TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ አሕመድ አሊ የኦሮሞ ብ/ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳዳር ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ አሕመድ አሊን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የቀድሞው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሰን እና አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ አሊ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

ም/ቤቱ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

በተጨማሪም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አቶ ከድር አሊን የዞኑ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ አቶ ጀማል ሐሰንን የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ እና አቶ መሐመድ ሙሳን የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አድርጎ ሹሟል።

#AMC

@tikvahethiopia
#Ethiopia

አጫጭር መረጃዎች #1፦

- የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ ጀምሯል፤ ነገር ግን በተሟላ አቅሙ ወደ ስራ አልገባም። አሁን ላይ የድንገተኛ ህክምና ፣ የተኝቶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ሆስፒታሉ የመብራት መቆራረጥ፣ የመድሃኒት እጥረትና የአምቡላንስ ችግር አለበት። የነበረው አንድ አምቡላንስ ለህልውና ዘመቻ ሄዶ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን የአምቡላንስ አለመኖር በታካሚዎች ላይ ትልቅ ችግር ይፈጥራል ተብሏል። ሆስፒታሉ የጎደሉት እንዲሟሉለት ጥሪ ቀርቧል።

- ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረብርሃን የቆዩ ወገኖች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ሲመለሱ የደ/ብርሃን ህዝብና ሌሎች አካላት ስላደረጉላቸው መስተንግዶ አመስግነዋል። ደ/ብርሃን በጦርነት የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያስጠለለች ከተማ ስትሆን አብዛኛው ተፈናቃዮች አሁን ወደቀያቸው ተመልሰዋል።

- በሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ ዶ/ር ጥላሁን ጎሹ (Mihret Medical Supply) ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከነትራንስፖርታቸው 4.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ቪታሚኖችና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሀኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

- በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ላይ በደረሰው ውድመት ምክንያት የረሀብ አደጋ ማንዣበቡን ገልፀዋል። ከመፈናቀል እየተመለሱ ያሉትን ለመደገፍ በወር 1.2 ሚልየን ኲንታል እህል እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገልፆ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እጆቻቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርባል።

#AMC #AmbFitsumArega #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዛሬ ተገቢው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጾልኛል ሲል…
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናና ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ።

ፎረሙ ጥያቄውን ያቀረበ ዛሬ ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ነው።

የመግቢያ ፈተናውን ውጤት ተከትሎ የሚወጡት መረጃዎች ያልተለመዱና አስደንጋጭ ናቸው ያለው ፎረሙ በተወሰኑ ተማሪዎችና ወላጆች ግፊትና ጫና የተስተካከሉ ውጤቶች ለተፈጠረው ስሕተት ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።

የአማራ ትምህርት ቢሮ የሁሉንም ትምህርት ቤቶች ውጤት ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው የጠቆመው ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው ለማረም እድል ያገኛሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

በተማሪዎችና ወላጆች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ሁሉም ወገን በቅንነት ተቀብሎ የድጋሜ እርማትን እና ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ በዜጎች ዘንድ ፍትሐዊነትና ተዓማኒነት ከማረጋገጡም በላይ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ይጠቅማል ሲል አሳስቧል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናውና ውጤቱ ላይ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አቻችሎና ሰምቶ በመተው የሚፈቱ ሳይሆን የትውልዱን እድል የሚወስኑ በመኾናቸው በፍጹም አካዳሚያዊ ሥነ ምግባርና ከፍተኛ መሆን አለበት ብሏል።

ፎረሙ ሁሉም አካላት ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቋል።

ፈተና በደቦ እየተሠራ መልካም ትውልዶችን መፍጠር አይቻልም ያለው ፎረሙ ጉዳዩ ከብሔር አውድ ፍፁም ነጻ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ጠይቋል።

ተማሪዎችና ወላጆች ጥያቄው መልስ እስኪያገኝ ተረጋግተው እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ 160 እጩ የወረዳ ፍ/ቤት ዳኞችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

#AMC

@tikvahethiopia
#አብን

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮቹ ያቀረቡትን ስራ መልቀቂያ አልቀበልም አለ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።

በስብሰባው በተለይ በፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኩል " አሁን ላሉ በርካታ ጉዳዮች ላለፉት 4 አመታት በከፍተኛ አመራርነት ያገለገልን አመራሮች ለቀን በአዲስ እንተካ " የሚለውን ሃሳብ ፓርቲው ጊዜ ሰጥቶ የተወያየበት መሆኑን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጣሂር ሞሀመድ ተናግረዋል።

ሆኖም ሊቀመንበሩ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ሃሳብ ማዕከላዊ ኮሚቴው አልቀበልም ብሏል።

አሁን እየታየ ላለ ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆን አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት በማምጣት እንተካካ የሚለውን ሃሳብም ፓርቲው ሀምሌ 18/2014 በሚያካሂደው ስብሰባ በጥልቀት እንደሚያየውና እስከዛም ፓርቲው በትኩረት ስራውን እየሰራ እንደሚቀጥል ተገልጧል።

የፓርቲው ውስጣዊ አንድነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተመለከተ የህዝብ ግንኙነት ኀላፊው አቶ ጣሂር ሞሀመድ " ማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችና ለድርጅቱም አቅምና ውስጣዊ አንድነት የሚበጁትን ሃሳቦችና ውሳኔዎች የምናሳልፍበት ስብሰባ ሀምሌ 18 ይካሄዳል " ብለዋል።

#AMC

@TIKVAHETHIOPIA
#BahirDar

በባሕር ዳር የባጃጆች ሰዓት ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ከተማ የባጃጅ ወይም የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ እንዲሆን ገደብ ተጣለ።

የባሕር ዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ምክር ቤቱ በአደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስጠብቁ ያላቸውን ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል።

በዚህም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ትዕዛዝ ተላልፏል።

ምክር ቤቱ አሁን ካለው ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለከተማው ሰላምና ደኅንነት ሲባል ውሳኔው መተላለፉን አሳውቋል።

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውም የባጃጅ ወይም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የተባለ ሲሆን ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰድበት ማንኛውም ቅጣትና እርምጃ ኀላፊነቱን ባለቤቱ ወይም አሽከርካሪው ይወስዳል ሲል ምክር ቤቱ አሳስቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል። በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ…
#AddisAbaba

በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ የተናገሩት ፦

" ... በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች እጣ ይወጣባቸዋል።

ቀደም ብሎ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባር እና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በእጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል። "

#AMC

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ፤ የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ምን አሉ ?

- በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት ተወስኖ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

- ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

- በአማራ ክልል ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ ነው። ይህንን በተመለከተ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተወይይተናል።

- በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች ተከስተዋል። ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል።

- አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው።

- ልዩ ኃይሉ ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም ፤ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

- ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ ሊዘጋጅ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ በሁኔታው #ቅሬታ ውስጥ ገብቷል።ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ ነው።

- አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ ነው።

- አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም።

- የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ የለም።

- በተፈጠረ የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ ናቸው። አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አይደሉም።

- የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ፤ ከአንደኛው ችግር ሳናገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት ነው።

- በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም ይቻላል ፤ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል ይገባዋል።

- ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ ናቸው።

- የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባል።

- የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው።

- ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

- ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት አለበት ፤ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና ይገባል።

- የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሸጋገሩት።

- በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለን።

#AMC

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ በጀግኖች አርበኞች ስም መንገድ ሰየመች።

82ኛው የጀግኖች አርበኞች ቀን በባሕር ዳር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ዛሬ ተከብሯል።

በዚህም በባሕር ዳር ከተማ " ከገጠር መንገድ እሰከ ኤርፖርት " ያለው መንገድ በጀግኖች አርበኞች ስም መሰየሙን በአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር አሳውቋል።

ዛሬ በነበረው ዝግጅት የአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዜዳንት ዳኝነት አያሌው ተከታዩን መልዕክት አስተላልዋል ፦

" ለሀገር በመስዋዕትነት  ከፍለው ሀገር ያጸኑ ጀግኖችን መዘከር ይገባል።

' ጀግናን መፍጠር ጀግናን ከማክበር ይጀምራል' የሀገርን ነጻነት፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ያጸኑ ጀግኖቻችን እንኮራባቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን።

የዚህ ዘመን ትውልዶች ከድል ታሪኩ በመማር በመከባበር፣ በመደጋገፍ ፣በአንድነት ሀገርን ማጽናት ይገባናል።

በአንድ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመተባበር ሀገርን ማሻገር ይገባል። ' ሀገሩን የማያውቅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ የማያውቅ ሕጻን እንደማለት ነው ' እና ሀገራችን በምንና እንዴት እንደቆመች መረዳት ይገባናል።

በሚጠበቅብን ዘርፍ ሁሉ የአርበኝነት ሚናችን መወጣት ይገባል። "

#AMC

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

" 522 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ፤ የተገኘው ሀብት ግን ዝቅተኛ ነው " - የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ

በአማራ ክልል ፤ #በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት 522 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ሲል የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ የመንግሥትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዓመታዊ የአጋርነት የምክክር መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰተው ችግር 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በክልሉ እንደሚገኙ የገለፀው ቢሮው ፤ 11 ነጥብ 4  ሚሊዮን ሕዝብ  ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ  የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

ሰባት ዞኖችና ሶስት ሜትሮፖሊታንት ከተሞች በጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸእ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን ዞኖች መልሶ ለማቋቋም እና  መልሶ ለመገንባት ከ522 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል ብሏል።

ጉዳት የደረሰባቸውን ዞኖች  መልሶ ለመገንባት ጥረት ቢደረግም  የተገኘው ሀብት ዝቅተኛ በመኾኑ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አለመቻሉን ቢሮው አመልክቷል።

ቢሮው ፤ መንግሥት ከሚያደርገው ሥራ ባለፈ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ የልማት ሥራዎች እና በመልሶ ግንታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህ ዓመትም በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 374 ፕሮጀክቶች በክልሉ እየተከናወኑ ነው ተባቧል።

ድርጅቶች በቀጣይም የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል።

በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ ችግሩን በሰላም ለመፍታት ጥረት ተደርጎ ነበር ያሉ ሲሆን " ካለፈው ጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ እየተስተዋለ የመጣውን የክልሉን የሰላምና ጸጥታ ችግር በክልሉ አቅም ለመፍታት የታየው ዳተኝነት እና የአመራሩ የተዛነፈ እይታ ችግሩ ውሎ ሲያድር አቅም እንዲያገኝ እና ከክልሉ መንግሥት አቅም ውጭ እንዲሆን አድርጎታል " ብለዋል።

ግጭቱ ፦
- በክልሉ ውስጥ እየተስተዋለ የመጣው ዋልታረገጥ ልዩነት፣
- #የሕዝብ_ጥያቄዎች_አለመመለሳቸው_የፈጠረው_ብሶት
-  የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የፈጠረው የሥነ-ልቦና አለመረጋጋት የፈጠሩት ችግር እንደሆነ አቶ ደሳለኝ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያመርቱ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት አቀጣጣይ ነበሩም ብለዋል።

ኮማንድፖስቱ ከታወጀ ማግስት ጀምሮ በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ሰላም ታይቷል ያሉ ሲሆን አሁንም ቀሪ ሥራዎች በመኖራቸው የኦፕሬሽን ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ ፤ በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የግጭት አማራጭን በመተው ለሰላማዊ ትግል እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

" የሰላም አማራጮች አሁንም በሮቻቸው ዝግ አይደሉም " ያሉት አቶ ደሳለኝ " የሚፈለገው የሰላም አማራጭ ከተገፋ ግን ሕግን የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ ተደምጠዋል። #AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው " 5 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡ " ብለዋል። ሌሎች 5 ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን እንዳሳለፉ ገልጸዋል። ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦ 1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት (ደብረማርቆስ) 2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት 3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት…
#አማራ

በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙ ካሳለፉ 5 ትምህርት ቤቶች 3ቱ በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው።

ሶስቱ ትምህርት ቤቶች ፦
- ደሴ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት፣
- ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ የአደሪ ትምህርት ቤት
- ባሕር ዳር ስቴም ትምህርት ቤት ናቸው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በማኅበራዊ ሳይንስ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪም የሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።

እንደ አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ በሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት እና በደሴ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በድምሩ 32 ተማሪዎች 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

አማራ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክልሎች ባለፉት አመታት በሰላም እጦት ክፉኛ እየተጎዳ ቢሆንም መሰል ትልልቅ ውጤቶች መመዝገባቸው ለቀጣይ ተስፋ ሠጪ ነው ተብሏል።

የአማራ ክልል ተማሪዎች የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተምረዋል፤ የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተፈትነዋል፡፡ አብዘኛዎቹ የክልሉ ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት በወደሙ እና በተዘረፉ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተገድደዋል፡፡ በፈተና ወቅት በተፈጠረ አለመረጋጋት ፈተናውን አቋርጠው የወጡ ተማሪዎችም ነበሩ።

ይህ ሁሉ ቢሆንም በሀገር አቀፉ ፈተና የተገኘው ውጤት አጥጋቢ ባይሆንም፣ ሰላም ከተረጋገጠ፣ የተረጋጋ እና የተስተካከለ ትምህርት መሥጠት ከተቻለ ግን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ያሳየ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው እንደ ሀገር የተዘመገበው ውጤት ዝቅተኛ መሆኑን ገልጾ በትምርት ስርዓቱ ላይ በርካታ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

ከታች ጀምሮ መሥራት ከተቻለ ውጤት ማምጣት የሚችሉ ልጆች አሉንም ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል ጦርነት እና ግጭት በፈጠሩት ሥነ ልቦናዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተፈተኑ ተማሪዎች መኖራቸው ያስታወሰው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች ጫናውን ተቋቁመው ያስመዘገቡት ውጤት ጥሩ መሆኑን አመልክቷል።

ወደ ፊት መሥራት ከተቻለ ተስፋ የታየበት መሆኑንም ገልጿል።

ቢሮው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ትምህርት ሰጭ ነው ያለ ሲሆን የተሻለ ዜጋ ለማፍራት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት ያስፈጋል ብሏል። በክልሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑንም አሳውቋል። #AMC

@tikvahethiopia
#ስሃላሰየምት🕯

የስሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና  አሥተዳዳሪ ሲሳይ ብሩ ፦

" ትናንት ከቀኑ 6፡00 ገዳማ ከስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት በግምት 26 ሰዎች ውስጥ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

ከ26ቱ አንድ ሕጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው ተርፏል።

አደጋው ከደረሰ በኋላ የሟቾችን አስከሬን ለመፈለግ በተደረገው ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ 2 ሰዎች ብቻ አስከሬን ተገኝቷል።

ሕይወቱ የተረፈው ሕጻን ከፍተኛ ጉዳት ስላስተናገደ ወደ ሰቆጣ ተፈራ ኃይሉ መታሰብያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲላክ የተቀሩት ስድስቱ መሸሀ ጤና ጣብያ ገብተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

ከአራት ዓመታት በላይ ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው እና እስከ ሰኔ ወር መጨረሻዎች ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ከስሃላ - ዝቋላ የሚያገናኘው የተከዜ የብረት ድልድይ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁ የሰው ሕይወት መቅጠፉን እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል። "
#AMC

@tikvahethiopia