TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት⬇️

የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድቤት ተረኛ ችሎት በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ቦንብ ወርውረው በማፈንዳትና በማቀበል ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙት ጥላሁን ጌታቸው እና ብርሃኑ ጃፋር ላይ ፖሊስ የጠየቀባቸውን 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

ቦንብ በማቀበል ወንጀል የተጠረጠረው ብርሃኑ ጃፋር ጥቃት የፈፀሙ ግለሰቦችን ከመመልመል በቡድን እስከማደረጃት ድረስ የደረሰ ተግባር በመፈፀሙ ወንጀሉ ሽብርተኝነትን መደገፍ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዳሉትም ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ በሌሎች ላይ ከመሰከርክ እለቃለሁ ብለኞል ስለዚህ ባልሰረሁት ወንጀል እየተጠየኩ ነው ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቴን ሊያስከብርልኝና በውጭ ሆኜ እንድከራከር ሊፈቀድልኝ ይገባል በሚል ተጠርጣሪ ብርሃኑ ጃፈር ጥያቄ አቅርቧል።

ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ የጠየኩት ከኢትዮ ቴሌኮም ተጥርጣሪዎቹ ያደረጉትን የስልክ መልዕክት ልውውጥ እና የኤፍ ቢአይን የምርመራ ውጤት ለመመልከት ነው ሲል ገልጿል።

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ፖሊስ አዳዲስ መረጃዎችን አላቀረበም ሆን ብሎ ለማንገለላታት ነው ተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቀው ይህ በመሆኑ የዋስተና መብታችን ይከበርልን ሲሉ ጠይቀዋል።

ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ከወንጀል ውስብስብነት አንፃር ለምርመራ የተጠየቀው ጊዜ ተገቢ ነው በሚል ፈቅዷል። ይሁን እንጂ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የምርመራ ስራውን በአግባቡ እንዲያከናውን አሳስቧል። ጉዳዩንም ለመመልከት #ለጳጉሜ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መግለጫው ተራዘመ⬇️

ሰኔ 16 ቀን ጠ/ሚ #አብይ_አሕመድ ድጋፍ ለመግለጽ በመስቀል አደባባይ በተጠራ ሰልፍ ላይ የደረሰው ስለተፈጸመው የቦምብ ጥቃት እና የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር #ስመኘው_በቀለ ግድያ አስመልክቶ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በነገው ዕለት መግለጫ ለመስጠት የያዘውን ቀጠሮ #ለጳጉሜ 1 ቀን 2010 ዓ.ም አራዝሞታል፡፡

©DireTube
@tsegabwolde @tikvahethiopia