TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበረው ውይይት የቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎቿ እንደተመለሰላትና ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ዝርዝር እና ሰፊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። @tikvahethiopia
#ቅዱስ_ሲኖዶስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ ፦

" ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው።

የነበረን ጥያቄ አጠቃላይ በመንግስት ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲሁም በሌሎች እዛ ባሉት ተገቢ ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ስለዚህ ጉዳይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። የተገኘውን ውጤትም አጠቃላይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን።

ዛሬ ይሄን አጭር መግለጫ ለመስጠት የወደድነው ምእመናኖቻችን ህዝባችን ስለሚጠብቅ ፤ ህዝባችን ምንም ከቆምንበት ዓላማ ወደኃላም ሆነ ወደፊት እንዳላልን ሁል ጊዜ የህገ ቤተክርስቲያን አቋም የፀና እንደሆነ፣ የቀኖና ቤተክርስቲያን የፀና እንደሆነ ይሄንን ለማረጋገጥ ነው።

ይሄ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ስለዚህ ምእመናንን ወገኖቻችን ስለምታደርጉ የፀሎት ፣ የምክር አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ በቤተክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን።

በፀሎት ትጉ፣ በምዕላ ትጉ ፤ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቷል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አንዳንድ የምሰማቸው እና የምናያቸው ነገሮች ስላሉ ነው ዛሬ ጠቅላላ መግለጫ ያላወጣነው።

ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ መግለጫ እንሰጣለን። "

@tikvahethiopia
#ቅዱስ_ሲኖዶስ

• የግጭት ተሳታፊዎች ካለፈው የጦርነት ውጤት ተማሩ።

• የተፈጠረውን ችግር #በጥበብና #በማስተዋል ፤ በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይታችሁ ፍቱ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ስብሰባ በማድረግ ወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረጽ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
  
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም መደፍረስና የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ውድ ሕይወት እያለፈ እና በርካታ የሀገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት እየወደመ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች " ብሏል።

" ሰላም ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፍጡራን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ  " ሰላም ከሌለ ቀድሶ ማቁረብ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ ማምረት፣ ተምሮ ማስተማር  ወልዶ ማሳደግ፣ ወጥቶ መግባት፣ አገር መምራትና ማስተዳደር አይቻልም ። በጥቅሉ ሰላም ሲጠፋ አብረው የሚጠፉ መልካም እሴቶቻችን ብዙ ናቸው፡፡ " ሲል አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቅርብ ጊዜ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ከሞት የተረፉት ወገኖቻችንም ለስደትና ለረሀብ የዳረገ ፣ ለአካልና ለእእምሮ ስብራት ያጋለጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ አድባራትና ገዳማትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ያፈረሰ እና መተኪያ የሌላቸውን ውድ ቅርሶቻችንን ያወደመ እጅግ በጣም አስከፊ ተግባር መሆኑን አስታውሷል።

በመሆኑም ፡-

በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ልንማጸን ይገባል ብሏል።

በሀገራችን በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና የእርስ በርስ ግጭት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንዱያደርጉ መልእክቱን አስተላልፏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ከአደራ ጋር ታስተላልፋለች ብሏል።

@tikvahethiopia