TIKVAH-ETHIOPIA
" በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ። ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም ርእሰ አድባራት ወገዳማት…
#Update
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚከናወን ተገለፀ።
ቋሚ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ተፈፅሟል ባለው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንደሚካሄድ አመልክቷል።
" በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ተፈጽሞ በመገኘቱ አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲጠራ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።
በዚህም ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ለሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጥሪ እንዲተላለፍ፣ 2ኛ የመክፈቻ ጸሎቱ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በ10፡00 ሰዓት እንዲከናወን 3ኛ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲካሄድ ቋሚ ሲኖዶስ ወስናል።
በክልል ትግራይ ሚገኙ ብፁዓን አባቶች ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል በመነጠል የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት በሚል አቋቁመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ማከናወናቸው ፤ ሃምሌ 15 እና 16 /2015 ዓ.ም እንዲሁም ሐምሌ 23 ደግሞ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ከዚህም በተጨማሪ፤ ዛሬ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት በመቐለ ህዝባዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ፤ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳዩ #ምስሎች ከላይ ተያይዘዋል።
@tikvahethiopia

July 31, 2023