TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል።

በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል።

#ለማስታወሻ - የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፦

- ከኢንተርናሽናል እና የማህበረሰብ  ትምህርት ቤቶች ውጭ ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይተገበራል።

- ግብረ ገብ ፣ አገር በቀል ዕውቀት ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናት እና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው ይሰጣሉ።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት ይሰጣል።

- ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይሰጡ የነበሩት ኬሚስትሪ ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ " ጄኔራል ሳይንስ " ተብለው ይሰጣሉ። ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤ ከ7ኛ ክፍል -12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል።

- ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ።

- 3ኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን #ተጨማሪ_ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል።

-  አጠቃላይ ፈተና በክልል ደረጃ 6ኛ ክፍል ላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል።

- የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች " ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን " የተባለ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው ይሰጣቸዋል።

- 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ቢዝነስ ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከእነዚህ የሙያ ትምህርቶች ውስጥ የመረጡትን ይወስዳሉ።

- የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍልን እንዲሁም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ 5 የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል ፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል።

መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ / ኢፕድ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia