TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 28 ክላሽንኮቭ፣ 459 ሽጉጦች እና በመቶ ሺህዎች የሚቁጠሩ የአሜሪካ ዶላር #በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል #ከሁለት_ክልሎች በረቀቀ መንገድ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ መሃል ከተማ የገባ 25 ታጣፊ እና 3 ባለ ሰደፍ በድምሩ 28 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳትም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በተመሳሳይ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቴል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ በኮሮላ የቤት ተሽከርካሪ ውስጥ 459 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና 2 የዝሆን ጥረስ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የካቲት 29 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤቴል ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ከ700 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia