TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እናት_ፓርቲ #ድርድር

እናት ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ለማድረግ የታሰበውን ድርድር እንደሚገፍ ገልጾ ነገር ግን በሁለቱ ፓርቲዎች (ብልፅግና እና ህወሓት) መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በላከልን መግለጫው ነው ይህን ያለው።

እናት ፓርቲ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ሁሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው ብሏል።

ጦርነቱ ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዞን ለብዙ አሥርት ዓመታት ወደኋላ መልሷል ያለ ሲሆን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽምግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷሳ።

አሁንም ያ ውድመትና ውረድ እንውረድ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት በደስታ የሚመለከተው ኩነት መሆኑን ገልጿል።

በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው ጥሩ ነበር ከተከሰተ በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ መልካም ነበር ሲል ገልጿል።

ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው ያለው ፓርቲድ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን "አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ ጅብ ፈርቶ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ፓርቲው ለድርድሩ ውጤታማነት ወሣኝ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችን አንድ በአንድ ዘርዝሮ በመግለጫው አስቀምጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

" መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንድታደርጉ፣ መገናኛ ብዙኃንም ዕለቱን በሙሉ ሐዘናችሁን ከመላው የኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገባው እንድትገልጹ እንጠይቃለን። " - ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲዎች ትላንት ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 27 ቀን 2015 እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ ፈረመዋል።

ስምምነቱ ዋነኛው ተግባር ምንድነው ? ፋይዳውስ ? ስለ ስምምነቱስ በጋራ ምን አሉ ?

" የትብብር ስምምነቱ ፓርቲዎቻችን በሚከተሉት አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራና በትብብር እንዲሠሩ ማዕቀፋዊና ሞራላዊ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

በሀገራዊ መግባባት፣ በምርጫ፣ በሰላም ማስፈን እና መሰል ጉዳዮች  ላይ የጋራ አቋሞችን በማራመድ #በሰላማዊ_መንገድ በትብብር #እንታገላለን፡፡

በተለይ በየዕለቱ ለሚሞተው እና በድርሱልኝ ሲቃ ለሚቃትተው ወገናችን ድምጽ በመሆን ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ መሥራት ከግንባር ቀደም ተግባሮቻችን ዋናው ነው፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" እናቴን አላገኘኋትም " - አሠልጣኝ ኃይለ ኢያሱ

ዛሬ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ወደ #መቐለ ከተጓዘው የትግራይ ተወላጆችን ያቀፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት መካከል የአትሌት ለተሰንበት ግደይ አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ አንዱ ነው።

አሰልጣኙ ከ2 ዓመት መለያየት በኋላ ዛሬ ከቤተሰቦቹ ጋራ መተያየቱን የገለፀ ሲሆን እናቱን ግን በህይወት እንዳላገኛቸው ገልጿል።

" #ሰላም_ያመጡ ሰዎችን አመሰግናቸዋለሁ " ያለው አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ " ወደ ሀገሬ በመምጣቴም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ሆኖም #እናት እና ሀገር አንድ ናቸው። ባጋጠመው ሊሆን በማይገባው ሁኔታ #በመድኃኒት_እጦት ምክንያት ሕይወቷ ማለፉን ነግረውኛል " ሲል ለቪኦኤ ሬድዮ ተናግሯል።

Credit : ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ ትላንት እሁድ በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ መከልከሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

ፓርቲድ " ክልከላ በእሳት ፈትኖ እንደ ብረት ቢያጠነክረን እንጂ ሸብረክ እንድንል አያደርገንም " ብሏል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በቅድሚያ 6 ኪሎ የሚገኘው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሥር የሚተዳደረው የስብሰባ ማዕከል አዳራሽ ይሁንታ አግኝተን በመንግሥት ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

ቀጥሎም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኩል አስይዘን ስለነበር ወደዚያ ቀይረን እንዲሁ ለጉባኤው ከ48 ሰዓት በታች ሲቀር በድጋሚ ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

#የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ ሦስተኛ አማራጭ ከብዙ ድካም በኋላ የቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሰርግ አዳራሽ ሕጋዊ ሂደቶችን አሟልተን፣ ክፍያ ፈጽመን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አስገብተንና ትላንት ጠዋት ከሀገራችን 4ቱም ማዕዘናት ከመጡ ከ700 በላይ አባላት ተገኝተው፣ የተጋበዙ የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን ወደአዳራሽ ስናመራ “ከመንግሥት የመጣ ትዕዛዝ” በሚል ወደውስጥ እንዳንገባ ታግደናል፡፡     
   
በዚህ መሐል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓላፊ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳዩን አስረድተን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ በተዋረድ ካሉ የጸጥታ ተቋማት ሓላፊዎች ጋር ቢደወልም መፍትሔው ሊቀርብ አልቻለም፡፡

ፓርቲያችንም ከ3 (ሦስት) ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገበት ጉባኤ ሳይከናወን አባላትን ለከፍተኛ እንግልት ዳርጎብናል፤ እንደፓርቲም ከፍተኛ የገንዘብ ኪሣራና የሥነልቡና ጉዳት አድርሶብናል፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " እናት እና ልጅን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል " በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል። ትናንት ምሽት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከምሽቱ 12:05 ሰዓት በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጎርፍ…
" የአራቱም ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ " ማንጎ ሰፈር " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ #እናት እና #ልጅን ጨምሮ 4 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸዉን ተከትሎ የአስክሬን ፍለጋ ሲደረግ ውሏል።

በዚህም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የዋናተኛ ቡድን የአራቱንም ሰዎች አስከሬን ማግኘት እንደቻለ ኮሚሽኑ አሳውቋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሟቾቹን አስከሬን ለማግኘት በተደረገዉ ጥረት ለአካባቢዉ ማህበረሰብና ለጸጥታ ሀይሎች ምስጋናዉን አቅርቧል።

#ሰሞኑን_እየጣለ_ባለዉ_ዝናብ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም ህብረተሰቡ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በዚህ መግለጫው፤ መንግሥት " ኦነግ ሸኔ '' እያለ ከሚጠራው የታጠቀ ቡድን ጋር በታንዛኒያ እያደረገው ያለው ድርድር ከሴራ ፖለቲካ በፀዳ መልኩ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ምኞቱን ገልጿል።

እናት ፓርቲ ፤ " ካለ ፍትሕ ሰላምን ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን ብናምንም ድርድሩ ከተለመደው የሴራ ፖለቲካ በጸዳ መልኩ ተከናውኖ በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ሊታደግ በሚችል መልኩ እንዲቋጭ እንመኛለን፡፡ " ብሏል።

መንግስት ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ሀሳብ ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም የጋራ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችል ውይይት እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ የአማራ ክልል ብልጽግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያን ተከትሎ መንግስት አሁንም " ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች" ን ትጥቅ በማስፈታት " ሰላም አስከብራለሁ " በሚል በአማራ ክልል የጀመረው እንቅስቃሴ ከሕወሓትና " ኦነግ ሸኔ " ጋር የታለፈበትንና አገርን ውድ ዋጋ ያስከፈለ አካሄድ የሚደግም ነው ብሎታል።

" መንግስት ካለፈ ስህተቱ መማር ሲገባው  ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት አገርንና ሕዝብን የሚከት፤ የክልሉን ወጣት ለአመጽ የሚጋብዝ " ነው ያለው ፓርቲው " በዚህም ከቀደሙት መደበኛ ጦርነትና የሽምቅ ውጊያ ሂደቶች ትምህርት ያልወሰደ፣ የሚያስከትለውንም መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መዘዝ በአግባቡ ያላገናዘበ አደገኛ የማንአለብኝነት አካሄድ እየተከተለ ነው " ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

ስለዚህ መንግሥት ከጀመረው የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችን የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት ወዘተ. በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ አካሄዶች ራሱን አቅቦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር አጽንዖት ሰጥቷል።

ከዚህ ውጭ የድርድርና የውይይት ፍኖትን ባለመሻት መንግሥት በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፥ በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦች መፅናናት ተመኝቶ ፤ ምርመራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች በአግባቡ ባልተለዩበት ሁኔታ የሚደረጉ ፍረጃዎች የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛባው ገልጿል።

(ፓርቲው የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት #ኢሕአፓ #መኢአድ

እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ ዛሬ በሰጡት የጋራ መግለጫ መንግሥት በአማራ ክልል ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም ጠይቀዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ መጣሉ አስታውሰዋል።

" ጦርነቱ የትግራይ ፣ የአማራ፣ የአፋር ህዝብን የበለጠ  ጎድቶታል " ያሉት ፓርቲዎቹ " ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን  የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፤ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፤ ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል፤ የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል " ብለዋል።

ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መክፈቱን የገለፁት ፓርቲዎቹ " ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነገሮች በተወሳሰቡበት ሁኔታ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል ሠራዊት አዝምቶ ' ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት ' በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል ሲሉ ሶስቱ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ ገልጸዋል።

" የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በኃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ የጠየቁት እነዚህ ሶሶት ፓርቲዎች " ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት #የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " -  ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ (የኢሮብ ወረዳ ነዋሪ) #እናት

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚገኙ የኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ የከፋ ችግር ላይ መሆናቸው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

" የሰብዓዊ እርዳታ ካቆመ ብዙ ጊዜ ተቆጥሯል " ያሉት ወ/ሮ ትብለፅ ልጆቻውን ለመመገብ መቸገራቸውን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅዬ በመጠለያ ውስጥ ነው ያለሁት፤ እርዳታ ብዙም አላገኝም ነበር  ፤ አሁን ደግሞ ካቆመ ብዙ ጊዜ አልፎታል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብ ለማስተዳደር በጣም ከባድ ነው በፈጣሪ ኃይል ነው ያለነው። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እርዳታ ቆሟል ፤ ይህ ከፍተኛ ስጋት ነው ያሳደረብን " የሚሉት ወ/ሮ ትብለፅ " ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " ሲሉ ምን ያህል አስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስረድተዋል።

ቀድሞውኑም ችግር ላይ የነበሩት እነዚህ ዜጎች አሁን ላይ እርዳታ ማቆሙ የከፋ ችግር ላይ ጥሏቸዋል።

አንዲት የኢሮብ ነዋሪ በሰጠችው ቃል " በአሁን ሰዓት ለህፃናት #ወተት ለመስጠት ቀርቶ አንድ ዳቦም ቢሆን አይናቅም ለእኛ ትልቅ እርዳታ ነው ፤ እርዳታ ወደዚህ መምጣት ካቆመ ብዙ ወራት አልፏል ረሃብ ላይ ነው ያለነው " ስትል ሁኔታውን ገልጻለች።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ አሁን ላይ የተገኘው ሰላም በጣም እንደሚያስደስት ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

" ህዝባችን ወደቦታው ተመልሶ ሰርቶ እንዲበላና ከእርዳታ ጠባቂነት እንዲላቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በጋር መስራት አለባቸው " ሲሉ መልዕልት አስተላልፈዋል።

የኢሮብ ነዋሪዎቹ በአካባቢያቸው የኤርትራ ኃይሎች እንደሚንቀሳቀሱ በመጠቆም ይኸው ኃይል ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ እንዲደረግ የሚመለከታቸው አከላት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እግድ " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን…
#እናት

" የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው እናሳስባለን " - እናት ፓርቲ

እናታ ፓርቲ ፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙኃን ተቋም ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤነው አሳሰበ።

ፓርቲው ይህን ያሳሰበው ትላንት በላከልን መግለጫ ነው።

" በህግ ሽፋን በጊዜያዊነት እንዲዘጋ ዉሳኔ የተላለፈበት የማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙኃን ተቋም የሠራዉ ጥፋት ካለ በግልጽ ቀንና ሰዓቱ ተጠቅሶ ሕዝቡ እንዲያዉቀዉ ማድረግ ያስፈልጋል። " ያለው እናት ፓርቲ " ይህ ባልሆነበት ሁኔታ መገናኛ ብዙሃን ድርጅቱን በተለመደው አይነት ጥቅል ፍረጃና ካለ ተጨባጭ አሳማኝ ማስረጃ ማገድ ተገቢ አይደለም " ሲል ገልጿል።

" ህዝባችን መረጃዎችን በነጻነት የማግኘት መብቱን ሊነጠቅ አይገባም " ያለው ፓርቲው " የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው እናሳስባለን " ብሏል።

የማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙሃን ተቋም ኅብረተሰቡን የማገልገል መብቱ ተጠብቆለት የእግድ ትዕዛዙ በአስቸኳይ እንዲነሳለት እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ፈተናውን ብዙዎቹ ሊያልፉ ይችላል የሚል ግምት ነው የተያዘው " - የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል #ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል። በቅርቡ ለሚተገብረው #የሠራተኞች_ድልድል ሲባል…
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ የሚሰጠውን የመንግሥት ሰራተኞችን ፈተና ተቃወመ፤ እንቅስቃሴው እንዲቆምም ጠይቋል።

ፓርቲው ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " የመንግሥት ሠራተኞችን ፈተና ፈትኜ ምደባ አደርጋለሁ " እያለ የሚገኝበት ሁኔታ ሲቪል ሰርቪሱን ይበለጥ ውጤታማ ለማድረግ ተፈልጎ ሳይሆን በፖለቲካዊ ውሳኔ የመጣ በመሆኑ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

መንግሥት እያደረገ የሚገኘው የፈተና እሩጫ የማይፈልጋቸውን ሠራተኞች ለማሰወገድ በአንጻሩ ደግሞ የሚፈልጋቸውን ለመተካት ሆን ብሎ ያቀናበረው ስልት ነው ሲል ፓርቲው ገልጿል።

" የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንንም መንግሥት በተመሳሳይ መልኩ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ፈተና እየፈተነ መሆኑን አረጋግጫለሁ " ያለው ፓርቲው " የፈተናውን መልስ በክፍያ የሚያሰራጩ ግለሰቦች አጋጣሚውን እንደ ገንዘብ ማግኛ ምንጭ አድርገው እየተጠቀሙበት ይገኛል " ብሏል።

በተጨማሪም ከፈተናው በፊት መልሱ በየትምህርት ቤቱ አስቀድሞ ተለጥፎ መገኘቱንም ለመረዳት እንደቻለና ይህ ተከትሎም ፈተናው ለጊዜው መቋረጡን እንደደረሰበት አሳውቋል።

በዚህ ያህል መጠን በተዝረከረከና ለከት ባጣ ሁኔታ ሠራተኛውን "ፈተና ትፈተናለህ '' ብሎ ማዋከብ ድብቅ አጀንዳ ከሌለው በስተቀር አንዳች ረብ የለውም ያለው እናት ፓርቲ ፤ የሠራተኞች ፈተና አሰጣጥ መንገዱ ሕጋዊ ባለመሆኑ፣ የግልጽነት ችግር ስላለበት እና በፖለቲካዊ ውሳኔ የመጣ ጉዳይ በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብሏል።

ፓርቲው በተለይ ብሔር መጥቀስን መሠረት ያደረጉ ፎርሞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች በሰው ሀብት የሥራ ክፍል አማካይነት አስገዳጅ በሆነ መንገድ እንዲሞሉ እየተሠራ መሆኑን ማረጋገጡን ገልጾ ይህ ደግሞ መንግሥት እየሄደበት ያለውን አካሄድ ይበልጥ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል ብሏል።

በመሆኑም ፦

- መንግሥት በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ የአዲስ አበባ የመንግሥት ሰራተኞችን ፈተና የሚፈትንበት መንገድ እና እያከናወነ የሚገኘው ምደባ ሕጋዊነት የሌለው ኢ-ምክንያታዊ የጥድፊያ ሥራ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም፤

- በአዲስ አበባ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እየሰሩ የሚገኙ ሠራተኞች "ብሔር" እንዲሞሉ የሚያስገድደው ፎርም በአስቸኳይ እንዲቆም፤

- በአዲስ አበባ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የፈተና አሰጣጡን፣ ምደባውን እና አስገዳጅ የ"ብሔር" ጠቃሽ ፎርሙን በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወሙ እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 11 ንፁሃን ነው የተገደሉት " - የዶዶላ ከተማ አስተዳደር በዶዶላ ባለፈው ሰኞ ዕለት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በተፈፀመ ጥቃት 11 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል። የከተማው አስተዳደር ለሬድው ጣቢያው " በዕለቱ በድንገት በተፈፀመ ጥቃት 11 ሰዎች ሞተዋል። በጥይት ተመተው የተጎዱም አሉ። ከጥቃቱ ጀርባ በገደብ አሳሳ ፣ አዳባ፣…
#እናት

እናት ፓርቲ ፥ " መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል።

ይህን ያለው ከሰሞነኛው የዶዶላው ግድያ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው።

" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ባለፋት ሶስት አስርት ዓመታት እጅግ በጣም አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል " ያለው ፓርቲው " በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት በቤተክርስቲያኗ እና ምእመናኗ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ እና አሰቃቂ ግድያዎች ክፉኛ ተጠናክረው ቀጥለዋል " ሲል ገልጿል።

ፓርቲው ፥ በዶዶላ ከተማ ባለፈው ሰኞ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ  ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ መርጌታ፣ 2 ልጆቻቸው እና ባለቤታቸውን ጨምሮ ከ2 ወራት በፊት ሥርዓተ ጋብቻቸውን የፈጸሙ ሙሽሮች (አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ታላቅ እህቱ ጋር) በአጠቃላይ 7 ንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም በቀን ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ 4 ንጹሐን ዜጎችም በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል።

ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 7 ሰዎችም በዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁሟል።

ፓርቲው ፤ " ከዚህ ማብቂያ ካጣው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆምና መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከእነዚህ ንጹሐን ደም  ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ የሚያካሂደው ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል መሆኑን በመግላጽ መንግሥት በአባላቱ ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ እና እስር እንዲያቆም አሳሰበ።

ፓርቲው ፤ የቅዱስ ላልይበላና አካባቢው ቅርንጫፍ አባሉ አቶ ሰብስብ ገናነው ከቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት አሳውቋል።

አቶ ሰብስብ ሰኔ 4/2016 ዓ/ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን ፓርቲው ገልጿል።

ቤተሰቦቻቸው " መጠየቅ አትችሉም " በመባላቸው ምክንያት እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ አመልክቷል።

እናት ፓርቲ ፥ " የአባላቶቼ አፈናና እስር የፖለቲካችን ስብራት አንድ ማሳያ ነው " ሲል ገልጾ " ትግላችን ሰላማዊ በመሆኑ መንግሥት አባላቶቻችንን እያሳደደ ማሰሩን ሊያቆም ይገባል " ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia