TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችልም ትንብያዉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና #እንዲጠነቀቅ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በአብዛኛዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጥሩ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ትንበያዉ የሚያመለክት ሲሆን ይህም ለግብርናዉ የስራ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ታምኖበታል፡፡ ቀድመዉ የተዘሩ እና በእድገት ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የሚገኘዉ እርጥበት በጎ ሚና አለዉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ለቋሚ ተክሎች የዉሓ ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላለቸዉና ለአርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች የግጦሽ እና የመጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

በቀጣይ የሚኖረዉ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተፋሰሶች ላይ ለዉጥ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ በአብዛኛዉ የተከዜ፣ የኦሞ ጊቤ የአባይ፤ የላይኛዉና የመካከለኛዉ አዋሽ እና አፋር ደናክል ተፋሳሾች ከፍተኛ እርጥበት ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
ፎቶ: ፋይል

@tsegabwolde @tikvahethiopia