TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በጋሞ አካባቢ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ?

አዲሱ የፌዴሬሽኑ 12ኛ ክልል " የደቡብ ኢትዮጵያ " በይፋ ከነባሩ ክልል ስልጣን ከተረከበ ኃላ በጋሞ አካባቢ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከመዋቅሩ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል።

ምንድነው ጥያቄው ?

አዲሱ አደረጃጀት ሕዝብ ሲያነሳ የነበረውን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ፤ መንግሥት የ " ጋሞ ክልላዊ መንግሥት " ምስረታን ጥያቄ ቸል በማለት የክላስተር አደረጃጀትን ተግባራዊ እያደረገ ነው በሚል ነው።

አንድ በአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ሰሞነኛውን ሁኔታ በተመለከተ ባላኩት መልዕክት ፤ መጀመሪያውንም ሲጠየቅ የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደር የክልልነት ጥያቄ ነበር ፤ ነገር ግን ያ ጥያቄ ተገቢው ምላሽ ሳያገኝ የክላስተር አደረጃጀት ተግባራዊ እየሆነ ነው ብለዋል።

የክልል ጥያቄው እንዳለ ሆኖ ከዚህ ቀደም የአዲሱ ክልል የርዕሰ መስተዳደር መቀመጫ ' አርባ ምንጭ ' ትሆናለች ተብሎ ሲነገር ቢቆይም አሁን ላይ ይህ አልሆነም ይህ ደግሞ በፖለቲካዊ አሰራር የተፈፀም የማታለል ተግባር ነው በሚል ከፍተኛ ቅሬታን አሳድሯል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን ላይ እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ጋሞ እራሱን ችሎ ክልል ይሁን የሚል ነው። ለዚህም ሃሳቡን የሚደግፉ በተለያየ መንገድ ሰላማዊ ተቃውሞ እያሰሙ ነው " ብለዋል።

ከዚሁ በ ' ጋሞ ዞን ' ካለው ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ " ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " ለትላንት ነሐሴ 4 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርብም ሰልፉ በመከልከሉ ሳይደረግ መቅረቱን ለማውቅ ተችሏል።

ፓርቲው ፤ መንግሥት የጋሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለማቋቋም የተጠየቀውን የህዝብ ጥያቄ በመቀልበስ በክላስተር ክልል ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊ እንቅስቃሴ በማቆም ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤን በሚል ነው የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው።

በሰልፉ ላይ የጋሞ ክልላዊ መንግስት ማቋቋምን በሚመለከት " ጋሞ ክልላችን አርባ ምንጭ ማዕከላችን ፤ የጋሞ ጥያቄ ክልል እንጂ ክላስተር አይደለም " የሚሉ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ታቅዶ ነበር።

የዞኑ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ግን ለህዝብ ሠላምና ደህንነት ሲባል የሰላማዊ ሰልፉ #እንዳልተፈቀደ ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ በማሳወቁ ሰልፉ ሳይደረግ ቀርቷል።

ፓርቲው ከሰሞኑን ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንግሥት ጥያቄ ለማፈን እየጣረ እንደሆነና አባላቱንም እንዳሰረበት ገልጿል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ስለ አዲሱ ክልል ምን ይላሉ ?

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከቀናት በፊት ከአርባ ምንጭ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት አዲሱ ክልል ከምስረታው ጀምሮ የዞኑን ህዝብ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲደራጅ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

" የተሰጠን ከፍላጎታችን ጋር የማይመጣጠን ነው "  አቶ ብርሃኑ " አብረውን ለተደራጁ ህዝቦች ፍላጎት አክብሮት ሲባል መቀበል ይኖርበናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የክልሉን ህግ አውጪ ጨምሮ ግዙፍ  እና ብዙ ተገልጋይ ያሉዋቸው ተቋማት መቀመጫቸውን አርባምንጭ ከተማ ማድረጋቸውን ያብራሩት አቶ ብርሃኑ ተቋማቱ የአከባቢውን የመልማት አቅም እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት  ያሳድጋሉ ብለዋል።

የዞኑ ነዋሪችም መቀመጫቸው አርባምንጭ ከተማ እንዲሆኑ የተመደቡ ቢሮዎችን ለመቀበል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከጋሞ ዞን ባገኘው መረጃ ዛሬ የዞኑ ምክር ቤት የአዲሱ ክልል " ረቂቅ ህገመንግስት " ላይ ሲመክር ውሏል። በተጨማሪ በከተማ እና በወረዳ ደረጃ ውይይቶች ሲደረጉ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ " ጉሎመኻዳ ወረዳ " አቅንቶ ነበር።

የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፤ " የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሊያዙ የተቻሉት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ በመታገዝ ነው " ብለዋል።

አቶ ሃፍቶም ፤ የትግራይ ኢትዮጵያዋ የጉሎመኻዳ ወረዳ ሰፊ አከባቢ ከሃገረ ኤርትራ የሚዋሰን በመሆኑና በጦርነቱ ምክንያት በዛላኣንበሳ ከተማ የነበረው የቁጥጥር ኬላ በመፍረሱ የተለያዩ እቃዎች በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ይተላለፋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

" ዛላኣምበሳ ጨምሮ የወረዳው ስድስት ቀበሌዎች #በኤርትራ_መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት አቶ ሃፍቶም ፤ በዚሁ በኩል ወደ ኤርትራ ለማሸጋገር የሚድረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመግታት እንዲቻል ህዝቡ ባለቤት በመደረጉ ምክንያት አመርቂ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የዞኑ የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኪዱ ገ/ፃድቃን በበኩላቸው ፤ ከግንቦት እስከ ሃምሌ 2015 ዓ.ም  የ4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ መሳሪዎች በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

የተያዙት ፦
- ጤፍ ፣
- የፊኖ ዱቄት ፣
- ቡና ፣
- የመብል ዘይት ፣
- ነዳጅ ፣
- የሞባይል ቆፎዎች ፣
- ጌሾ ፣
- በርበሬ ፣
- የቤት እቃዎች ፣
- ዘመናዊ ማዳበሪያ ፣
- ስሚንቶ ፣
- ቴንዲኖና የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉሎመኸዳና ኢሮብ ከኤርትራ የሚዋሰኑ የምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች መሆናቸው የጠቀሱት አቶ ኪዱ ፤ ብዘት ዳሞ ፣ ፋፂ ዛላኣምበሳ ፣ ሰበያ፣ ደውሃን ዓይጋ የሚባሉት ቦታዎች ዋና የህገወጥ ኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች መሆናቸው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊው ፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ንብረቶች በመቆጣጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስፍራው ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኃላፊዎች ፦
-  የኮንትሮባንድ ዝውውር እንዴት እየተፈፀመ እንዳለ
- በኤርትራ ኃይል ስር ስላሉት አካባቢዎች
- በአካባቢው ስላለው የህገወጥ ሰዎች ዝውውር
- በጦርነት ምክንያት ስለወዳደቁ ብረቶች
- የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመከለከል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ ስላለው የጋራ ስራ   የሰጡትን ቃል በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#ጥናት #ሞዴስ

በኢትዮጵያ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ " ቢቢሲ አፍሪካ ቪዡዋል ጆርናሊዝም " ባካሄደው ጥናት አመልክቷል።

ጥናቱ ፦ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ዋጋ ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማየት የተደረገ ነው። 9 የአፍሪካ ሀገራትንም ዳሷል።

ጥናቱ ፤ ዝቅተኛ ወርሃዊ ገቢን ከርካሽ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ ጋር ያነጻጸረ ሲሆን በዚህም የምርቶቹ ዋጋ የበርካታ ሴቶችን አቅም ያገናዘቡ እንዳልሆኑ ደምድሟል።

ጥናቱ የተደረገባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?
- ጋና፣
- ኢትዮጵያ፣
- ሶማሊያ፣
- ኡጋንዳ ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሩዋንዳ፣
- ታንዛኒያ፣
- ደቡብ አፍሪካ
- ኬንያ ናቸው።

በጋና ዝቅተኛ ደመወዝ ያላቸው ሴቶች ከሚያገኙት ገቢ #ከፍተኛ የተባለውን ወጪ የሚያወጡባት ሲሆን ኢትዮጵያ ከጋና ቀጥላ ተቀምጣለች ፤ ኬንያ በአንጻሩ ምርቶቹ ርካሽ የሆነባት አገር ናት።

ከ9ኙ አገራት መካከል በ6ቱ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች በየወሩ እያንዳንዳቸው 8 ነጠላ ሞዴሶችን የያዙ 2 እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለመግዛት ከደመወዛቸው ከ3 እስከ 13 በመቶ የሚሆነውን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

በጋና አንዲት ሴት ከምታገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ተብሎ ከተቀመጠው 26 ዶላር ውስጥ ሦስቱን ዶላር ወይም ከሚያገኙት 7 ዶላር ውስጥ አንዱን፣ ሁለት እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት ታወጣለች።

ይህም አሜሪካ እና በዩኬ ካሉ ሴቶች ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ ነው። በአሜሪካ ሴቶች ከሚያገኙት 1 ሺህ 200 ዶላር ዝቅተኛ ገቢ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት የሚያወጡት 3 ዶላር ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ አንዲት ሴት ከምታገኘው ገንዘብ በአማካይ ስድስት በመቶውን ለሞዴስ ታወጣለች ብሏል ጥናቱ።

በኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በፊት በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።

በዚህ ውሳኔ መሠረት እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም።

ጎረቤት አገር ኬንያ በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ በማድረግ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር የሆነችው እንደ አውሮፓውያኑ 2004 ነበር።

ከ2 ዓመት በኋላ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ አድርጋለች።

በዚህ ምክንያት በኬንያ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ዋጋ ቀንሷል። አሁን ላይ ርካሹ የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በ35 የአሜሪካ ሳንቲም ይሸጣል።

ሆኖም ሴት ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ምርቶቹ ከዚህ ያነሰ ዋጋ ለተገልጋዮች እንዲቀርቡ አሁንም እየጠየቁ ነው።

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢዝነሳችሁን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናችሁ?

ለVisa Everywhere Initiative 2015/16 E.C ልዩ የኢትዮጵያ ውድድር በመመዝገብ እውቅና ማግኘት፣ የቬንቸር ካፒታሊስቶችን ዐይን መሳብ ፣ ኢንቬስትመንት እና አጋሮችን
ማግኘት ይቻላል።

ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14 ድረስ ክፍት ነው።
https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-i
nitiative/initiative.html

#EverywhereInitiative
TIKVAH-ETHIOPIA
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ? በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ ? #ባሕርዳር ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው…
#Amahra

በአማራ ክልል ከተሞች ላይ ያለው አንፃራዊ ሰላም አሁንም መቀጠሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ፤ ከተማዋ ወደ ቀደመው መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ገልጸዋል።

የሰዎች እንቅስቃሴም ካለፉት ቀናቶች በተሻለ መኖሩን ጠቁመው አሁንም አንዳንድ በትልልቅ ቋጥኞች የተዘጉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ፤ ካለፉት ቀናት ጀምሮ በከተማው የቱክስ ድምፅም ሆነ ግጭት እንደሌለ አመልክተዋል።

በጎንደርም አንፃራዊ ሰላም ያለ ሲሆን ታክሲዎች፣  የቤት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን ፤ ሱቆች እና አንዳንድ ተቋማት መከፈታቸውን ነዋሪዎች አመልከተዋል።

አንድ ነዋሪ ፤ ትላንት በርካታ የከተማው ነዋሪዎች በወፍጮ ቤት እህል ለማስፈጨት እና ሱቆች ላይ እቃ ለመሸመት ተሰልፈው መመልከቱን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ግጭቱትን ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ በመናሩ ህብረተሰቡ እየተቸገረ መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ ተቀስቅሶ የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በሸቀጦች ላይ በእጥፍ ጭማሪ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ የደሴ ነዋሪ ፤ ውጊያ ከመቀስቀሱና መንገድ በመዘጋቱ በፊት 6,800 ብር ይገዛ የነበረው አንድ ኩንታል ነጭ የዳቦ ዱቄት 8,800 ብር መግባቱን ገልጸዋል። ውጊያው ከፈጠረብን ጭንቀት በላይ የተጋነነው የሸቀጦች ዋጋ ያሳስበናል ብለዋል።

እስከ 800 ብር ይገዛ የነበረ 5 ሊትር ዘይት 1150 ብር ፤ 50 ብር የነበረው አንድ ኪሎ ሽንኩርት እና ቲማቲም 100 ብር ፣ እስከ 90 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ስኳር 120 ብር መግባቱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነጋዴ ከአዲስ አበባ ያመጣንበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ጭማሪ ለማድረግ ተገድጃለሁ ያሉ ሲሆን ይህ የነጋዴው ምላሽ ግን ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከነዋሪዎች አስተያየት የሰጡ ገልጸዋል።

ውጊያ ከተነሳ በኃላ መንገድ ተዘግቶ ስለነበር ነጋዴ በውድ ዋጋ ሊያመጣ የሚችልበት መንገድ የለም ፤ ቀድሞ ከውጊያ በፊት የገባን ምርት ጨምሮ መሸጥ ሸማቹን ለችግር መዳረግ ነው ብለዋል።

እኚሁ አስተያየት ሰጪ ምርቶችን የመከዘን ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

በባህር ዳር በግጭቱ ሳቢያ ውሃ 1 ሳምንት መጥፋቱን አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ውሃ ፍለጋ ጉድጓድ ወዳለበት ጄሪካን ይዞ ለመሄድ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በጎንደር በግጭቱ ምክንያት ለ6 ቀን ውሃ ተቋርጦ መቆየቱን አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ባልደረባ ገልጸዋል።

የውሃ አገልግሎት መቋረጡ በቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል አገልግሎቱን የሚያገኙ ወላድ እናቶች ላይ እንዲሁም በሌሎች ህሙማን ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።

ውሃ ባለመኖሩ ሃኪሞች የሚለብሱት ጋዋን ፣ ቀዶ ህክምና የሚደረግላቸው ህሙማን የሚለብሱት አልባሳት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሳይታትጠብ መቆየቱን ገልጸዋል። እንደ አማራጭ ከሌሎች ህክምና ተቋማት አልባሳትን መዋስ ፣ የዝናብ ውሃ እስከመጠቀም ተደርሶ ነበር ብለዋል።

ማክሰኞ እና ረቡዕ ችግሩ ተባብሶ ቀዶ ጥገና ተቋርጦ እንደነበር አስተውሰዋል። ከትላንት ጀምሮ ግን የተቋረጠው የሆስፒታሉ ውሃ መምጣቱን የህክምና ባልደረባው አመልክተዋል።

መረጃው ከቪኦኤ (መስፍን አራጌ) የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መታየት የጀመረው የአንበጣ መንጋ ብዛትና ስፍቱ እየጨመረ እንደሆነ የአይን እማኞች አረጋገጡ ።

ነሃሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ዞኖች በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የአንበጣ መንጋ ታይተዋል።

የአንበጣ መንጋው በምስራቃዊ ዞን ጉሎ መኸዳ ፣ ኢሮብ ፣ ፅራእ ወምበርታ ፣ ስቡሓ ሳዕስዕ ወረዳዎች ፤ በደቡባዊ ምስራቅ ዞን በእንደርታ ወረዳ ፣ በደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ታይተዋል።

የአንበጣ መንጋው ከዓፋር ክልል አቅጣጫ መምጣቱ የጠቆሙት ባለሞያዎች ፣ ህብረተሰቡ በየአከባቢው በባህላዊ መንገድ መከላከል እንዲቀጥልና ጊዚያዊ አስተዳደሩና የፌደራል መንግስትም ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው ከትግራይ መቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
                         
Photo Credit  : Ataklti Arefe / Tsegay Gebretekle

@tikvahethiopia
#COOP

የዓመቱ ትልልቅ ግጥሚያዎች እነሆ ጀምረዋል! ከመዝናኛው ዓለም አይራቁ !
የDSTV ክፍያዎን በኮፔይ ኢብር ይክፈሉ።
@coopbankoromia