TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልልና የሱማሌ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በምክክር መድረኩ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ላቀ አያሌው የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ለሶማሌ ክልል የልዑክ አባላት #ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የአማራ ክልል ለሶማሌ ክልል ሁሉም የልዑክ አባላት አገልግል እና የዘጌ ቡና በስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የሶማሌ ክልል ልዑክ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትሥሥር የሚያጎለብት ውይይት ተካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መሥራችነት የተጀመረው የባሕር ዳር የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ የሳይንስ ማዕከሉ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን የሳይንስ ትምህርቶችን ያስተምራል፡፡ ተማሪዎቹ በ8ኛ ክፍል ውጤታቸው ተመርጠው ነው ማዕከሉን የሚቀላቀሉት፡፡ ማዕከሉ የመጀመሪያዎቹን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ሐምሌ 14 2011ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የላቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ዓላማ አድርጎ ነበር የተቋቋው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ለክልሉ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአማራ መገናኛ ብዙኻን ዛሬ ባስተላለፉት ማብራሪያ የሰኔ 15ቱ የባለ ሥልጣናት ግድያ ወንጀል ምርመራ እስካሁን ያልተጠናቀቀው ወንጀሉ ውስብስብና ምርመራው ዘርፈ ብዙ ስለሆነ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርብ ዝርዝር ሪፖርት እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሴራውን በማክሸፋችን ክልላችን ከመፍረስ አድነነዋል፤ ባንቆጣጠረው ኖሮ ግን የባሰ ትርመስ ይፈጠር ነበር ብለዋል፡፡ እስካሁን በተደረሰበት ድምዳሜ ከጀርባ ስላሉ አካላት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ ድምዳሜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል #ፌስቡክ ላይ የሚሰሩ ሃይሎች ግን ከባድ ችግር ስለፈጠሩብን መንግሥት ያግዘን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ_15 #ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ለተፈጠረውን ችግር የፀጥታ ተቋማት መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት አለመስጠታቸው እንደሆነ አመለከተ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በጋራ የተስማማባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅርቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተፈጠረውን ችግር የተመለከተ ጉዳይ አቅርቧል፡፡ የጥፋት መንስኤው የፀጥታ ተቋማት አመራሮች መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት ባለመኖሩ መሆኑን ለምክር ቤት አባላቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

በክልሉ መንግሥት የሠላም እና ደኅንነት ተቋም ላይ ችግሮች ከመከስቱ በፊት የፖለቲካ አመራሩ አስቀድሞ ዋነኛ መንስኤዎችን እየለዬ መፍታት ባለመቻሉ የተከሰተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሰኔ 15/2011ዓ.ም የተፈፀመው ድርጊት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በመቆጣጠር በወቅቱ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ መሪዎችን በመክበብ ግድያ መፈጸሙ፤ በቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም ስልጣን ለመያዝ የተፈፀመ መሆኑን ነው ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው፡፡ የክልሉ ሕዝብ፣ የክልሉ እና የፌዴራል ፀጥታ አካላት ችግሩን ለመፍታት ባስተዋይነት ለወሰዱት ፈጣን እርምጃ እና መሰዋዕትነት ለከፈሉት ወዳጅ ዘመዶቻቸው የክልሉ ምክር ቤት መፅናናትን እየተመኘ በማንኛውም ወቅት ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጧል፡፡

አሁንም ቢሆን በወቅቱ የተፈጸመውን ድርጊት ለመሸፋፈን መሞከር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/AM-07-23

@tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ከነማ

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች እና ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ባህር ዳር ከነማን ለማሰልጠን #ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋሊዎቹ በምክትል አሰልጣኝት እየሰራ የሚገኘው ፋሲል ተካልኝ የጣናው ሞገድን ለማሰልጠን በቃል ደረጃ ተስማምቷል፡፡ ከዋሊያዎቹ ጋር ድሬዳዋ የሚገኘው ፋሲል ተካልኝ የባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ለመሆን እንደተስማማ የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አማረ ዓለሙ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ከነማ

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለአንድ ዓመት ባሕር ዳር ከነማን ለማሰልጠን ዛሬ ፈርሟል፡፡ ቡድኑን ለማሰልጠን በቃል ደረጃ ተስማምቶ የነበረው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ዛሬ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም ፊርማውን አስቀምጧል።

Via #AMMA
ፎቶ: #SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

‹‹ዛሬ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ቤቴ በመፍረሱ ዝናብ ይዘንብብኝ ነበር፤ ፈጣሪ እድሜያችሁን ያርዝመው።›› በበጎ አድራጎት ስራ ቤታቸው እየተሰራላቸው ያሉ አዛውንት

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ስራ እያከናወኑ ነው፡፡ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ዛሬ ነሐሴ 8/2011 ዓ.ም 15 የአቅመ ደካሞች እና በደባል ሱስ ጉዳት ውስጥ ያሉ ወጣቶችን ቤት ለይተው አፍርሰው በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ በአጭር ቀናት ግንባታቸውን አጠናቅቀው እንደሚያስረክቧቸው የክፍለ ከተማው የማህበራዊ ልማት ዘርፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደስታዬ ማረው ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ 1 ሺህ 864 የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ከሐምሌ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ የጽዳት፣ የደም ልገሳ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ማስተማር፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ጥገና እና አፍርሶ ግንባታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ወጣቶቹ እስካሁን ሲሰሩ የቆዩት በገንዘብ ሲተመን 129 ሺህ 719 ብር እንደሚገመት ገልፀዋል። ወጣቶቹ በበጎ ፍቃደኝነት 60 ሺህ ብር በማዋጣት ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ እያዋሉ እንደሚገኙም አቶ ደስታዬ አብራርቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት ወንጀል የቅድመ ክስ ምርመራ ምስክርነት ዛሬ በባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደመጥ ጀመረ።

በዚህም በነ የማነ ታደሰ መዝገብ ስር በተከሰሱ 48 ግለሰቦች ላይ ቅድመ ክስ ምርመራ ምስክርነት እንዲደመጥ የአቃቤ ህግ ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

የተከሳሽ ጠበቆችም በጋራ በመሆን የክስ አቀራረቡ ዝርዝር ማስረጃ የለውም፣ ማን ምን፣ የት እና እንዴት ፈጸመ የሚለውን አያሳይም፣ የምስክሮችን ስም አይጠቅሰም ስለዚህ ክሱ እንደገና ተሻሽሎ ይቅረብ ካልሆነ ደንበኞቻችን በነጻ ሊቀቁ ይገባል በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል።

ዓቃቤ ህግም ክስ ጥቅል ነው ለተባለው ወታደሮች በህብረት ሆነው የፈጸሙት ወንጀል በመሆኑና የምስክሮች ስም ቀድሞ ያልተጠቀሰው ለደህንነታቸው ሲባል በመሆኑ ተገቢ ነው ምስክር የማስማት ሂደቱ እንዲቀጥል ይፈቅድልን ሲል ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የዓቃቤ ህጎችን የክስ መሰረተ ሃሳብና የጠበቆችን የመቃዋሚያ ካዳመጠ በኋላ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ጉዳዮች ያለአግባብ ሊጓተቱ አይገባም በማለት ምስክርነት የመደመጥ ሂደቱ እንዲቀጥል ፈቅዷል።

በዚህም ከሰዓት በፊት በነበረው ችሎት የአንድ መስክር ቃል መደመጡንና የቀሪዎችን ለመስማት ከሰዓት ስምንት ሰዓት በመቅጠር ከሰዓት በፊት የነበረው የፍርድ ቤቱ የችሎት ተጠነቋል።

በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት 218 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት በርካቶቹ በየጊዜው ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው እየተጣራ መለቀቃቸው የሚየታወስ ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ ወር በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙ የእሳት አደጋዎች ፦

#ወልቂጤ_ከተማ (ጉራጌ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በኩር ክ/ከተማ አርሴማ መንደር

• የደረሰው ጉዳት - 14 ቤት ሙሉ በሙሉ 6 ቤት በከፊል ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

#ቤሮ_ወረዳ (ምዕራብ ኦሞ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ሾላ ቀበሌ

• የደረሰው ጉዳት - 1840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት ፣ 109 የወርቅ ማሽን በአጠቃላይ 586 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እስካሁን አልታወቀም።

#ሆሳዕና_ከተማ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰው በአንድ የገበያ ማዕከል አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል። በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ንግድ ድርጅቶች ከነ ንብረታቸው ወድመዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ፖሊስ እያጣራው ነው።

#መካነሠላም_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• በመካነ ሠላም ከተማ በንግድ ቦታ ላይ ድንገት የተከሰተ አደጋ።

• የደረሰው ጉዳት - በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ በሴቶች የውበት ሳሎን፣ በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሳል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም።

#ወላይታ_ሶዶ_ከተማ (ወላይታ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - መርካቶ ገበያ

• የደረሰው ጉዳት - 1 ቢሊዮን 57 ሚሊዮን 670 ሺህ ብር ወድሟል። 42 ሺህ ገደማ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለቀውስ ተጋልጠዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አንታወቀም፤ በፖሊስ እየተመረመረ ይገኛል።

#ማሻ_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 2 ሼዶች በውስጣቸው ካለ ሙሉ ንብረት ጋር ወድመዋል። ሼዶቹ በውስጣቸው ሱቆች፣ ፖስታ ቤት፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይገኙበታል። 1 ሚሊዮን 224 ሺህ 936 ብር የሚገመት ሃብት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም፤ እየተጣራ ነው።

#ዌራ_ወረዳ (ሀላባ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ

• የደረሰው ጉዳት - 11 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እህል የተከመረበት ቦታ ላይ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞባልይ ስልክ ፈንድቶ።

#ምሻ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ማጋቾ ቀበሌዎች

• የደረሰው ጉዳት - 128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያየ እህል፣ 18 የንብ ቀፎ ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች በድምሩ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - የተፈጥሮ እሳት

#ሶሮ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በጃቾ ከተማ

• የደረሰው ጉዳት - ከ250 ሺህ ብር በላይ ወድሟል።

• የአደጋው ምክንያት - የመብራት ኮንታክት

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

• የአደጋው የደረሰበት ቦታ - ዋናው ግቢ ህንፃ 3

• አደጋው የኤሌክትሪክ መቆጣጣሪያ ላይ የተነሳ ነው።

• የደረሰው ጉዳት - መጠኑ ያልተገለፀ ንብረት ጉዳት ደርሶበታል።

#ቡራዩ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ገብርኤል አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 16 ሱቆች ፣ 3 መኖሪያ ቤቶች፣ 3 ባርና ሬስቶራንቶች ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ ግምንቱ 10 ሚሊዮን ብር የሆነ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እየተጣራ ይገኛል።

#ባህር_ዳር_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 3 ጉዶባህር የሚባለው ሰፈር

• የደረሰው ጉዳት - 22 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በገንዘብ 300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ ነው።

#ጅግጅጋ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 2 ልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ

• የደረሰው ጉዳት - 7 የምግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ንብረት አደጋ ደርሶበታል ይህም 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ከአንድ ቤት ውስጥ ነው የተነሳው ተብሏል።

#ደብረማርቆስ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ጉልት ገበያ አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - 48 የንግድ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ አትክልት እና ፍረፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም በፖሊስ እየተጣራ ነው።

በዚህ ወር በደረሱት የእሳት አደጋዎች በርካቶች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ፣ ቤታቸው ወድሞባቸው ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

በርካቶች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

* የአብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ በግልፅ አይታወቅም።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia