TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ADAMA

በአዳማ ከተማ ባሉ ጎዳናዎች ላይ "ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በከተማው ውስጥ አንገብጋቢ ካልሆነ በስተቀር እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል" የሚሉ ማስታወቂያዎች እየተነገረ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግሩ።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ትልልቅ የድምጽ ማጉያዎችን በጫኑ መኪኖች በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በዋና ዋና ጎዳናዎች ማስታወቂያውን እያሰራጨ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለፁት።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አቶ ፀጋዬ ሁንዴና ወ/ሮ ኤልሳቤት አዱኛን በስልክ አግኝተናቸው ነበር በአዳማ ከተማ በሚገኘው የሳራ የንግድ ማዕከል ተከራይተው ለሚሰሩ ኢትዮጵያውን የሶስት (3) ወር ኪራይ ነፃ አድርገውላቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት መተጋገዝ፣ መተባበር፣ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል አዳማ ከተማ የሚገኙት 'ቱ ብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አኽ-ዋን ኃ/የተ/የግ/ማህበር 5.5 ሚልዮን ብር የሚተመን የተለያዩ እገዛዎችን ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- አቅም ለሌላቸው ወገኖች እንዲሆን ለአዳማ ከተማ መስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ግብረ ኃይል 500 ኩንታል መኮረኒ፣ 4000 ካርቶን ብስኩት፣ 500 ኩንታል ዱቄት አስረክበዋል።

- በድርጅቶቹ ውስጥ ለሚሰሩ ከ4,500 በላይ ሰራተኞች 10 ኪሎ ዱቄት እና 5 ኪሎ መኮረኒ ተሰጥቷል።

- በአዳማ ከተማ ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያዎች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የእጅ መታጠቢያ በማዘጋጀት እና ህዝቡ እራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

በአዳማ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ 55 አሽከርካሪዎች በገንዘብ መቀጣታቸውን በአስተዳደሩ የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል አሰታውቋል።

የግብረ ኃይሉ አባል ኮማንደር አለማየሁ በቀለ እንደገለጹት አሽከርካሪዎቹ የተቀጡት መመሪያውን ተላልፈው ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ ትርፍ በመጫንና ከተፈደላቸው ውጭ አገልግሎት ሲሰጡ በመገኘታቸው ነው።

በዚህም 2,000 እስከ 5,000 ብር መቀጣታቸውን አመልክተዋል፡፡ ቅጣቱ ከተላለፈባቸው መካከልም የባጃጅ፣ ሚኒባስ ታክሲዎች፣ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን፣ የቤት አውቶሞቢልና ከባድ የጭነት አሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

'የፍቅር ማዕድ' ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን!

ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን በአዳማ ከተማ ለሚገኙ 156 ወገኖች የፍቅር ማዕድ የምገባ ፕሮግራም መርሐግብርን ትላንት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ እና የፋውንዴሽኑ እና የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ሃላፊዎች በተገኙበት አስጀምረዋል።

የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ አ.ማ. ግብረ-ሰናይ ድርጅት የሆነው ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን የአክስዮን ማህበሩ አንድ ኩባንያ ከሆነው ሬድ ፎክስ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ቢዝነስ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለ156 የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ለአንድ ወር የሚቆይ የምግብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ወጪው በገንዘብ ብር 1 ሚሊዮን ይተመናል፡፡

ድጋፉ ፋውንዴሽኑ በአገሪቱ በሚገኙ ስምንት ከተሞች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የዕለት ጉርሳቸውን ማሟላት የተቸገሩ 10,000 ወገኖችን ለመርዳት እየሰራ ያለበት የፍቅር ማዕድ የተሰኘ ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑን የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ የፅ/ቤት ሃላፊ ና የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባል አቶ ፍፁም ንጉሴ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

በአዳማ ከተማ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት እና የኤፍራታ ጁስ እና ፒዛ ድርጅት መስራች እና ባለቤት የሆኑት አማኑኤል አለሙ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ–19) ወረርሽኝ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በቅርቡ ለድርጅቱ ቅርጫፍነት አስገንብተው የጨረሱትን ባለ አራት(4) ፎቅ ህንፃ ለለይቶ ማቆያ እንዲሆን ለመንግስት አስረክበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ADAMA : የጠበቃ እና ህግ ባለሞያው አብዱልጀባር ሁሴን ስርዓተ ቀብር ትላንት በአዳማ ከተማ ተፈፅሟል።

የህግ ባለሙያ እና ጠበቃው አብዱልጃባር ሁሴን ነሃሴ 5 ቀን 2013 ዓ/ም በአዳማ ከተማ (ገንደ ገዳ ቀበሌ) ነው ህይወታቸው አልፎ የተገኘው።

ከቤተሰቦቻቸው በተገኘው መረጃ በዕለቱ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ከቤት ወጥተው ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ማረፋቸው የተሰማው።

በወቅቱ አስክሬናቸው ወደአዳማ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አ/አ "ሚኒሊክ ሆስፒታል" ተወስዷል፤ በኃላም ምርመራው ሲጠናቀቅ አስክሬናቸው ወደአዳማ ተመልሶ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

በስርዓተ ቀብራቸው ላይ ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጆቻቸው እንዲሁም የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከአሟሟታቸው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአስክሬን ምርመራ ውጤት ሪፖርቱን እስካሁን በይፋ ለማወቅ ባይቻልም እሳቸው አባል የሆኑበት የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ስለአሟሟታቸው ምክንያት እና ሁኔታ ለማወቅ እየሰራ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

የህግ ባለሞያ እና ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን ከእነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ሌሎችም እስረኞች ጠበቃዎች መካከል አንደኛው ሲሆኑ ለፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው እና ለሌሎች በርካታ ታሳሪዎች ጥብቅና በመቆም በሞያቸው አገልግለዋል።

@tikvahethiopia
#Adama

ሀሰተኛ መታወቂያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።

በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች ስም በተዘጋጁ ሀሰተኛ መታወቂያ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ 13 ሰዎች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ የመረጃ ባለሞያ ረ/ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በእስራት እና በገንዘብ የተቀጡት በአዲስ አበባ ቀበሌዎች ስም ሀሰተኛ መታወቂያ ያሰሩት 10 ግለሰቦች በአዳማ ከተማ ቀበሌዎች ስም ሀሰተኛ መታወቂያ ያሰሩ 3 ግለሰቦች ናቸው።

ረ/ኢኒስፔክተር ወርቅነሽ አሁን ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ግለሰቦቹ ሊያዙ መቻላቸውን ገልፀዋል።

በአዳማ ቦኩ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው " ባቡር ጣቢያ " አካባቢአንደኛ ተከሳሽ (ወንድ)፣ ሁለተኛ ተከሳሽ (ወንድ) እና ሶስተኛ ተከሳሽ (ሴት) በህገወጥ መንገድ በተዘጋጀ መታወቂያ ወደ ድሬዳዋ ሊንቀሳቀሱ ሲሉ ተይዘዋል።

ሀሰተኛ መታወቂያው በቦሌ ክ/ከተማ ጠገቻ አራራ ቀበሌ ስም የተዘጋጀ እና ግለሰቦቹ በገንዘብ ያወጡት መሆኑና ቀበሌውን ሆነ አካባቢውን እንደማያውቁት ረ/ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ተናግረዋል።

አዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ሶስቱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በሰነድ እና በሰው ማስረጃ ተረጋገጦ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ትላንት እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት እስራት እና በ1500 ብር የገንዘብ ቅጣት ተቀጥተዋል።

በተጨማሪ በህገወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች መታወቂያ በማውጣት ወደ ሀረር ነው የምንጓዘው በሚል 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው መዝገባቸው ሲጣራ ቆይቶ እያንዳዳቸው በ4 ዓመት እስራት እና በ5 ሺህ ገንዘብ ተቀጥተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ኑሆ ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አርቲስት ኑሆ ጎበና ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞና በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ዜማዎችን ለአድማጭ አበርክቷል፡፡ አርቲስት ኑሆ ፤ ከአባቱ አቶ መሃመድ ጎበና እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ አደም በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡ #ኤፍቢሲ/#ኦቢኤን @tikvahethiopia
#Adama

የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በአዳማ ከተማ ተፈፅሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ቤተስቦቹ፣ አርቲስቶች፣ ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹ እንሲሁም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

አርቲስት ኑሆ ጎበና በድሬደዋ ቀፊራ ገንደጋራ በ1940 ዓ.ም ነበር የተወለዱት ፤ ለረጅም አመታት ለኦሮሞ ኪነ ጥበብና ለአፋን ኦሮሞ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አንጋፋ አርቲስት ነበሩ።

ፎቶ ፦ ኦቢኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Harari #SafaricomEthiopia በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል። በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል። ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች…
#ADAMA #BAHIRDAR

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል።

የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

📍ባህር ዳር

አራት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ቀበሌ 14 - የተባበሩት ፊትለፊት፣ ቀበሌ 16 - ኖክ ፊትለፊት፣ ቀበሌ 11 - አባይ ማዶ፣ ቀበሌ 12 - ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ካምፓስ ፊትለፊት) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

📍አዳማ

ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ፍራንኮ እና ፖስታ ቤት አካባቢ) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

በባሕር ዳር እና አዳማ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

የሳፋሪኮም የጥሪ ማእከል 700 ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን በዚሁ ማግኝት ይቻላል። በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Adama

ሰላም ሚኒስቴር " የአገር ግንባታ መሠረታዊያን በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር " ትላንት በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዶ ነበር።

በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደኣ፣ መሰል የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው ግጭትና አለመግባባት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ብዙ የሚያለያዩ ጉዳዮች ቢኖሩም፤ ብዙ የጋራ ትስስር የሚፈጥሩ ነገሮች እንዳሉ፣ ይሁን እንጅ ልዩነት ላይ በማተኮር ግጭቶችና አለመግባባቶች እየተፈጠሩ ከዚህ መደረሱን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ስንሻው፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ በሌለበት ማኅበራዊ ሚዲያ ሰላምን መገንባት እንዴት እንደሚቻል በገለጹበት አውድ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል።

አክለውም፣ ሰፊ ውይይት በማድረግ አገራችን ከድጡ ወደ ማጡ የምትሄድበትን ሁኔታ መቀልበስ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ፦
አገር፣ አገረ መንግሥት፣ አገረ ብሔር
አገራዊ ማንነት፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮ
አገራዊ እሴት፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮ
አገራዊ ጥቅም፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮ
የሚዲያ ሚና ሰላምን ከመገንባት ረገድ 
በሚሉት ነጥቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋግቶ የተላከ ነው።
 
@tikvahethiopia
#Adama

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው #በቁማር_የተበላዉን ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia