TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ 320 የትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ አውርደው አስረክበዋል። የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊትም ታጣቂዎች ያወረዷቸውን ትጥቆች ርክክብ አድርጓል። በዛሬው ዕለት 320 የትግራይ ተዋጊዎች ቀላል መሳሪያዎችን አውርደው በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ያስልጠና ማዕከል አቅንተዋል። …
#DDR

" ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " - የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር 

የመጀመሪያ ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝድ በማድረግ ወደ  ተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ በይፋዊ ስነስርዓት ተጀምሯል።

ዛሬ በተካሄደ ይፋዊ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያው ፤ " የዴሞብላይዜሽን አሰራር ሴት ተዋጊዎችን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና በአደረጃጀት ውስጥ ያሉ አመራሮችን በማስቀደም ይፈፀማል " ብለዋል።

በዴሞብላይዜሽን አሰራር በየቀኑ 320 ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመጀመሪያ ዙር 75 ሺህ ታጣቂዎች እንደሚስተናገዱ አክለዋል።

" ማንኛውም ትጥቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ መያዝ የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ይከለክላል ስለሆነም በትግራይ እየተፈፀመ ያለው የዴሞብላይዜሽን አፈፃፀም ህግና ስርዓት ተከትሎ የሚፈፀም ነው " ሱሉ ተናገረዋል።

ብ/ጄነራሉ ፤ " ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረይ ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " ብለዋል።

" ትጥቅ ማስረከብ ማለት ያለችን እንዲት ሀገር ከሚጋረጡባት የውጭ ስጋቶች መታደግ መሆኑን መገንዘብ ያሻል " ያሉት ጀነራሉ  " ትጥቅ የማስፈታት ተግባሩ የትግራይ እና በክልሉ ደንበር አከባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተፈፃሚ ይሆናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

የትግራይ የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ ሃላፊ ጀነራል ፍስሃ በበኩላቸው ፤ " ትጥቅ የመፍታቱ ተግባር እርምጃ ለትግራይና ለሀገር ሰላም የተከፈለ ውድ እና ሁሌ በታሪክ ድምቆ የሚታወስ ፍፃሜ ነው " ብለዋል።

ዛሬ ትጥቃቸው ያስረከቡ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ሲሆኑ ወደ ተዘጋጀላቸው የስልጠና ማእከላት ማምራታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ስነ-ስርዓቱ ከተከናወነበት ቦታ በላከው መረጃ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DDR " ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " - የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር  የመጀመሪያ ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝድ በማድረግ ወደ  ተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ በይፋዊ ስነስርዓት ተጀምሯል። ዛሬ…
#Update

" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን ሁሌም ምርጫችን ሰላም ነው " - ተመላሽ ታጣቂዎች 

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞብላይዜሽን  እና መልሶ ማቋቋምያ ስነ-ሰርዓት በትግራይ መቐለ በይፋ ተጀምሯል።

ቅዳሜ ህዳር 14/2017 ዓ.ም በይፋ በተከናወነው የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓተ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ተገኝተው ነበር።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በDDR የሚታቀፉ የትግራይን ጨምሮ በስድስት የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ  ታጣቂዎች በሁለት ዓመት ውስጥ ዴሞብላይዝ በማድረግ  ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ምን አሉ ?

ትጥቅ መፍታትና ዴሞብላይዜሽን (DDR)  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነቶች ዋነኛ እና ጎልቶ የሚጠቀስ ነጥብ ቢሆንም በሃብት እጦት ምክንያት መዘግየቱ ተናግረዋል።

በትግራይ ጦርነት የተሳተፉ 274,800 ታጣቂዎች በDDR ዴሞብላይዝ ሆነው በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ህዝብ ይቀላቀላሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፦
👉 በአንድኛ ዙር 75 ሺህ 
👉 በሁለተኛ 100 ሺህ
👉 በሦስታና ዙር 53 ሺህ 800 
👉 በአራተኛ ዙር 46 ሺህ እንደሆነ አብራርተዋል።

በተካሄደው እጅግ አሰቃቂ ደም አፋሳሽ ጦርነት " በርካታ ህይወት ተቀጥፈዋል ፣ አካል ጎድሏል የሀገር እና የህዝብ ሃብት ወድመዋል " ያሉት አቶ ተመስገን ይህ እንዳይደገም እንደ ሀገር እና ህዝብ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳን ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

DDR ቀድሞ መደረግ የነበረበት ቢሆንም፤ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ ነው የዘገየው ፤ የዘገየም ቢሆን ዛሬ መጀመሩ ለሰላም ያለው ትርጉም ትልቅ ነው ብለዋል።

ተፈናቃዮች ባልተለመለሱበት፣ የትግራይ ሉኣላዊ ግዛቶች ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ባሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ታጣቂዎች ተይዞ ባለበት ወቅት DDR መጀመሩ ከስጋት ወጪ ሆኖ እየተፈፀመ ባይሆንም ሁኔታዎች እየተስተካከሉ ይሄዳሉ ከሚል ተስፋ ድጋፋችን መስጠት እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል።

የDDR መተግበር የትግራይ ሰላም መቀጠል ከሀገር ሰላም መፅናት ተያይዞ መታየትና መፈፀም እንዳለበት የፌደራል መንግስት እና ለጋሾች ትኩረት አደርገው ደጋፋቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅብረዋል።
 
የተሰናባች ታጣቂዎች ተወካይ ነጋሽ  ገ/ዮሃንሰ ምን አሉ ?

" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ ስለሆነም የነበረው ችግር በጠረጴዛ ውይይት መፍታት ከተቻለ ትጥቅ አንግበን የምንኖርበት ፍላጎት ስለሌለን  በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን " ብለዋል።

ታጣቂዎች " የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ምርጫችን ሰላም ነው የተሟላ ሰላም እንዲሰፍን አሁንም ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ መሬት ያሉ ታጣቂዎች ለቀው እንዲወጡ ለፌደራል መንግስት እና ለአደራዳሪዎች እንጠይቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። 

" ለቀድሞ ታጣቂዎች ለማቋቋምያ የተመደበው በቂ ስላልሆነ ቀጣይ የሆነ ድጋፍ እንሻለን " በማለትም ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - DW

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ' ተቀምተናል ' የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው "  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል " ብለዋል።

" ' ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ' የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት " ተቀምተናል " የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

" ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል። 

" ' ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ' በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው " ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ " በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል " ብለዋብ።

" ጠላት " ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው " መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት " ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

" ' የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ' የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ' ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ DW

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል…
#Tigray

በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው የተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ በአዲስ አስተዳዳሪ ተተኩ።

ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ፤ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ በተባሉ አዲስ አስተዳዳሪ ነው የተተኩት።

አዲሱ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህዳር 18 / 2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ መተካታቸው ለማወቅ ተችላል።

በአቶ ሰለሞን መዓሾ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ የትግራይ ክልል ፓሊስ እያጣራሁት ነው ማለቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወጣት እንስቶችን በግፍ ከገደሉ ውስጥ አንዱ በእድሜ ልክ አስራት ሲቀጣ ፤ የተቀሩት ለፍርድ ተቀጥረዋል። የመቐለ የማእከላዊው ፍርድ ቤት ትላንት ባዋለው ችሎት ኣፀደ ታፈረ በተባለች እንስት ወጣት በተፈፀመ የግድያ ወንጀል በይን የሰጠ ሲሆን ዓድዋ ከተማ ላይ በተገደለችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።  ሟች ወጣት ኣፀደ ታፈረን በአሰቃቂ…
#Update

" ውሳኔው በሌሎች ሴቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡ የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " - አባት

በግፍ የተገደለችው የዓድዋዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ የፍርድ ሂደት ገዳዮች ላይ የሞት እና የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በማስተላልፈ እልባት አግኝቷል።

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ህዳር 23/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በተማሪ ማህሌት ግድያ የተጠረጠሩት ሁለት ግለሰቦች ወንጀለኝታቸውን አረጋግጦ ፍርድ ሰጥቷል።

አንደኛው ወንጀለኛ በሞት ሁለተኛው ደግሞ በፅኑ የዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ከተማ ታግታ ከወራት መሰወር በኋላ ተገድላ ተቀብራ ስለተገኘችው ወጣት ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ካለፈው ዓመት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ መረጃዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላም የሟች አባት አቶ ተኽላይ አጭር አስተያየት ተቀብሏል።

የሟች አባት አቶ ተኽላይ " የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንደ ቤተሰብ ትክክል እና የሚሳምን ፤ በሌሎች ሴቶች ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡት የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " ብለውታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ለመሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ' የቀድሞው ' ከተባሉ ክልሉን (ትግራይን) ማነው እያስተዳደረ ያለው ? ይህ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የቀረበ ጥያቄ ነው። አቶ አማኑኤል አሰፋ ይህን ጥያቄ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞው ፕዜዳንት " ብለው በመጥራታቸው ነው። " የፕሬዜዳንት ውክልና ሲነሳ ፕሬዜዳንቱ በሌለበት ማን እንደሚሰራ…
" የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 17/2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አማኒኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞ ፕሬዜዳንት " ሲሉ ጠርተዋቸው ነበር።

ህዳር 22/2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማና ዙሪያዋ ከሚገኘው ደቡባዊ ምስራቃዊ ዞን ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የተወያዩት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በመድረኩ ለአቶ አማኒኤል ንግግር በስሜትና ኃይለ ቃል በመጠቀም " እሳቸው ለሚገኙበት ቡድን " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?   

" ባለፈው ጊዜ አንድ ሃላፊ ነኝ ባይ በመንግስት ሚድያ ' ነባር / የቀድሞ ፕሬዜዳንት ' ሲል ሰምታቹሃል ? ተልካሻ ነው። የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል።

እነዚህ አንድ ቀን ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። መዋቅራቸው ስርቆት ላይ የተሰማራ ነው። አሁን የልዩነት ነጥቡ ፓለቲካ መሆኑ ቀርቷል። 

የኔ ሳምንት ይሁን ወር በዚህ ወንበር መቆየት ያን ያህል አያሳስበኝም ፤ ይህን አደገኛ ቡድን ግን የወንጅል ትስስር (Crime network ) ነው የሚመራው።

በሰሜን ምዕራብ ማእከላዊ ዞኖች ወርቅ ፣ መዳብ እና ሌላ ማዕድናት ያካተተ ዘረፋ የሚያካሄደው ይህን በወንጀል የተሳሰረ ቡድን ነው ፤ ስለሆነም ዞኖቹን ከሱ ቁጥጥር ውጪ እንዲወጡ ፍላጎት የለውም።

ቡድኑ ይህን የዘረፋ ባህሪ አሁን ያመጣው አዲስ ነገር አይደለም ፤ የቆየበት ነው ፤ ሃሜት አይደለም እየነገርኳችሁ ያለሁት ተደራጅቶ እየዘረፈ ነው ያለው።

በስንፍናችን ይሁን ድንገት ወደ ስርቆት ኔትወርክ ያልገባን ሰዎች አለን። ስለሆነም እነዚህን ያለ የሌለ ውሸት ፈጥሮ ስማችን በማጥፋትና በማጠልሸት ' ከጨዋታ ውጪ ማድረግ አለብን ' ብለው ነው በኛ ላይ የዘመቱት።

ስለዚህ ይህንን የቡድኑን ተግባር እንደ ፓለቲካ ሳይሆን እንደ ሌብነት ነው መቆጠር ያለበት፤ ስለሆነም ቡድኑ አንድ እሱን የመሰለ ሌባ አቀፎ ለመያዝ የመጣበት አከባቢ ሳይለይ አባሉ ያደርገዋል " ብለዋል። 


#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ የወሰደው እርምጃ ህዝቡን ወደአላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ ነው " - የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ 

የመቐለ ከተማ ም/ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰጠው የመቐለ ከንቲባ ሹመት ከመቃወም አልፎ " ህገ-መንግስት የጣሰ ተግባር " ብሎታል። 

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ህዳር 24/ 2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት አብላጫ ድምፅ የተሾሙ ከንቲባ በስራ ላይ እያሉ የምክር ቤት እና የህዝብ ሉአላውነት በመጣስ ፓሊስ ስራቸው እንዳይሰሩ አግዷል ብሏል።

" በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ህጋዊ ያልሆኑ ከንቲባ በአስተዳደሩ አንድ አዳራሽ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።

" በምክር ቤት በስርዓት የተሾሙ ከንቲባ ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ የመቐለ ፓሊስ ከህግ አገባብ ውጪ ፅህፈት ቤታቸው በማሸግ ህዝብ አገልግሎት እንዳይገኝ አስተጓጉለዋል " ሲል ከሷል።

" የፓሊስ ኢ-ህጋዊ ተግባር  አገልግሎት ያጣ ህዝብ ወዳልተፈለገ ሽብርና ቀውስ እንዲገባ አድርገዋል " ብሏል።

በተጨማሪ የቋም ኮሚቴው በመግለጫ ምን አለ ?

👉 " በህገ-መንግስት የተሰጠ ስልጣን በመቀማት አምባገነን ስርዓት ለመትከል የተፈፀመ ተግባር ነው ይህንን እንኮንናለን። የተፈፀመው አግባብነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲታረም ጥሪ እናቀርባለን። "

👉 " የመቐለ ፓሊስ አመራር በህገ-መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው የፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር በማስተካከል በምክር ቤት የተሾሙ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ሳይውል ሳያድር  ስራቸው እንዲሰሩ እና አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲያደርግ እንጠይቃለን "

👉 " የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመው የህግ ጥሰት በመገንዘብ ህግ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የመቐለ ከተማ ህዝብ ህገ-ወጥ ተግባሩ በመቃወም ከምክር ቤቱ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የምክር ቤቶች ሉአላዊ ስልጣን በመጣስ የወሰደው እርምጃ ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ መሆኑ በመገንዘብ በዚሁ በህገ-መንግስት ጥሰት የተሳተፉት አካላት በህግ እንዲጠይቃቸው ጥሪ እናቀርባለን "

... ብሏል።



በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሸሙት አዲሱ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ መደበኛ ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት አንደሚጀምሩ ታማኝ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ሰጥተውታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ጊዜያዊ አስታዳደሩ የወሰደው እርምጃ ህዝቡን ወደአላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ ነው " - የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ  የመቐለ ከተማ ም/ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰጠው የመቐለ ከንቲባ ሹመት ከመቃወም አልፎ " ህገ-መንግስት የጣሰ ተግባር " ብሎታል።  የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ህዳር 24/ 2017…
" በምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ነው ከፅህፈት ቤቱ ያወጣው " - በድብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት መግለጫ አውጥቷል።

ደርጅቱ በመግለጫው ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዜዳንት ውክልና አንስቶ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታውሷል።

' ቡድን ' ሲል የገለፀው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የጊዚያዊ አስተዳደር በመምራት ላይ የሚገኘውን ህወሓት " የህዝብ ውክልና የያዙ ምክር ቤቶች እውቅና በመንሳት እና ውሳኔዎቻቸው በመጣስ በማን አለበኝነት ምስለኔዎች በመሾም አስተዳደራዊ እና ህዝባዊ ስራዎች እያደናቀፍ ይገኛል " ሲል ከሷል።

የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ህገ-መንግስት ላይ የተቀመጠውን የህዝብ እና የመንግስት ከፍተኛ መገለጫ የሆነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመጣስ በህዝብ ላይ አምባገነንነት ለመጫን በሙሉ አቅሙ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብሏል።

" ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ከፅህፈት ቤቱ በማውጣት በራሱ ምስሌኔ የአስተዳደሩ ፅህፈት ቤት ለመቆጣጠር መክሮዋል " ሲል አክሏል።

" ህገ-ወጥ ሙከራው ከግለሰባዊ አምባገነንነት የሚነሳ ነው " ያለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ አባላቱ ትግላቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማስታውስ ፣ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ህጋዊ ተጠያቂነት ፣ ህግ እና ስርዓት እንዲያስከብሩ በማለት ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia   
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወጣቶቻችን😭   " በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል !! " - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች " ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል ፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ " የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። …
#ስደት🚨

" ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሰደዋል ፤ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል " - የትግራይ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ

🚨 " ያሉት ችግሮች ወጣቱን ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደትን እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲመለከት እያደረጉት ነው !  "

በትግራይ በተካሄደው አስከፊና እውዳሚ ጦርነት ምክንያት የወጣቶች ህገ-ወጥ ስደት እንግልትና ሞት በእጅጉ ተባብሶ መቀጠሉ ተነግሯል።

የፕሪቶሪያ ውል ተሟልቶ አለመፈፀሙ ፣ የመልሶ ግንባታ  ስራዎች አለመጀመራቸው ፣ ሰፊ የስራ እጦት መኖር ለህገ-ወጥ የወጣቶች ፍልሰት መባባስ ምክንያቶች ናቸው ተብለዋል።

ይህን የሰማነው የትግራይ የስፖርትና የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከለጋሽ ድርጅቶች በመተባበር " ህገ-ወጥ ስደት " በሚል ካዘጋጀው አንድ መድረክ ላይ ነው።

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የበርካታ ወጣቶች ህይወት እየነጠቀ ያለውን ህገ-ወጥ ስደት አስመልክቶ በ49 የክልሉ ወረዳዎች በተካሄደ ጥናት ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች መሰዳዳቸው ያሳያል።

ከ38 ሺህ ስደተኞች ከ6 ሺህ በላይ ባለፈው ዓመት በጉዞ እያሉ ለህልፈት ተዳርገዋል ፤ አካላቸው የጎደለ አሉ ፣ አድራሻቸው የጠፉም ብዙ ናቸው።

2017 ዓ.ም ከገባ ወዲህ ብቻ  ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ተሰደዋል ከነዚሁ ደግሞ 300 ገደማ ለህልፈት ተዳርገዋል።

አደጋው የክልሉ ከፍተኛ ስጋት ወደ መሆን ተሸጋግረዋል ሲል ቢሮው አሳውቋል።

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ፦
የኢኮኖሚ አውታሮች ወድመዋል ፣
የብድር አገልግሎት መስጠት እጅግ የደከመ ነው፣
ሰፊ የስራ እጦት አለ እነዚህን እና ሌሎች ችግሮች ወጣቱ ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደት እንደ ብቸኛ አማራጭ  እንዲመለከት አድርገውታል።

ይህ ከፍተኛ ችግር እንዲቀረፍ የፌደራል መንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፋቸው እንዲቸሩ የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ። ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት…
#Tigray

በመቐለ ማንኛውም ሰላማዊ ስልፍ እንዳይካሄደ ተከለከለ ፤ ክልከካው አስከ መቼ እንደሚቀጥል የተገለፀ ነገር የለም።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በመቐለ ከተማ ተደረግብኝ ላለው የከንቲባ መፈንቅለ ስልጣን " ሰላማዊ ስልፍ እንዳካሂድ ይፈቀድልኝ " ሲል በመቐለ የህወሓት ፅህፈት ቤት በኩል ህዳር 25/2017 ዓ.ም ለመቐለ ከተማ አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።

ሰልፉን እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:30 ለማድረግ ነበር የጠየቀው።

ድርጅቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሂድ በጠየቀበት ደብዳቤው ፤ " ህዳር 23/2017 ዓ.ም የተፈፀመው በመሳሪያ የተደገፈ የመቐለ ከተማ መደበኛ አስተዳደር  መፈንቅለ ስልጣን ለማውገዝ " ነው ብሏል።

በተጨማሪም ፥ " ለዘመናት በከፈልነው መስዋእት ያፀናነው መብታችን እና የመሰረትነው ምክር ቤት በአዲስ ገዢ ግለሰቦች አምባገነንነት ሲፈርስ አንታገስም " ሲል ገልጿል።

ደንረጽዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ቡድን "  ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ በተደጋጋሚ ከአባሎቻችን በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ፤ እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 አስከ ቀኑ 6:30 ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ ቅድመ ዝግጅት ስላጠናቀቅን ፍቃድ እንዲሰጠን እና የፀጥታ ጥበቃ እንዲደረግልን እንጠይቃለን " ሲል ነው በደብዳቤው የገለጸው።

ለመቐለ ህወሓት ፅህፈት ቤት ደብዳቤ ዛሬ አርብ ህዳር 27 /2017 ዓ.ም ምላሽ የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የከተማው ጥምር ኮሚቴ በሰጠው መምሪያ መሰረት በመቐለ ከተማ ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ #ተከልክለዋል ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia