TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢራን

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በአደባባይ በስቅላት ገደለች።

ሞሀመድ አሊ የተባለው ይህ ኢራናዊ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በርካታ ሴቶች እንደሚያገባቸው ቃል በመግባት አስገድዶ ደፍሯቸዋል ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በተከሰሰበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ትፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መሀመድ አሊ ከ10 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከእሱ የጸነሱትን ልጅ እንዲያስወርዱ መድሃኒት ሰጥቷልም ተብሏል፡፡

ሰውየው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 200 ሴቶች ደፍሮናል የሚል ክስም ተመስርቶበታል።

በግለሰቡ ተደፍረናል ያሉ ሴቶች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍም ተደርጎበት ነበር፡፡

ሀገሪቱም ግለሰቡን በአደባባይ በስቅላት እንዲቀጣ አድርጋለች።

#አልአረቢያ #አልአይንኒውስ

@tikvahethiopia