TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ #ጥንቃቄ 🚨

ይህ የተንጋደደና ለመውደቅ ጫፍ የደረሰ የመንገድ መብራት ምሰሶ ወድቆ በአስፓልቱ ላይ በሚተላለፍ ተሽከርካሪ እና በሰው ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት።

ይነሳ አልያም በአግባቡ ይጠገን።

ቦታው አዲስ አበባ ፣ ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን መሄጃ የትራፊክ መብራቱ ጋር ነው።

እንዲሁ ሊወድቅ እንዳለና እንደተንጋደደ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን የሚያነሳው እና የሚያስተካክለው አልመጣም።

ከከባዱ የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ወድቆ ጉዳት ሳይደርስ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው።

👉 ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
👉 ትራፊክ ማኔጅመንት

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ባለበት ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ " የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር " በሚል የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቆ ነበር። መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ-…
የሚተላለፉ ውሳኔዎች ?

(አዲስ አበባ)

ከዚህ ቀደም " ጥዋት እና ማታ ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት " በሚል የኮድ 2 ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ይህም ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር እንደሚገባ አንድ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ኃላፊ ለሚዲያ ይናገራሉ።

ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 መኪናዎች በፈረቀ እንዲንቀሳቀሱ የህግ ማዕቀፍ ሁሉ መዘጋጀቱን ነበር የተናገሩት።

በራሱ በባለስልጣን መ/ቤቱ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉት እኚሁ ግለሰብ ይህን በተናገሩ በሰዓታት ውስጥ መ/ቤቱ በማህበራዊ ሚዲያ ይወጣና " ይሄ ወደፊት በጥናት የሚሆን እንጂ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን አይደለም ፤ የእኔ አቋም አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥቶ ጉዳዩ በዛው አበቃ።

አሁን ደግሞ የትራንስፖርት ቢሮ " ትምህርት ቤት በመከፈቱ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለብዙሃን ትራንስፖርት (ህዝብ ማመላለሻ) ብቻ የተመረጡ መንገዶች አሉ ከእሁድ ጀምሮም ተግባራዊ ይደርጋል " የሚል መግለጫ ለሚዲያ ያሰራጫል።

መስመሮቹ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ያለባቸው ናቸው።

ሰዓታት ሳይቆይ ቢሮው " ከባለድርሻ አካላት ጋር እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ባለበት ይቀጥላል " የሚል ውሳኔ በማሳለፍ የቀድሞውንና ለህዝብ የተሰራጨውን ውሳኔ ቀሪ አድርጎታል።

ቀድሞውንስ እንዴት እንዲህ ያለው እጅግ በርካታ የከተማውን የትራንስፖርት ተገልጋይ የሚመለከት ውሳኔ ያለ ውይይት ሊተላለፍ ቻለ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል። የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡ ዝርዝር መረጃ ፦ - በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100…
አንድ ሰው ከኢትዮ ቴሌኮም የገዛውን አክሲዮን ድርሻ ማዘዋወር፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ቢፈልግ ይችላል ወይ ?

አትዮ ቴሌኮም አሁን የሚጀመረው የአክሲዮን ሺያጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህ ምዕራፍ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ብቻ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።

ዜጎች ድርሻቸውን ማዘዋወር ፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም የሚችሉት ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ምዕራፍ ብሎ ባስቀመጠው ሲሆን ይህም ገና በሂደት ላይ እንዳለ ተጠቅሷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌኮም በ " listing " ሂደት ላይ እንደሚገኝ እና ይህም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የጠቀሱ ሲሆን ይፋዊ ቀን ግን አልተቆረጠለትም።

የሁለተኛው ዙር አክሲዮን ሽያጭ ሲጀመር ደግሞ ዜጎች ድርሻ ማዘዋወር ፣ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ያስችላቸዋል።

እንዴት ነው አክሲዮን የሚገዛው ?

በቴሌብር ላይ ነው መግዛት የሚቻለው። ቴሌብር ላይ ሲገቡ አክሲዎን ለመግዛት የሚል አማራጭ ይገናኛል (ልክ ላውንች ሲደረግ) በዛ አማካኝነት ነው መግዛት የሚቻለው። በዛ ዝርዝር መረጃ ይገኛል፤ የደብንበኝነት ውልን ስለሚኖር አንብቦ መቀጠል ይችላል ከተስማሙ።

(እስካሁን ድረስ ቴሌብር ላይ ይህ የአክሲዎችን ሽያጭ አማራጭ አልመጣም ልክ ሲመጣ እናሳውቃችኃለን)

ፎርሙን በ48 ሰዓት ውስጥ ማስተካከል  ይቻላል ፤ በተመሳሳይ ክፍያም በ48 ሰዓት ውስጥ መከፈል አለበት። ከ48 ሰዓት በኃላ ፎርሙን ማስተካከል አይቻልም።

ፎርሙን መጀመሪያ በመደበኛ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት መሙላት የሚቻል ሲሆን መጨረሻ ላይ የሼር ባለቤት ለመሆን የናሽናል አይዲ (ፋይዳ) ያስፈልጋል።

ሼር ገዢ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ለሽያጭ ከቀረበው ሼር በላይ ከመጣ ከዛ ውስጥ እነማን የሼሩ ባለቤት ይሆናሉ የሚለውን ለመለየት የሚያስችል አሰራር ተቀምጧል። (በቀጣይ በዚህ ላይ መረጃ እናቀርባለን)

➡️ ሼር መግዛት ማመልከይ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና እዚሁ ሀገር ውስጥ በአካል ያለ ነው።

2016 ዓ/ም በወጣ የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ የካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

በመጀመሪያ ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ደግሞ 100 ሚሊዮን ሼር ነው። የአንድ ሼር ዋጋም 300 ብር ነው። ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል። ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
" ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይመስላል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን 4ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ትላንት እሁድ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

ጉባኤው ትኩረቱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት እና ስራ ከጀመረነት ጌዜ አንስቶ ምን ምን አብይ ጉዳዮችን አከናወነ ? ምን እንቅፋቶች ገጠሙት? ለእንቅፋቶቹስ ምን መፍትሄ ሰጠ የሚለውን ዋና የመወያያ አንጀዳ አድርጎ ነበር።

በዚሁ መድረክ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ  (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።

ዳንኤል (ዶ/ር) ፤ " ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ ? የሚለው ነው " ብለዋል።

መንግስትም ሲጠየቅ " ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ " ይላል።

ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ " እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው " ይላሉ።

ስለዚህ ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም " ብለዋል።

ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን አንስተዋል።

" ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የተዓማኒነት ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ችግር ባይሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም ነው " ያሉት።

" አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ " ከችግሩ ክብደት አንጻር ላይገርም ይችላል ነገር ግን ብዙ ነገሮች እየመጡ ሲያልፉ አይተናል አሁን ያለውም ችግር ከኢትዮጵያውያኖች አቅም በላይ ነው ብዬ አላስብም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine