TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከውጭ የሚገቡ ዜጎች እራሳቸውን ለ14 ቀን ለይተው እንዲቆዪ መመርያ መሰጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ፦

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት #ግዴታ የተጣለባቸው ከየትኛውም ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በሚኖራቸው ቆይታ ሙሉ በሙሉ ወጪያቸውን ራሳቸው እንደሚሸፍኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StateOfEmergency

የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች ፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች እና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ #ግዴታ አለበት።

የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ወደክልሉ በመኪናም ይሁን በአየር የሚገባ መንገደኛ ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ የመቆየት #ግዴታ አለበት። ይህን ልናሳታውሳችሁ እንወዳለን!

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡን መረጃ መሰረት ዛሬ የተደረገውን 6 የላብራቶሪ ምርመራ ጨምሮ በትግራይ 105 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (ከዚህ ውስጥ ሀምሳ አምስቱ /55/ #EPHI ተልኮ የተመረመረ ነው) ሁሉም #ነፃ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በጎንደር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቷል።

በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ተጥለዉ የነበሩ ክልከላዎች ዉስጥ የሰዓት ገደቡ ተነስቷል።

ከምሽቱ 4.00 እስከ 11.30 የነበረዉ ክልከላ የተነሳ እና 24 ሰዓት በሰላም ሁሉም አካል ፣ ተሸከርካሪም ጭምር መንቀሳቀስ እንደሚቻል ትላንት ተወስኗል።

ሌሎች ክልልከላዎች ግን የሚቀጥሉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት ፦

• ከተፈቀደለት የጸጥታ አካሉ ዉጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• ማንኛዉም ሰዉ መሳሪያ/ተተካሽ/ ይዞ ወደ መጥጥ ቤት ይዞ መግባት ሆነ መዝናናት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• እንግዶችን ሆነ ማንኛዉንም ሰዉ ማዋከብ መረበሽ የተከለከለ ነው።
• አግባብነት የሌለዉ ዋጋ በማናቸዉም ሽያጮች አገልግሎቶች መጨመር የተከለከለ ነዉ።
• ማንኛዉም ሰዉ የሚመለከታቸዉ የጸጥታ አካላት መታወቂያ እንዲያሳይ ሲጠየቅ የማሳየት #ግዴታ አለበት።
• የብሎክ አደረጃጀት ጥበቃዉ የማይቃረጥና ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
• በፀጥታ አካሉ አማካኝነት የኬላ ፍተሸ የድነገተኛ ፍተሻ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ዘንድ ሁሉም ሰዉ ከፀጥታ አካሉ ጎን እንዲቆም ፤ ከአቅም በላይ የሆኑ የጸጥታ ችግሮች ሲገጥሙ በአቅራቢያ ለሚገኘዉ የፖሊስ ጣቢያ ሪፖረት ማድረግ ወይም በየአካባቢዉ ለሚገኝ የፀጥታ አካል ሪፖርት በማድረግ የመተባበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

መረጃው ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ "

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።

በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦
👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣
👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ሚኒስትሮች፣
👉 ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
👉 ኮሚሽነሮች፣
👉 ምክትል ኮሚሽነሮች፣
👉 ዋና ዳይሬክተሮች፣
👉 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም #ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ #ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር  የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በየተቋማቸው ያለውን የሀብት ምዝገባ መረጃን ለማንኛውም መረጃ ጠያቂ እንዲሰጡ አለማድረግ፣ ወይም ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር የሕገ መንግሥቱን የግልጽነትና ተጠያቂነት ድንጋጌንና የሀብት ማስመዝገቢያና ማሳወቂያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ጽንሰ ሐሳብና መሠረታዊ ዓላማን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መረጃ ያለመስጠት ድርጊት ለተጀመረው የሙስና ትግል ምንም ዓይነት አበርክቶ የሌለው በመሆኑ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ተቋሙ ጠይቋል፡፡

(የኢ/ሕ/ዕ/ጠ/ተቋም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ ከላይ ተይይዟል)

#Reporter
#EthiopiaInstitutionoftheOmbudsman

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#አማራ

ከፊታችን ያሉት ሃማኖታዊ በዓላት በአደባባይ እንዲከበሩ ተፈቀደ።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በአማራ ክልል ለመውሊድ ፣ ደመራ እና መስቀል በዓላት መሰባሰብን ፈቀደ።

ዕዙ ፤ መስከረም 16 እና 17 /2016 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ እየሰራሁ ነው ብሏል።

ምንም እንኳን የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ቢከለከሉም መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀዱን ገልጿል።

ዕዙ ፤ እነዚህ መሰባሰቦች ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ  የሚውሉ እንደሆነ አሳውቋል።

የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ገልጿል።

በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር #ግዴታ እንደተጣለ አሳውቋል።

በአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ከክልሉ አስተዳደር አቅም በላይ በመሆኑ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተቀመጡ ክልከላዎች አንዱ ደግሞ " መሰባሰብ " ነው። ከቀናት በኃላ በሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ ስነሥርዓቶቹ ተከናውነው እስኪያልቁ መሰባሰብ መፈቀዱ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
ኤርፖርት ...

በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው።

ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል።

ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና ሀገሩን ኢትዮጵያን ወዶ ወደዚህ የተመለሰ ፣ እዚህም በስራ ላይ የተሰማራ ነው።

የትላንት ጉዞውም የስራ ነበር።

ልጃቸው አስፈላጊውን ዶክመንት ሁሉ አሟልቶ የሚጠበቅበትን አድርጎ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሲደርስ አንድ ሰራተኛ  " የት ነው የምትሄደው ? " ይለዋል። ልጅም ቦታውን ይናገራል። " ስራህ ምንድነው ? " ሲል ሌላ ጥያቄ ያስከትላል " ስራዬን ሴልስ ማን ነው " ሲል ይመልስለታል።

ከዚህ በኃላ የኢሚግሬሽን ሰራተኛው ፓስፖርቱን ንጥቆ ወርውሮ ፣ ከዚህ ሂድ በማለት ያንገላታዋል ፤ ልጅም " ፓስፖርቴን መልስልኝ " ሲለው " ፓስፖርትህን አልሰጥም ሂድ ውጣ " በማለት እስከ ድብደባ ሊደርስ እንደነበር አባት በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።

በኃላም አባት ለኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ በተደረገው ማጣራት ከአንድ ሰዓት መጉላላት በኃላ ኢሚግሬሽን አልፎ ጉዞውን ማድረግ ችሏል።

" ህጋዊ ወረቀት ፓስፖርት ቪዛ ይዞ የሄደውን ሰው በዚህ ደረጃ ለምን ማንገላታት ያስፈልጋል ? ለምን ፓስፖርት መወርወር አስፈለገ ? ግልምጫ ማንጓጠጡስ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በአንዳንድ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ አሰራር ፣ እጅግ በጣም የብዙ ሰዎችን ልብ እየሰበረ መሆኑን ፤ ለጥቅም ተብሎ በሚሰራ ስራ እጅግ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ነብዩ ፤ እንዲህ ያለው አሳዛኝ እና ህገወጥ ተግባር በሁሉም ሰራተኞች ይፈፀማል ባይባልም በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ ተግባር የተቋሙን የቅን አገልጋዮችን ስም እንደሚያጎፍ እና ማረም እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተውበታል።

አቶ ነብዩ ሲራክ ፤ ለረጅም አመታት የህገ ወጥ ስደትን በመቃወምና በመከላከል ፣ በህገወጥ መንገድ ወጥተው ሌላ ሀገር እየተቸገሩ ስላሉ ዜጎች ጉዳይ ላይ ስራ እንዲሰራ ብዙ እየደከሙ ያሉ ሰው ናቸው።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሰራተኞች ስንት ዜጎችን ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበትም ይሁን የሚደውሉበት አጥተው ይሁን ?

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርፖርት ... በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው። ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል። ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና…
#ቦሌኤርፖርት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን እንደተገነዘበ ገልጿል።

አየር መንገዱ ከደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል መቆየቱን አመላክቷል።

በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል ብሏል።

በቦሌ ኤርፖርት ውስጥ በሚሰሩ የተለያዩ ህገወጥ ተግባራት እና ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶች በርካቶች ተማረው ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተለይ በኢሚግሬሽን ፣ በፍተሻ ቦታዎች ላይ በተጓዦች ላይ በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀሙ ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶችን ተከትሎ የአየር መንገዱ ስም በተደጋጋሚ ይነሳል።

በቅርቡም አንድ አባት ልጃቸውን ወደ ውጭ ለመሸኘት በተገኙበት ወቅት ልጃቸው በኤርፖርት ኢሚግሬሽን ሰራተኛ ማንገላታት፣ ማመናጨቅና ፓስፖርትም እስከመወርወር የደረሰ ተግባር መፈፀሙ ይታወሳል።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ ሰራተኞች ስንት ዜጎች ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበት አጥተው ይሁን ? የሚል ጥያቄ አስነትቷል።

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia