TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ ፤ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭትና የጸጥታ ችግር እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ ሲከታተል መቆየቱንና ይህንኑም አስመልክቶ በነዋሪዎች እና…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰኮ) ፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ እና ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን አስታውቋል።

በመጪው ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዋጁ ላይ ለመምከርና ለመወሰን አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች በጥንቃቄ አጢኖ ተግባራዊ እንዲያደርጋቸው ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለይም ፦
- በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎች፣
- ለመንግሥት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣
- የአዋጁ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰን፣
- የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብት (mmunity) ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ፤
- በአጠቃላይ የአዋጁ እያንዳንዱ አንቀጾች ከጥብቅ አስፈላጊነት (Necessity) ተመጣጣኝነት (Proportionality) እና ሕጋዊነት (legality) አንጻር አንዲመረመሩ ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀኖች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቅት ተወግዶና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው በመንግሥት በይፋ የተገለጸ በመሆኑ ምክር ቤቱ ፦ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰንን በተለይ በጥንቃቄ በማጤን ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን ፦

👉 የጊዜ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት የበለጠ እንዳይሆን፤

👉 የከባቢያዊ ተፈጻሚነቱም ልዩ አደጋው ተከስቷል በተባለበት ቦታ ብቻ የተገደበ እንጂ በጠቅላላ ሀገሪቱ እንዳይደረግ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

(ይህ የተመለከተ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ቁጥር_6_2015_በተመለከተ_ከኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን_ኢሰመኮ_የተሰጠ_ምክረ.pdf
916.4 KB
#EHRC

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 " በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የላከው ምክረ ሃሳብ በዚህ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቶ ነበር። አብን በዚህ መግለጫው ፤ በየትኛውም አሰላለፍ እና አግባብ ስለአማራ ህዝብ የተሰለፉ ሀይሎች #ጦርነት ዘላቂ ጥቅምን ለማረጋገጥ አስቻይ እንዳልሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ብሏል። ይልቁን ጦርነት ህዝብን ለተደራራቢ የማህበራዊ ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ስለሚዳርግ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄዎች ተገቢውን…
" በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ዘፈቀዳዊ የማንነት ተኮር ጅምላ እስራቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው " - አብን

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፤ በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚፈፀም ማንነት ተኮር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተስተዋለ መሆኑን አሳውቋል።

በዚህ ረገድ አዋጁን ተገን በማድረግ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ዘፈቀዳዊ የማንነት ተኮር ጅምላ እስራቶች እየተፈፀሙ መሆኑን፣ በዚህ መልኩ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ ወዳልታወቁ ቦታዎች ተወስደው መታሰራቸውን እንዲሁም ዛቻዎች፣ የቤት ብርበራዎች፣ አካላዊ ጥቃቶች እና ማንነት ተኮር ዘለፋዎች እየተፈጸሙ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል።

ከምንም በላይ ማንነት ተኮር ጅምላ እስር እና የመብት ጥሰት፤ ጽንፈኛ የፖለቲካ አተያይ ያላቸው የህግ አስፈጻሚ ግለሰቦች አዋጁን ተገን አድርገው አማራዊ ማንነትን ወንጀል የማድረግ አካሄድ በአስቸኳይ እርምት ካልተወሰደበት የሚያስከትለው ዳፋ ከባድ እንደሚሆን በጥብቅ ማስገንዘብ እንፈልጋለን ብሏል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን ገልጾ ፤ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን አጠቃላይ ስጋት በሚመለከት ክትትል እያደረገና ተጨባጭ መረጃዎችም እየደረሱት እንደሚገኙ አመልክቷል።

የደረሱትን ጥቆማዎች ተከትሎ ባደረገው ማጣራትም የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ምክንያት ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተዳረጉና በተለይም ለማንነት ተኮር እስራት እና ለቤት ውስጥ ፍተሻዎች መጋለጣቸውን ማረጋገጥ መቻሉልን በመግለጫው አሳውቋል።

በመሆኑም:-

የፌዴራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ጋር በተያያዘ በፀጥታ አካላቱ፣ በማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች፣ እንዲሁን በልዩ ልዩ አግባብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በተደራጁ ተቋማት ላይ ጥብቅ ክትትልና ምርመራ በማድረግ ከአሁን በፊት የተፈጸሙ ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲታረሙ እና ጥፋተኞችም ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

በቀጣይም አዋጁን ተገን በማድረግ ምንም እይነት ማንነት ተኮር የዘፈቀደ እስራቶች እና ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ የማድረግ ተጨባጭ ርምጃ እንዲወስዱ ፓርቲው አሳስቧል።

በተጨማሪ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎች እና አንድምታ ውጭ በማንነት ተኮር ጅምላ ፍረጃ ምክንያት የተያዙ እና በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሃን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሳስቧል።

የሀገር ውስጥና ዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀሙትን ማንነት ተኮር ጥቃቶች በማጣራት ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርጉ እንዲሁም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መልኩ በጥፋት ተግባሩ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በመለየትና ተጠያቂ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አብን ጠይቋል።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎች እና አንድምታ ውጭ በማንነት ተኮር ጅምላ ፍረጃ ምክንያት የተያዙ እና በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሃን በአስቸኳይ ይለቀቁ ዘንድ ጫና እንዲፈጥሩም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

(የፓርቲው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከምባታጠምባሮ

የዱራሜ ከተማ የምክር ቤት አባላት በሙሉ እየተደራጀ በሚገኘው ክልል ያለውን የቢሮ ክፍፍል ተቃወሙ።

አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል።

የምክር ቤት አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡት በ2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የምክር ቤት አባላት ምን አሉ ?

አዲስ እየተደራጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም ያለማግኘት እና ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል በመሆኑ በፍጹም መታረም ያለበት ነው ብለዋል።

እኩል የመልማት ፣ የመበልፀግና የማደግ መብት እንዲከበርም ጠይቀዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ  ክልል " የክላስተር አደረጃጀት ያለው ኢ-ፍትሃዊ አደረጃጀትን በሙሉ ድምፅ በመቃወም ፤ በቀጣይ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ በመጠየቅ አስቸኳይ ጉባኤያቸውን አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ በቢሮ ክፍልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የዱራሜ ነዋሪዎች ሰኞ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰልፉን የሚያስተባብረው አካልም ከከተማው ፍቃድ እንዳገኘ ተሰምቷል። በዚህም ሰኞ ጥዋት ከ3 እስከ 5 ድረስ በዱራሜ ኢፍትሃዊ ነው የተባለውም የተቋማት ክፍፍል የሚቃወም እና ማስተካከያ እንዲደረግበት የሚጠይቅ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው ?

" ለጦርነት የሚዘጋጅ ኃይል ሰራዊቱን አይቀንስም ፤ ዝግጅታችን ለሰላም ብቻ ነው " - አቶ ረዳኢ ሓለፎም

" ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀች ነው " በሚል እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች #ሀሰተኛ ናቸው ሲል ክልሉ ገለጸ።

ከሰሞኑን ክልሉ " ለጦርነት ዝግጅት እያደረገ ነው ፤ በኃይል ተይዘውብኛል የሚላቸውን የክልሉ አካባቢዎች ነፃ ለማድረግ ወደ ኃይል እርምጃ ሊገባ ነው " የሚሉ የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሰራጨ ይገኛል።

" ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀች ነው " በሚል ስለሚሰራጨው መረጃ የክልሉ ጊዜያዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ረዳኢ ሓለፎም " ይህ ውሸት ነው ፤ 24 ሰዓት ሙሉ ክልሉ እየሰራ ያለው ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ ነው ፤ ጉዟችን ሁሉ ለሰላም ነው " ብለዋል።

አቶ ረዳኢ ፤ " ሰላሙ እንዲጠከር ስለምንፈልግ ነው ታጣቂ ኃይሉን እየቀነስን ያለነው ፤ ከአሁን ቀደም ከትግራይ በኩል ማውረድ የነበረብንን ትጥቅ በየጊዜው እያስረከብን መጥተናል በተፈራረምነው የሰላም ስምምነት ከትግራይ የሚጠበቁትን እያደረግን ነው ቀረ የሚባል ነገር ያለ አይመስለኝም ፤ በቀጣይነትም ይህን አጠናክረን ወደ ተሟላ ሰላም ለመሄድ የትግራይ በሮች ክፍት ናቸው " ብለዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ 24 ሰዓት እየሰራ ያለው ሰላሙን ለማፅናት ነው፤ ዘላቂ እንዲሆን ነው " ያሉት አቶ ራዳኢ ፤ " እኛ በራሳችን ማድረግ የሚገባንን እያደረግን ነው በሌላው ወገን ያልተተገበሩ ነገሮች አሉ የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ምድር ላይ ነው ያሉት፣ የሻዕቢያ ሰራዊት አሁንም በትግራይ ነው ያለው ፤ ያ በመሆኑ ተፈናቃዮቻችን አሁንም በስቃይ ነው እየኖሩ ያሉት ስለዚህ ይህ መፈታት አለበት ፤ እነዚህ ኃይሎች መውጣት አለባቸው ተፈናቃዮችም ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው " ብለዋል።

" ይህ እየሆነ ያለው ግን እኛ ያልፈፀምነው ነገር ስላለ አይደለም የሚጠበቅብንን ሁሉ እያደረግን ነው " ሲሉ አክለዋል።

አቶ ረዳኢ ፤ " ለጦርነት የሚዘጋጅ ኃይል ሰራዊቱን አይቀንስም ፤ በቅርቡ እራሱ ከ50 ሺህ በላይ ሰው Demobilize እያደረግን ያለነው ፤ አጠቃላይ ጉዟችንም ቢሆን የሰላም ነው ፤ ሰላሙ እንዲፀና ነው የምንፈልገው፤ ድሮም ቢሆን እንዳልነው ተገደን የገባንበት እንጂ መርጠን የገባንበት አይደለም ፤ በዚህ የሚመጣው ክስ (ጦርነት ሊጀምሩ ነው) ከተግባራችን ጋር የማይሄድ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህንን እያስወሩ ያሉት " ምኞታቸውን ነው " የሚሉት አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፤ " ትግራይ ወደ ሰላም መግባት የለባትም የሚል አቋም የያዙ አካላትና ኃይሎች ናቸው ሰላሟን እንዲታወክ ስለሚፈልጉ ሆን ብለው በየቀኑ አጀንዳ ያመጣሉ " ሲሉ ወቅሰዋል።

" ከጦርነት በፊትም ኮሽ ባለ ቁጥር የወያኔ እጅ አለበት ፤ የትግራይ እጅ አለበት ፣ ሶስተኛ ወገን አለበት እያሉ ነበር ህዝቡን ሲያጦዙት የነበረው ፤ በሌለ ነገር አዲስ ስሜት ፈጥረው ቀስቅሰው በትግራይ ተወላጆች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ስህተት እና ክህደት የፈፀሙት ፤ አሁንም ይህን የማስቀጠል ነገር ነው ዓላማቸው ፤ በትግራይ በኩል ለጦርነት የሚዘጋጅበት ምንም ነገር የለም ፤ እየተዘጋጀ አይደለም ፤ የትግራይ ህዝብም መስተዳደርም ዝግጅቱ ለሰላም ብቻ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#CBE

ነጋዴ ነዎት?

እንግዲያውስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርቻንት አፕ (Merchant APP) ተጠቅመው ክፍያዎትን ይቀበሉ።
==========

መርቻንት አፕ ነጋዴዎች ወይም የሽያጭ ባለሙያዎች ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡

መተግበሪያውን ከ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbebirr.merchantapp አውርደው በመጫን ባቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ይመዝገቡና መለያ ቁጥር (Till No.) ይውሰዱ ። ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር (Till No.) ወስደው ከሆነ በቀጥታ መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ፡፡

አጠቃቀሙ

1. መተግበሪያውን ከፍተው የደንበኛውን ስልክ ቁጥር በማስገባት ክፍያውን ያስጀምሩ፣

2. ገዥው የነጋዴውን መለያ ቁጥር (Till No.) እና የክፍያውን መጠን የያዘ መልእክት ስልኩ ላይ ይደርሰዋል። ትክክለኛነቱን አረጋግጦ የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) በማስገባት ክፍያውን ያከናውናል፡፡

3. የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል። አለቀ፡፡
#Update

ላለፉት በርካታ ዓመታት መቀመጫዉን በሐዋሳ አድርጎ የቆየው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሰሞኑ የስልጣን ርክክብ በሗላ ሰራተኞች ወደየተመደቡበት አካባቢ በሚሄዱበት ሁኔታ ከየሴክተር መ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ምክክር ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

በደረሰን መረጃ መስረት ሰራተኞች ከመስከረም አንድ በፊት በተመደቡበት ዞንና የምድብ ቦታ በመገኘት ስራ እንዲጀምሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከሰራተኛዉ በኩል በረካታ ጥያቄዎች እየተንሱ ሲሆን ሰራተኞች ከሚያነሷቸዉ አብይ ጥያቄዎች መካከል የትራንስፖርት አበልና ድጋፍ  የልጆች ትምህርት ቤት ማመቻቸት በሚሄዱበት አካባቢ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሁም የባለትዳሮች የመደባ ሁኔታ ተጠቃሾች ናቸው።

ጥያቄዎችን ለመፍታት ከየሴክተር መስሪያቤት ኃላፊዎችና አመራሮች በተጨማሪ ይህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋመዉ የቴክኒክ ኮሚቴ ምላሸ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ሰኞና ማክሰኞ መሆኑ ለሰራተኞች ተነግሯል።

በምደባው መሠረት የሲዳማ ክልልን ምርጫቸዉ ካደረጉ 2804 አመልካቾች መካከል 300 ብቻ ሲመደቡ ፤ በደቡብ ክልል ስር 2320 ሰራተኞች በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስር 1995 እንዲሁም በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል 35 ሰራተኞች መመደባቸዉ ለመስማት ተችሏል።

ወደ አዲስ ቦታው ተመድበው የሚሄዱት የደቡብ ክልል ሰራተኞች ስሜት ምን ይመስላል ?

ስሜታቸውን ያጋሩን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የኢንቭስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ፤ ምንም እንኳን በስራ ጉዳይ ቦታ መቀየርና ከወዳጅ ዘመድ መለያየት ያለ የነበርና የተለመድ ጉዳይ ቢሆንም ከቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ባለፈ ዉብና የብሔር ብሔረሰቦች መነሀሪያ የሆንችዉን ሀዋሳን ጥሎ መሄድ ስሜቱ ከባድ መሆኑን ይገልጻሉ።

ረዥም አመታት አብረዋችዉ ከሰሩ ባልደረቦቻችዉ ጋር መለያየታችው እንደሚያሳዝናቸው የሚገልጹት ሰራተኞቹ ፤ ተመድበው በሚሄዱባችዉ ከተሞችና አካባቢዎች ሁሉ ያለዉ ደግሞ ወገናችዉ መሆኑ አንደሚያጽናናቸዉ ገልጸውልናል።

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የጤና ቢሮ ሰራተኞች በበኩላችዉ የጉዞዉን ስሜት መግልጽ እጅግ ከባድ መሆኑን አስረድተውናል።

ረጅም ዓመታት ከሰሩበትና ጠንከራ ማህበረሰባዊ መስተጋብር ከፈጠሩበት አካባቢ ወደሌላ መሄድ ስሜቱ ከባድ መሆኑን ገልጸዋል።

አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የደቡብ ክልል የግብርና ቢሮ ሰራተኛ ደግሞ ፤ የዞንና የክልል አመራሮች በምንሄድባቸዉ ከተሞች ሁሉ ከቤት ኪራይና የሸቀጥ ዋጋ ጋር  በተያያዘ ሊከሰት የሚችለዉን ጭማሪ ለመቆጣጠር ካሁኑ የቤት ስራቸዉ ሊያደርጉት ይገባል  ብለዋል። 

@tikvahethiopia
#OFC #OLF

ቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከእያንዳንዳቸው 50 በመቶ ተወካዮችን ይዘው ለመቅረብ እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።

የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከሰሞኑን ከ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ቃለ ምልልስ ፓርቲያቸው በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕ/ር መረራ ፤ መንግሥት አሁን ላይ እየሄደበት ባለው መንገድ ወደፊት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ይደረጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጻዋል።

ያም ሆኖ ግን ለምርጫው ከኦነግ ጋር ስምምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

፣ ከእኛ ሃምሳ በመቶ ከእነሱ ሃምሳ በመቶ ተወካዮችን አዘጋጅተን በምርጫ ለመምጣት ዕቅድ አለን፡፡ " ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲያ "  ከኦነግ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዲሁም የኢህአዴግን ስርዓት በመጣል ውስጥ ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸው የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በምን ምክንያት እንደጠፉ የተጠየቁት ፕ/ር መረራ ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኔ እንደምገምተው የፖለቲካ ምኅዳሩ አልተመቸውም፡፡ " ያሉት ፕ/ር መረራ " የፖለቲካው ምኅዳር ጠቦበታል፣ በዚህ በኩልም እሳት ነው ፤ በዛም እሳት ነው መንግሥትም እሳት ሆነበት  " ሲሉ መልሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እሳቸው እና የሚመሩት ፓርቲ ከመንግሥት ጋር አብሮ እየሰራ ነው የሚባለው ወሬ ሀሰት መሆኑና ከመንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ፕ/ር መረራ ጉዲና ለጋዜጣው ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦
- አሁን ላይ ዝምታ መርጠው ስለጠፉበት ሁኔታ፤
- ስለ ኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ፤
- በኦሮሚያ ክልል ስላለው ቀውስ እና ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ፤
- ስለ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና የመንግስት ድርድር፤
- ስለ ህገመንግስት መሻሻል ፤
- በኦሮሞ እና በአማራ ፖለቲካ ስላለው ሁኔታ፤
- ስለ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ምላሽ የሰጡበት የ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ቃለ ምልልስ በዚህ ይገኛል ፦ https://www.ethiopianreporter.com/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከምባታጠምባሮ የዱራሜ ከተማ የምክር ቤት አባላት በሙሉ እየተደራጀ በሚገኘው ክልል ያለውን የቢሮ ክፍፍል ተቃወሙ። አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል። የምክር ቤት አባላቱ ጥያቄውን…
#Update

ነገ በዱራሜ ሊደረግ የነበረው ሰልፍ እንዲሰረዝ መደረጉን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

ከነባሩ ክልል / ስያሜውን " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ " በሚል እየተደራጀ ከሚገኘው ክልል የተቋማት መቀመጫ እና ድልድል ጋር በተያያዘ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቅሬታዎች እንዳሉ ይታወቃል።

ነዋሪም ቅሬታውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ሲሆን የዱራሜ ከተማ ምክር ቤትም የቢሮ ክፍፍሉ ፍትሃዊ አይደለም በሚል በሙሉ ድምፅ ተቃውሞ በማድረግ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቋል።

ከዚሁ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለው ቅሬታ ጋር በተያያዘ ነገ በዱራሜ ከተማ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነበር።

ሰልፉን ለማድረግ ሲያስተባብሩ የነበሩ አካላት " በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ የሚፈፀምን ኢፍትሃዊ ድርጊትና የልማት ተጠቃሚነትን የሚጎትት ውሳኔ የዓለም ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተዘጋጀ " ገልጸው የነበረ ሲሆን በከተማው አስተዳደርም እውቅና አግኝቶ ነበር።

በከተማው አስተዳደር የተፈደቀው ሰልፍ ነገ ከጥዋት 3 እስከ 5 ሰዓት ድረስ ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ነበር።

ነገር ግን በዛሬው ዕለት በከተማው ከንቲባ በተፃፈ ደብዳቤ " ሰልፉ መሰረዙ " ተገልጿል።

የከተማው አስተዳደር የሰልፉ መሰረዝ " በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ያለዉን ግጭት ምክንያት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን ወደ ብጥብጥ በመቀየር የሰዉ ህይወት እንዲያልፍና ንብረት እንድወድም ለማድረግ የተዘጋጁ ሀይሎች አንዳሉ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ በጥልቀት የገመገመ በመሆኑ ነው " ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ፤ የቢሮዎች ድልድል ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ መንግስት ከዞን አመራር ጋር በመቀናጀት ምላሽ እንደሚሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ ተሰርዟል ሲል አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ " በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የክላስተር ማዕከላት ከተሞች የቢሮዎች ድልድል ሒደት ለከምባታ ጠምባሮ ዞን የተደለደለው የቢሮ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን በተመለከተ የዞኑ አመራር ባቀረበው ጥያቄ መነሻነት የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ/ም በአካል ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ዞኑ ገልጿል።

ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ዞኑ ገልጿል።

በዚህ መነሻነት የሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዱራሜ ከተማ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ በማግኘቱ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ወደ ልማት ሥራዎች ፊቱን እንዲያዞርና ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

የዞኑ አስተዳደር በሰጠው ማብራሪያ ምን ያህል ቢሮ እንደተጨመረ፣ የተጨመሩት ቢሮዎችስ የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia