TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" ግለሰቡ ህፃናቱን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የ ' ግብረሰዶም ወንጀል ' የፈፀመ ግለሰብ  በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገለፀ።

የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው በክ/ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5 ፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል።

ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ሌሎቹ 2 ህፃናትም ተመሳሳይ ድርጊት እንደፈፀመባቸው በመግለፃቸው በ3 የምርመራ መዝገቦች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በሰው እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ በ19 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ህብረተሰቡ ከህግ እና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

#ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፁም የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ  መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይችላል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia