TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሚሰጠው የመታወቂያ ካርድ #ይዘትና ንድፍ ለካቢኔ ቀረበ፡፡ በምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በቀረቡለት ሁለት አማራጮች ላይ ከመከረ በኋላ አንዱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 መሠረት የተዘጋጀው አዲሱ መታወቂያ፣ ከቀድሞው የሚለይባቸው ይዘቶች አሉ፡፡

አዲሱ መታወቂያ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪ መታወቂያ›› የሚል ሲሆን፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ መግለጫ አልያዘም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የትውልድ ሥፍራና #የብሔር ስያሜ ያላካተተ ሲሆን፣ ዜግነትን በልዩነት አካቶ ይዟል፡፡

የአዲሱ መታወቂያ የምዝገባ ሒደት በኮምፒዩተር የታገዘ የዲጂታል አሠራር የሚከተል ሲሆን፣ በአሻራ የተደገፈ ነው፡፡

መታወቂያው በአማራጭ #በሁለት ቀለማት በመዘጋጀቱ፣ ካቢኔው የሚመርጠው አንደኛው ንድፍ ተቀባይነት እንደሚያገኝ ተመልክቷል፡፡

የመታወቂያ አሰጣጥ ሒደቱንና ይዘቱን እንደ አዲስ ማዘጋጀት ያስፈለገው፣ የቀድሞው መታወቂያ #ብሔርን የሚያጎላና #አንድነትን የሚያላላ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ እንዳሉት የቀድሞው መታወቂያ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል፡፡ የመታወቂያውን ይዘት በማስተካከል፣ አንድነትን ማጎልበት ያሻል በሚል ዕርምጃው መወሰዱ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም መታወቂያ አሰጣጡ አሻራን የሚጠቀምና ዲጂታል ስለሆነ፣ ሕገወጦችን ለመቆጣጠር አመቺ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ መታወቂያ ከዚህ ቀደም ይፈጸሙ የነበሩ ማጭበርበሮችን ማከናወን እንደማይቻል፣ በምርጫ ጊዜ ተደጋጋሚ ምዝገባ ማድረግ እንደማይቻልና ሌሎች ሕገወጦች ድርጊቶችን መፈጸም አይቻልም ተብሏል፡፡

መታወቂያው ለካቢኔው ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ በኋላ የሕዝብ አስተያየት እንደሚሰጥበት ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ በኋላ በቅርቡ የነዋሪዎች ምዝገባ እንደሚጀመር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአዲሱ መታወቂያ አጠቃላይ ወጪ ኅትመትን ጨምሮ 300 ብር ያህል ቢሆንም፣ ነዋሪዎች ግን የሚከፍሉት የካርዱን ዋጋ ብቻ 80 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia