዕዳ ጫና ለመውጣት ፦
#የታሪፍ_ማሻሻያዎችን በማድረግ
የውጭ የሃይል ሽያጭ አቅሞችን በማጠናከር
የውስጥ ገቢን በመሳደግ ለዕዳ ቅነሳው ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስቧል።

ኢ/ር አሸብር ፥ በቀጣይ ከጅቡቲ፣ ከኬኒያ እና ከሱዳን በተጨማሪ ለታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የዕዳ ጫናውን ለመቀነስ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በዕቅድ መያዙን  ተናግረዋል።

#HouseofPeoplesRepresentatives #CapitalNewspaper

@tikvahethiopia
#ግብር

የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም በሚል መጉላላት እየደረሰባቸዉ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማሕበር የበጀት ዓመቱን የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቅሬታዉን ለፍትህ ሚኒስትር ያቀረበዉ ማህበሩ  ከጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲያጋጥም የቆየውን ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍ የታመነበት ዝርዝር መመሪያ ሳይወጣና በሥራ ላይ እንዲውል ሳይደረግ የ2016 በጀት ዓመት የግብር መክፈያ ወቅት ተጀምሯል ብሏል።

ይህን ተከትሎ ፍትህ ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስትር እና ለአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ደብዳቤዉ ጽፏል።

በዚህም የጠበቆችን ታክስ አከፋፈል በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ ወጥቶ ችግሩ ወጥ በሆነ መልኩ በዘላቂነት እስከሚፈታ ድረስ ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት ሲስተናገዱበት በቆየው ነባር አሰራር የ2016 በጀት ዓመት የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲደረግ ጠይቋል።

በዚህ ምላሽ ሊያገኙ እንደሚችል በተገለፀበት ደብዳቤ  ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል የሚደርስባቸዉን መጉላላት ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት ተጥሎበታል።

#CapitalNewspaper #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦ ➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች ➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች ➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡ @tikvahethiopia
#Ethiopia

ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል።

የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡

ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

ከነዚህም ውስጥ #ድጎማ እና #የደመወዝ_ጭማሪ የሚጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ወጪዎች በአመቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

IMF ሰንድ ትንበያ ምን ያሳያል ?

- የመንግስት ወጪ ቀደም ሲል ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

- ይህንን ወጪ ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ገቢ 1.3 ትሪሊየን ብር (1.15 ትሪሊየን ብር ከታክስ) 214 ቢሊየን ብር ከውጭ የበጀት ድጋፍ በጥቅሉ 1.52 ትሪሊየን ብር የሚገኝ ይሆናል።

- ከውጭ ከሚገኘው 214 ቢሊየን ብር ብድር እና እርዳታ አምና (2016) ከተገኘው 43 ቢሊየን ብር አንፃር በአምስት እጥፍ (500 በመቶ) ጭማሪ ይኖረዋል።

- ከውጭ ከሚገኘው የበጀት ድጋፍ በተጨማሪም ደግሞ በእርዳታ ተቋማት አማካኝነት የሚፈሰው ሃብት ሲካተትበት በጠቅላላ ወደ 304 ቢሊየን ብር ይደርሳል።

- ወጪ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው 1.8 ትሪሊየን ብር ሲሆን የበጀት ጉድለቱ 270 ቢሊየን ብር ይሆናል።

- ከጠቅላላው የመንግስት ወጪ 1.24 ትሪሊየን ብር የመደበኛ ወጪ ይሆናል። ቀሪው 557 ቢሊየን ብር የካፒታል ወጪ ይሆናል፡፡

ሰኔ መጨረሻ ለ2017 በጀት አመት ፀድቆ ከነበረው 971 ቢሊየን ብር በጀት ውስጥ 358.5 ቢሊየን ብር ወይም ከጠቅላላው በጀት 37 በመቶ የሚሆነው የበጀት ጉድለት ነበር፡፡

ሆኖም በIMF ትንበያ ወጪ ይደረጋል ከተባለው 1.8 ትሪሊየን ብር ውስጥ የበጀት ጉድለቱ ከወር በፊት ተቀምጦ ከነበረው መጠን የሚያንስ ነው፡፡

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

#Capitalnewspaper #Ethiopia #IMF

@tikvahethiopia