TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ፖሊስ‼️

በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል የሚባለው ሰላማዊ ሰልፍ #ዕውቅና_የሌለው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለfbc በላከው መግለጫ፥ አንዳንድ ግለሰቦች #ቅዳሜ እና #እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰልፉ በከተማ አስተዳድሩም ሆነ በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑ ነው የተገለፀው።

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እና የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ሊካሄድ የታሰበው ሰልፍ ምንም ዓይነት እውቅና የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ አካላት የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር አስታውቋል።

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የተያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ስለሆነም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው በመሆኑ ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፎ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ ደንበኞቹ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ በማሰብ #እሁድ (ታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም) እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በተመረጡ ቅርንጫፎቹ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየውም የሚከተሉት ቅርንጫፎቹ ነገ ክፍት ናቸው።

1. አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ
2. ማህተም ጋንዲ ቅርንጫፍ
3. ሸገር ቅርንጫፍ
4. ስድስት ኪሎ ቅርንጫፍ
5. ሽሮሜዳ ቅርንጫፍ
6. ጥቁር አንበሳ ቅርንጫፍ
7. ፊንፊኔ ቅርንጫፍ
8. ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ
9. ጎተራ ቅርንጫፍ
10. አቃቂ ቅርንጫፍ
11. ባልቻ አባነፍሶ ቅርንጫፍ
12. ገዛኸኝ ይልማ ቅርንጫፍ
13. ገርጂ ቅርንጫፍ
14. ቦሌ መድሃኒዓለም ቅርንጫፍ
15. መስቀል ስኩዌር ቅርንጫፍ
16. ባምቢስ ቅርንጫፍ
17. ሰበታ ቅርንጫፍ
18. ዓለም ባንክ ቅርንጫፍ
19. ቤቴል ቅርንጫፍ
20. ዘነበ ወርቅ ቅርንጫፍ
21. ተስፋ ድርጅት ቅርንጫፍ

ምንጭ፦ epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: #እሁድ ጥዋት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት(ከWSU, AMU, WKU የተውጣጡ) በጉብሬ "ዘረኝነት እጠየፈሁ፤ ከተማዬን አፀዳለሁ!" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጠራው የፅዳት ዘመቻ ላይ ተሳትፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech
#ከጥላቻ_ንግግር_እንቆጠብ!!
የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ከልዩ ልዩ ጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አማካኝነት በግቢያችን ይካሄዳል።

#ፕሮግራሞች

#ቅዳሜ

☞ ብዙ ኪ.ሜ አቆራርጠው ለፍቅር እና ለሰላም ለሚመጡት የTIKVAH-ETH
ቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፣ ጥበባዊ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

#እሁድ

√የደም ልገሳ ፕሮግራም
√በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ስለጥላቻ ንግግር ፅሁፎችን ይቀርባሉ ፤ ልዩ ልዩ
ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
√በግቢያችን የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል

#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎርፍ እና የእሳት አደጋዎች #በአዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ #ቅዳሜና #እሁድ ሁለት የእሳት እንዲሁም ሶስት የጎርፍ አደጋዎች እንደተከሰቱ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በአደጋዎቹ ሳብያም የሰው ሂወት አለመጥፋቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ሲለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ ከታማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ በረንዳ ላይ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው ሳቢያም አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድቧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ሀያ ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት ከውድመት ታዲጌያለሁ ብሏል።

ሁለተኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በኮሊፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ስሙ አለም ባንክ አካባቢ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው 850 ሺ ብር የሚጠጋ ንብረት እንደጠፋና ስምንት ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን ተችላል፡፡

የጎርፍ አደጋዎቹ የደረሱት ደግሞ ሁለቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን አንደኛው በወረዳ አምስት ሶር አምባ ሆቴል አካባቢ ሲሆን ሌላኛው የጎርፍ አደጋ ደግሞ በወረዳ ሁለት ጣሊያን ሰፈር አካባቢ በመኖርያ ቤት የደረሰ የጎርፍ አደጋ ነው። በሁለቱም የጎርፍ አደጋዎች በግምት ሁለት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት የፊታችን እሁድ ይፋ ይደረጋል!

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት የፊታችን #እሁድ ነሐሴ 5፣ 2011 ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሔር እንደገለፁት የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እርማት በመጠናቀቁ የፊታችን እሁድ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ኤጀንሲው ይፋ ያደርጋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን 319,264 ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11፣2011 ድረስ መውሰዳቸውን ኃላፊው አስታውሰዋል፡፡

ተፈታኞች ውጤታቸውን ከፊታችን እሁድ ከ8፡00 ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራቸውን (Registration Number) በማስገባትና go የሚለውን አንዴ click በማድረግ መመልከት እንደሚችሉ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

#ሼር #share

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#KenenisaHotel

ትላንት ምሽት በገለፅንላችሁ መሰረት የአትሮኖስ ትሬዲንግ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ተድላ እና አቶ ተስፋዬ አየለ በዛሬው ዕለት በቅርቡ ተከራይተው እንደ አዲስ እየሰሩበት ከሚገኘው 'ከቀነኒሳ ሆቴል' ማነጅመት አባላት ጋር በመሆን የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው የሚችሉ 250 ወገኖችን መመገብ ጀምረዋል። ይህ ተግባር አሁን ያለው ችግር እስኪያበቃ ድረስ በየሳምንቱ #እሁድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Egypt #Ethiopia #Sudan

በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው ድርድር በሚቀጥለው #እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ነው።

ከታላቁ ህዳሴው ግድብ ድርድር ራሷን አግልላ የነበረችው #ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ላይ ያነሷቸውን ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : telegra.ph/ALAIN-12-29 (መረጃውን አዘጋጅቶ ያሰራጨው አል ዓይን ኒውስ ነው)

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ነገ እና እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት መታወቂያ ማሳደስ ትችላላችሁ "

#መታወቂያ_ለማሳደስ እየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም ህዳር 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ በየአካባቢው ባሉ የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ  ፅ/ቤቶች ይሰጣል።

ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየአቅራቢያቸው ባሉ ፅ/ቤቶች ተገኝተው መስተናገድ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ ይወስዳሉ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤ " እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ያ ማለት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሯቸውን ከሞላ ጎደል እነኚህን ኮርሶችን እንዲማሩ እናደርጋለን " ብለዋል።

" ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ አራት ወር ወስደን ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ መጫረሻ አካባቢ እነኚህን ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ እናደርጋለን " ሲሉ ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና ይመዘኑና ከመቶ ይያዝላቸዋል ፤ እሱን ወደ 30% ቀይረን ከማዕከል ተመሳሳይ ፈተና በግል ተቋማትም ዕጩ ለሆኖ ፍሬሽ ተማሪዎች በመንግስት ተቋማት ላሉ እጩ ፍሬሽ ማን ተማሪዎች ተመሳሳይ ፈተና እንሰጣለን። ይሄንን አድርገን 50 % እና ከዛ በላይ ያመጡትን ወደ መደበኛ ፌሽ ማን ፕሮግራም እንዲገቡ ይደረጋል። መደበኛ ፍሬሽማን ፕሮግራም ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ይሆናሉ " ብለዋል።

ተማሪዎች የሚማሩት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሳዩት ጉድለት ሲሆን ፦

- ቋንቋ፣
-  ሂሳብ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ (ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ) አስፈላጊ ከሆነ ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ ይዘት ይጨምሩላዋል ተብሏል።

በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ፦

- ጂዮግራፊ፣
- ታሪክ፣
- ቋንቋ እና ሂሳብ የሚማሩ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች እንደፍላጎታቸው ተጨማሪ ይዘት ሊጨምሩላቸው እንደሚችሉ ተገልጿል።

መንግስት ለ100 ሺህ ተማሪዎች የቅድመ ፍሬሽማን ኮርስ እድል የሚያማቻች ሲሆን ለዚህም ቁርጥ ያለ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ኮርስ ለሚወስዱ መንግስት ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦

" ወጪውን ችሎ ወደ መንግስት ተቋማት የሚሄደው የግል ውሳኔ ስለሆነ አነስተኛውን መቁረጫ ነጥብ ብቻ መንገር ነው የኛ ኃላፊነት።

በመንግስት የሚሄደውን መለየት ስላለብን በዝርዝር ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ፣ አካል ጉዳት ላለባቸው፣ ከታዳጊ ክልል ለመጡ፣ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች በዝርዝር ማስቀመጥ ስላለብን 100 ሺ ለመቀበል ስንት ተማሪ ምንያክል መቁረጫ ነጥብ አድርገን ነው የምናገኘው የሚለው የመንግስት ውሳኔ ነው የሚሆነው።

እኚህ መንግስት ወጪያቸውን ችሎ፣ ዶርም አስገብቶ፣ አብልቶ ፣ አስተኝቶ ሬሚዲያል ፕሮግራም ለሚሰጣቸው ነው።

በራስ ለሚወሰን አነስተኛውን ነው መንገር ያለብን በራስ ውሳኔ የሚለው የግድ ወደ ግል ተቋማት ይሄዳሉ ማለት አይደለም በመንግስት ተቋማትም ሊማሩ ይችላሉ ወጪያቸውን ሸፍነው " ብለዋል።

ይኸው እድል ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2014 ዓ/ም ፈተና ያለፉ #ተማሪዎችን_ምደባ እስከ #እሁድ ለማሳወቅ ፤ የቅድመ ፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበያ ነጥብ እስከ #ሰኞ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ተናግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት🚨

በአዲስ አበባ የጭነት ፣ ማሽነሪዎችን እና መሰል ተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ምን ይላል ?

- መመሪያው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ክልል በሚገቡና በከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ከተማዋን አቋርጠው በሚያልፉ የመጫን አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም ከ1ዐ ኩንታል በላይ የሆኑ የተለያዩ የፈሳሽና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 3፡00 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 10፡30 እስከ ምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫንም ሆነ ማራገፍ እንዲሁም በዋና ዋና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ መቆም የተከለከለ ነው፡፡

- በዚህ መመሪያ መሠረት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ እያለ የሰዓት ገደቡ ቢደርስበት በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ ከዋና መንገድ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ በመቆም የሰዓት ገደቡ እስኪያልፍ መጠበቅ አለበት።

- ማንኛውም የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በከተማ ውስጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በዚህ መመሪያ የተደነገገው የጊዜ ገደብ ቢደርስበት የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ ከመንገድ በመውጣት መቆም አለበት።

- በዚህ መመሪያ የተደነገገው የሰዓት ገደብ #እሁድ እና #የበዓል_ቀናት ላይ ተግባራዊ የማይደረግ በመሆኑ ማናቸውም የጭነት ተሸከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫን ሆነ ማራገፍ ይችላል፡፡

የሰዓት ገደብ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው ?

1. ሰሌዳቸው በሀገር መከላከያ ወይም በፖሊስ የተመዘገቡ የሀገር መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ስራዎችን የሚያከናወኑ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

2. በህግ መሠረት የድንገተኛ አደጋ ተሸከርካሪዎች ተብለው የተለዩ የድንገተኛ አደጋ የሚሰሩ ቀላልና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

3. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎች

አስተዳደራዊ ቅጣቱ ምን ይመስላል ?

🔵 በተከለከለ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ በመግባትና በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆመ ብር 10,000 (አስር ሺህ ) ይቀጣል፡፡

🔵 በዋና ዋና መንገድ ላይ የተንቀሳቀሰም ሆነ የጭነት መጫንና ማውረድ ተግባር የፈፀመ ወይም የኮንስትራክሽን ስራ የሰራ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ይቀጣል፡፡

🔵 በመመሪያው ላይ የተደነገገወን የሰዓት ገደብ በመተላለፍ ከተቀጣ በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋቱን በመድገም የተገኘ ማንኛውም ሰው ከላይ የተገለፀውን ቅጣት በእጥፍ ይከፍላል፡፡

NB. በተከለከለው ሰዓት በከተማው ውስጥ ሲንቀሳቃስ በመገኘቱ ቅጣት የተጣለበት አሸከርካሪ ሰዓቱ ሳይደርስ የቅጣት ወረቀት ይዞ በተከለከለው ሰዓት እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድለትም። የትራፊክ ተቆጣጣሪው ፍሰት በማያሰናክል ቦታ ላይ ተሸከርካሪው እንዲቆም በማድረግ ቅጣቱን እንዲከፍል ማድረግ አለበት፡፡

🗓 ይህ መመሪያ ከመስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#መውሊድ : 1499ኛው የታላቁ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በነገው ዕለት #እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia