TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse #DrMariaVanKerkhove

የዓለም ጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ ካሉት አሳሳቢ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ሁሉ በብዛት እየተዛመተ ያለው #ዴልታ የተባለው በፍጥነት ተላላፊው ዝርያ መሆኑን አስታውቋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማሪያ ቫን ኼርኾቭ በሰጡት ቃል አልፋ ፥ ቤታ እና ጋማ የሚባሉት የቫይረሱ ዝርያዎች እያንዳንዳቸው ከአንድ ከመቶ ባነሰ ደረጃ እየተዛመቱ መሆኑን በብዛት እየተስፋፋ ያለው ዴልታው ዝርያ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ መረጃ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ በኢትዮጵያ አዲሱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዝርያ (ዴልታ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረው በዚህም በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት በቫይረሱ የሚያዙ ፣ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸው የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀው ፤ ለአዲሱ ቫይረስ መስፋፋት ቫይረሱን ለመከላከል ሚተገበሩ "የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀዛቀዝ ምክንያት አንዱ ነው" ብለዋል።

ህዝባዊ ጥንቃቄ የጎደላቸው መሰባሰቦች መብዛታቸውና የህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ክትባት አለመከተብ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

Credit : MoH/ENA & WHO/VOA

@tikvahethiopia
" ዴልታ እና ኦሚክሮን አደገኛ ማዕበል እያመጡ ነው " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የኮሮና ቫይረስ #ዴልታ እና #ኦሚክሮን ልውጥ ዝርያዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን በማበራከት አደገኛ ማዕበል እያመጣ ነው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።

ዶ/ር ቴድሮስ፥ ይህንን ያሉት በአሜሪካና በመላው አውሮፓ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ መሆኑን እየተገለፀ ባለበት በአሁን ሰዓት ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ ለወረርሽኙ መበራከት የሁለቱ ዝርያዎች " ጥምር " ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

አክለውም ሁኔታው " በተዳከሙ የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር እና የጤና ስርአቶችን ሊያናጋው ይችላል" ብለዋል።

ከክትባት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሃብታም ሀገራት 3ኛውን ዙር ክትባት ወይም ማጠናከሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የበለፀጉ አገራት መጠነ ሰፊ የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎች " ወረርሽኙን እንዲራዘም " ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ለዚህ ምክንያትም የክትባት አቅርቦቶችን ከድሃ ሀገራት በማዘዋወሩ ቫይረሱ " እንዲሰራጭ እና አዳዲስ ዝርያ እንዲፈጥር የበለጠ እድል ይሰጠዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

እ.ኤ.አ. በ2022 አጋማሽ 70 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ህዝብ ክትባት እንዲያገኝ የተጀመረው ዘመቻ እንዲሳካ ሁሉም ሰው መከተብን የአዲስ አመት ዕቅድ እንዲያደርገው ዶ/ር ቴድሮስ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia