TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሞና የሲዳማ ሊህቃን የምክክር መድረክ‼️

“የሲዳማ ህዝብ ራሱን ለማስተዳደር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው” - አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ
.
.
የሲዳማ ህዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቴዎስ አስታወቁ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የኦሮሞና የሲዳማ ሊህቃን የምክክር መድረክ ላይ ነው። 

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በሀዋሳው ስብሰባ ለተሳተፉ ታዳሚያን ባሰሙት ንግግር “የሲዳማ ህዝብ በዚህች አገር ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት ባደረገው አስተዋጽኦ ልክ ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎት አለው” ብለዋል፡፡ የሁለቱን ህዝቦች ሊህቃንን ያገናኘው የዛሬው መድረክ “የሲዳማ ህዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት [መካሄዱ] ልዩ ያደርገዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡ 

የዛሬ የሀዋሳው የምክክር መድረክ ዓላማ “ሁለቱን ህዝቦች የሚወክሉ ፖለቲከኞች ልምዳቸውን ለመጋራት እና በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሀሳብ ለመለዋወጥ” እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይም አንጋፋና ወጣት ፖለቲከኞች ተሳትፈዋል፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገቡት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) መስራቾች እና አመራሮች የውይይቱ ተሳታፊዎች ነበሩ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ  “በኢትዮጵያ አሁን የተገኘው የፖለቲካ ለውጥ አዲስ የኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና የተገኘበት ነው” ብለዋል፡፡ “ቀደምሲል የነበረው ኢትዮጵያዊነት ከዝንጉርጉርነት ይልቅ አንድ አይነት ቀለም የሚታይበት ነበር” ያሉት አቶ ሌንጮ “ከዚህ በኋላ ማንነትህን ከደጅ ጥለህ ኢትዮጵያዊ ትሆናለህ የሚለው አካሄድ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

ሌላው የመድረኩ ተናጋሪ የኦዴግ አመራር አቶ #ሌንጮ_ባቲ በበኩላቸው “ወጣቶች ማለቂያ በሌለው ተቃውሞ ውስጥ በመግባት አሁን የተገኘው የፖለቲካ ምህዳር እንዳይበላሽ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ወጣቶች “በተለይም የሚያዳምጥ መንግስት ሲገኝ ጥያቄዎችን በሰከነ እና ሰላማዊና በሆነ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባቸው” ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ 

ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀዋሳን ሃይቅ ዳርቻ በማልማትና በማፅዳት ከተማዋን #በዓለም በማስተዋወቅና የጎብኝዎች መዳረሻ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቴዎስ ተናግረዋል። በጅግጅጋ በተካሄደው 8ኛው የከተሞች ፎረም ለ7ኛ ጊዜ ራስን በማስተዋወቅ ሀዋሳ ከተማ 1ኛ መውጣቷን ምክንያት በማድረግ ለከተማው ማህበረሰብና ባለሀብቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የሽልማትና እውቅና ስነ ስርዓት ላይ 25 ባለሀብቶች ሲሸለሙ ከተማዋ ራሷን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ቦታ እንድታገኝ የሰሩ 244 ባለሙያዎችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia