TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

" ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል " - አቶ አብርሃም ማርሻሎ

የሲዳማ ክልል መንግሥት የግምገማ መድረክ እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

ታዲያ በዚሁ እየተካሄደ ባለው የግምገማ መድረክ ላይ ከተገመገሙት አመራሮች አንዱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ናቸው ተብሏል።

ከንቲባው በ " ብልሹ አሰራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " በሚል ከስልጣን ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑ ተነግሯል።

ከንቲባው ከስልጣን መነሳታቸውንም የሲዳማ  ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት  ብልፅግና ፓርቲ አረጋግጧል።

ፓርቲው የከንቲባውን ከሃላፊነት መነሳት ያረጋገጠው በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ አማካኝነት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

አቶ አብርሃም ፤ በሀዋሳ ከተማ በርካታ መሰራት ያለባቸው የልማት ሥራዎች ሳይሰሩ መቅረታቸውን ጠቅሰዋል።

በመካሄድ ላይ በሚገኘው የግምገማ መድረክ ላይ ከንቲባ ፀጋዬ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች  ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባው ባሳዩት የሥራ ድክመት ከኃላፊነታቸው እና ከፓርቲ አባልነት እንዲነሱና በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑን አመልክተዋል።

ከንቲባውን በሚመለከት በተካሄደ ግምገማ ወቅት ፤ " አመራራቸው ደካማ ነው ፤ የአቅም ውስንነት አለባቸው ፤ ከፍተኛ ሙስና ውስጥም ገብተዋል " የሚሉ ሀሳቦች ተነስተው ነበር።

በተለይም ከተማው አስገነባሁት ካለው የመግቢያ በር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በሚዲያ 90 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት ቢነገርም በመሃንዲስ ተጣርቶ ወጪው ከ30 ሚሊዮን እንደማይዘል በግምገማ መድረኩ ላይ መነሳቱ ተሰምቷል።

ከንቲባው ስብሰባ ረግጠው ወጥተዋል በሚለው ጉዳይ ላይ ፤ እንዲሁም በግምገማው ወቅት ስለተነሳባቸው ክስ ምን ይላሉ ? የሚለውን ለማወቅ እና ምላሻቸውን ለማግኘት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ሊሳከልን አልቻለም።

ከንቲባው ብዙ ጊዜ ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚፅፉበት የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይም የሰጡት አስተያየት የለም።

ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

በሌላ በኩል ፤ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን በፌስቡክ ላይ " Hawassa City Press Secretary " እና "  Mayor office of Hawassa ,Sidaama " የተሰኙ ገፆች የሚያሰራጩት መረጃ እና መልዕክት ሙሉ በሙሉ የከተማው አስተዳደርን የሚወክል እንዳልሆነ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም በክልሉ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያነጋገራቸው ሰራተኞች ፣ ወጣቶች ክልሉ በሙስራ እና በብልሹ አሰራር ተዘፈቀ በመሆኑ ከታች እስከ ላይ ያለው #እንያንዳንዱ አመራር በጥልቅ ሊገመገም ይገባል ብለዋል።

መረጃው ከዶቼ ቨለ ሬድዮ፣ ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር እንዲሁም ከሲዳማ ክልል የቲክቫህ አባላት የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia