TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሟቾች ቁጥር 21 ደረሰ‼️

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ባለ አምስት ኮከቡ ዱሲት ዲ2 ሆቴልና የንግድ ማዕከል ባሳለፍነው ማክሰኞ #በታጠቁ_ኃይሎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

ጥቃቱ ከተከፈተበት ቅንጡ ሆቴልና የገበያ ማዕከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው የወጡ ሲሆን 28 ሰዎች ቆስለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው 19 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።

አልሸባብ እጄ አለበት ያለውን ጥቃት ለመቆጣጠር የፀጥታ ኃይሎች 19 ሰዓታት ወስዶባቸዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ትናንት በበብሔራዊ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ጥቃተን የፈፀሙት #አምስት ታጣቂዎችን #በመግደል የኦፕሬሽን ስራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ኬንያ አልሸባብን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ከላከችበትከፈረንጆቹ 2011 ጥቅምት ጀምሮ የሽብር ቡድኑ የጥቃት ዒላማ ሆናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተማሪዎች አስተማሪያቸውን #በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ‼️

ሦስት ተማሪዎች #ሞባይል ተወስዶብናል በሚል ሰበብ በአስተማሪያቸው ላይ ከተፈጸመ ግድያ ጋር በተያያዘ ኬንያ ውስጥ ተይዘው #ታሰሩ

#ናኩሩ በተባለው የኬንያ ግዛት ሆፕዌል በተሰኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር የሆኑት ፒተር ኦማሪ በተማሪዎቹ ጥቃት የተፈፀመበት ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ ላይ ነበር።
ተማሪዎቹ ቢያንስ አንድ ሞባይል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው በመምህሩ ተወስዶብናል በሚል ነው ድርጊቱን እንደፈፀሙ የተነገረው።

ለሥነ ሥርዓትና የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ሲባል በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ሞባይል እንዳይዙ ይከለክላል።

ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት መምህሩ በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ የምሽት ትምህርትን #እያስተባበሩ ነበር።

የአካባቢው ምክትል አስተዳዳሪ ኤሊም ሻፊ እንደተናገሩት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 150 ኪሎ ሜትር ሰሜን ምዕራብ ርቃ በምትገኘው የናኩሩ ከተማ፤ መምህሩ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ ነው ጭቅላታቸው ላይ ተመትተው ለሞት የበቁት።

ኬንያ ውስጥ በመምህራንና በትምህርት ቤቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመሆናቸው የሃገሪቱን ባለስልጣናት በእጅጉ እያሳሰበ ነው።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በምዕራባዊ ኬንያ በምትገኘው ኪሱሙ ውስጥ አንድ መምህር ከተማሪዎቹ ጋር ጠንከር ያሉ ቃላትን ከተለዋወጠ በኋላ በተማሪዎቹ በገጀራ ተመትቶ ለሞት ተዳርጓል።

ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ ኪሲ በተባለ ቦታ የሚገኝ የአንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን የቀጥታ ሥርጭት በቴሌቪዥን እንዳይከታተሉ በመከልከላቸው መኝታ ክፍላቸውን በእሳት አውድመውት ነበር።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እናት ነበረች ልጇን የገደለችው-ደሴ‼️ ‹‹ፖሊስን #በማድከሜ እና ህዝቡን #በተሳሳተ መረጃ በማስቆጣቴም ተጸጽቻለሁ፡፡›› እናት . . . ባለፈው ሳምንት ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ላይ አንድ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መፈጸሙን ተዘግቦ ነበር፡፡ ድርጊቱም አንዲት የ7 ዓመት ህጻን #ከተደፈረች በኋላ እንደተገደለች የሚገልጽ ነበር፡፡ በዕለቱም ተጠርጣሪዉ በፖሊስ መያዛቸውን እና ድርጊቱም ነዋሪዎችን ማስቆጣቱን ነበር…
#update ልጇን የገደለች የደሴ ከተማ ነዋሪዋ እናት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት #ተቀጣች። የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልጇን #በመግደል ወንጀል ተጠርጥራ የነበረችን እናት 18 ዓመት ጽኑ እስራት በይኖባታል። ወንጀሉ ጥቅምት 24/2011ዓ.ም እንደተፈፀመ መዘገቡ ይታወሳል። በዕለቱ ሌላ ተጠርጣሪ ተይዞ ነበር። ከቀናት በኋላ ግን እናት "እኔ ነኝ ልጄን የገደልኋት" በማለት እጇን መስጠቷንም ፖሊስ አስታውቆ ነበር።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹፌሩን እና ረዳቱን #በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን " FSR መኪና " ይዘው ከተሰወሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች አንዱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።

እንደ ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መረጃ ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቅ ጎጃም ዞን  ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፤ አባጀምበር ቀበሌ ፤ " የጨረቃን ጎጥ " ነው።

ከ " ገንዳ ውሃ " ከተማ ወደ " አዲስ አበባ " አንድ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ  ሾፌርና ረዳቱን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሰኔ 28/2015 ዓ/ም ሰዓቱ በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ ገድለው በመጣል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ፡፡

የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው ክትትል ተጠርጣሪ ወንጀለኛቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ማሳደራቸው መረጃ ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹን ክትትል በማድረግ ላይ እያለ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ/ም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ አንዱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ #ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ሌሎች ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ ነው ሲል የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል።

የጎንቻ ሲሶ እነሴና ግንደወይን ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ልዩ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ጓደኛቸውን #በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ ነው።

ጓደኛማቻቾቹ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል።

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ካበናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ " ወለቴ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት አረጋግጧል።

መኪናውም ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማወል ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia