TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ‼️

በሳዑዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ ግድያ ውስጥ “እጃቸው አለ” ያለቻቸው አሥራ ስምንት ሰዎች ወደ ድንበር ወደማይገድበው የአውሮፓ ሃገሮች የዝውውር ክልል ወደሆነው ሸንገን ቀጣና እንዳይገቡ ጀርመን #እገዳ መጣሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሃይኮ ማስ አስታወቁ።

በርሊን በግለሰቦቹ ላይ እገዳውን ከመጣሏ በፊት ከፈረንሣይ እና ከእንግሊዝ ጋር መመካከሯንም ጀርመናዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ገልፀዋል።

ብራስልስ ላይ ከተሰበሰሰው የአውሮፓ ኅብረት ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደ መግለጫ ላይ የተናገሩት ማስ “አሁን በራሱ በወንጀሉ ላይና አድራጎቱ እንዲፈፀም ማን እንዳዘዘ መለየትን ጨምሮ ከመልሶቹ ጥያቄዎቹ ይበዛሉ” ብለዋል።

የዣማል ኻሾግዢ ግድያ እንዴት እንደተፈፀመ የሚጠቁመው የተቀረፀ ድምፅ ምን እንደሆነ ሙሉ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ትናንት የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአድራጎቱ የአመፃና የክፋት መጠን መብዛት ምክንያት ድምፁን እራሱን ማዳመጥ እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

“የሥቃይ ድምፅ ነው፤ አስቀያሚ ድምፅ ነው፤ ሁከትና አመፃ የበዛበት፣ #የጭካሄና የክፋት አድራጎት ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA የአማርኛው አግልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብሄራዊ ቤተ መንግስት

የብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያቀው ከ300 በላይ #የስልክና #የኢንተርኔት መስመሮችን ጨምሮ ለግለሰቦች በሚውሉ መስተንግዶዎች ምክንያት በየዓመቱ #ከ11_ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱ ተገለፀ።

በአሰራር ክፍተት #ሲመዘበሩ የነበረ በርካታ ሚሊየን ብሮች ግምት ያላቸው ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉንም የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር አስታውቋል።።

በችግሮቹ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 31 ግለሰቦች ላይ #እገዳ የተጣለ ሲሆን፥ ቤተ መንግስቱ አሰራሩን በአዲስ መልክ በማደራጀት ክፍተቶቹን የማስተካከል ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በስሩ ከአስር በላይ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ቤተ መንግስቶችን የሚያስተዳድረው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር በዋነኝነት ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፈጽማል።

ከቤተ መንግስት ጋር ተያይዞ የሚገኙ ቅርሶችን መጠበቅና መከባከብ፣ ትላልቅ መስተንግዶዎችን ማከናወን እና ቤተ መንግስቱ ገቢውን በማሳደግ ራሱን በተሻለ ደረጃ እንዲያስተዳደር የሚሉ ናቸው።

የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር መቀመጫ የሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀላፊነት ሲወጣ ቢቆይም ለረጅም ጊዜያት ከመመሪያና አሰራር ውጪ የሆኑ ተግባራት ሲፈጸሙበት መቆየቱን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል።

ባለፉት 9 ወራት በተሰራው የማጣራት ስራ ቤተ መንግስቱ በአስተዳደር ሂደት ውስጥ የሚያቀርባቸውን የመስተንግዶ አገልግሎቶች ለግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጸሚያነት  እንዲውል በማድረግ በየዓመቱ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሲደረግ ቆይቷል።

ከስልክ፣ ኢንተርኔትና ኢ ቪድዮ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያገቃቸው ከ300 በላይ አካውንቶች በስሙ በየዓመቱ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ሲከፈል መቆየቱም ተደርሶበታል።

እነዚህ በማሳያነት የተነሱት ችግሮችና የተመዘበረ የገንዘብ መጠን ለማሳያነት የቀረቡ እንጂ በገንዘብ ያልተተመነና በአገልግሎት የሚገለጹ ሌሎች ጉድለቶችም እንደነበሩ ማረጋገጥ ተችሏል።

የገንዘቡም መጠን ሆነ የአገልግሎቱ ጉድለት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፥ ይህም ወደ ገንዘብ ሲለወጥ በ100 ሚሊየን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ሲመዘበር ቆይቷል ማለት ነው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት ችግሮቹን ከመለየት ባለፈ ድርጊት ፈጻሚዎች የሚባለኩት በአመራር ላይ የነበሩና ከአመራር የተሰናበቱ 31 ግለሰቦችን ለይቶ አግዷቸዋል።

ድርጊቱን በማስቆም ለተጠያቂነቱ ኮሚቴ በማዋቀር የማጣራት ስራን እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

ሌላው በብሄራዊ ቤተ የግዢ ስርአት ውስጥ የነበሩ ክፍተቶች በርካታ ግዢዎች እየተፈጸሙ ለአገልግሎት ከማዋል ይልቅ በመመጋዘን የማከማቸት ችግር ይታይ ነበር።

የተገዛው እቃ በመከማቸቱ እየተበላሸ ሌሎች በተለይም የውጪ ግዢዎችን በተከታታይ እየፈጸሙ መጠን እየቀናነሱ ማስገባትም ሌላኛው ችግር ነበር።

የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መየሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት የንብረት አያያገዝ ችግሩም ሀብቶቹ እንዲባክኑ እየሆነ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆታቸውን ያስታወቀው የብሄራዊ ቤተ መንግስቱ አስተዳደር፥ አሁን ላይ ወደ መፍትሄው እርምጃ መግባቱንም አስታውቋል።

በሂደቱ ተጨማሪና የተሻሉ አሰራሮችን መዘርጋትና ወደ ተግባር ማስገባነት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት በቅርቡ ለህዝብ ክፈት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩም መሆኑን ሰምተናል።

ቤተ መንግስቱ ያሉትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀምና እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም በማደስ በአጭር ጊዜ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ፣ በተለይ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ #እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ከክልሎች ደግሞ 'ከጋምቤላ ክልል' ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba🏍

በአዲስ አበባ ባለሞተሮች ከራሳቸው ውጭ ሌላ ተደራቢ ሰው እንዳይጭኑ #እገዳ ተጣለባቸው።

ሞተር ሳይክልን በተመለከተ በትራንስፖርት ቢሮ በኩል አዲሱ ጥናት ተጠናቆ ይወርዳል ተብሏል።

ይህ ጥናት እስኪወርድ መጪው የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ ውጭ ሌላ ተደራቢ ተሳፋሪ እንዳያጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ መተላለፉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከነገ ሚያዝያ 7 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ መመሪያ መሰጠቱም ታውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ከቅጣት በኋላ ካላስተካከሉ የማሸግ እንዲሁም ከዚህ አለፍ ሲል ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል " - በአ/አ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተጋጆቻቸውን " የተራቆተ " ልብስ የሚያስለብሱ ከሆነ ከ50 ሺህ ብር እስከ #እገዳ የሚደርስ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ መዘጋጀቱ ታውቋል።

የረቂቁ ስያሜ ፦ " በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት የሚሠሩ ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣ ጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ደንብ " ይሰኛል።

የተዘጋጀው ፦ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ነው።

በተለይም እንደ #ሥጋ_ቤቶች ባሉ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በታየው የአስተናጋጆች " የተራቆተ አለባበስ "  ምክንያት ረቂቁ ተዘጋጅቷል።

ረቂቁ ምን ያላል ?

- ከመስተንግዶ ስነምግባር እና ከሀገሪቱ ባህል የወጣ አለባበስ ይከለክላል።

-  አስተናጋጆች ከባህል፣ ከጨዋነት ያፈነገጠ እና የተራቆተ አለባበስ እንዳይኖራቸው ይከለክላል።

- አስተናጋጆች #በሚታይ የሰውነት አካል ላይ ንቅሳት እንዳይኖራቸው ይከለክላል።

- #ወንዶች በምንም ተአምር ጆሮ ጌጥ አድርገው እንዳያስተናግዱ አይፈቀድም።

-  የተቋማቱ ሠራተኞች ከሸሚዝ በላይ የሚሆን የአንገት ጌጥ እንዲሁም የእጅ ጌጥ እንዳይጠቀሙ ይከለክላል።

- ከጌጣ ጌጥ ጋር ተያይዞ ለሴቶች ጆሮ ጌጥ ይፈቀዳል። ነገር ግን ወደታች ያልወረደ እዚያው ላይ ልጥፍ የሚል መሆን አለበት። በተለይ በጆሮ ዙሪያ ላይ የሚደረግ ጆሮ ጌጥ አይፈቀድም።

- በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ . . . ምንም ዓይነት ንቅሳትም ሆነ ሌላም በሥዕል ተጠቅሞ ማስተናገድ አይቻልም። ይሁንና ከንቅሳት ጋር በተያየዘ የሚነሱ የባህል ጉዳዮች የደንቡን መጽደቅ ተከትሎ በሚወጣ መመሪያ ይታያል።

- ከአለባበስ፣ በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ ከሚደረጉ የጌጣ ጌጦች አጠቃቀም በተጨማሪ የፀጉር አያያዝን እንዲሁም የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መጠንን ላይ ገደብ ተቀምጧል።

ክልከላው እነማንን ይመለከታል ?

ሁሉንም ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪዎችን ይመለከታል።

* ሆቴሎች፣
* ካፍቴሪያዎች፣
* ምሽት ቤቶች፣
* ማሳጅ ቤቶች፣
* ጂሞች
* የስቲም እና ሳውና አገልግሎት ሰጪዎች ክልከላው ከሚመለከታቸው ውስጥ ናቸው።

ቅጣትን በተመለከተ ረቂቅ ደንቡ ምን ይላል ?

ደንቡ ላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ የሚተላለፉ ፦

በ15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል።

በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ ያማያደርጉ ከሆነ የ50 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

ከቅጣት በኋላም ካላስተካከለ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል። ከዚህ አለፍ ሲልም ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል።

መቼ ተግባራዊ ይደረጋል ?

ደንቡ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ለአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia