TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ታገሰ ጫፎ ከሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ጋር ተወያዩ።

ትላንት ኢትዮጵያ (አ/አ) የገቡት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ጋር ተወያይተዋል።

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎና የአሜሪካ ኮንግረሰ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ በቀጠናዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ፦
- በህዳሴ ግድብ ፣
- በህግ ማስከበር ፣
- በሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት፣
- ከሱዳን ድንበር ማስከበር ሥራ ጋር ተያይዞ ያለበት ደረጃና እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የሙሌት ሥራ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኗን አብራርተዋል።

ሙሌቱ የተፋሰሱን ሃገራት ጥቅም በማይነካ መልኩ እንደሚፈፀምም ገልፀዋል፡፡

ከ "ህግ ማስከበር" ጋር ተያይዞ የተከሰቱ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል። የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በመደረግ ላይ ነው ብለዋቸዋል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለሴናተሩ ተናግረዋል፡፡

ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ምን አሉ ?

በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የተሰጠው ማብራሪያ በኢትዮጵያ ውሥጥ እየተደረገ ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለመረዳት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ሴናተር ጀምስ አረጋግጠዋል፡፡ #FDRE_HoPR

@tikvahethiopia
#ወላይታሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

• " ለጉልበት ሰራተኞች 4 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ #የት_እንደገባ ማረጋገጥ አልተቻለም " - የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2013 በጀት ዓመት የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርትን ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

በዚህ ግምገማ ምን ተባለ ?

- ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ግኝቱን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ባለፉት አራት ዓመታት ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት አስተያየት ውስጥ ያለፈ ተቋም እንደሆነና በትኩረት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝቧል።

- ዩኒቨርሲቲው ማስመለስ ከነበረበት የገንዘብ ምጣኔ 99.95% እንዳላስመለሰ እና የኦዲት ግኝት መስተካከል ከነበረበት 11 ጉልህ  የኦዲት ግኝቶች 1 ብቻ ምላሽ እንዳገኘ ኮሚቴው ገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲው አመራር የፋይናንስ ህግጋትን እና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ ሰፊ ክፍተት በመኖሩ በትኩረት መስራት አለበት ተብሏል።

- ዩኒቨርሲቲው ባልተሰጠው ስልጣን አዳዲስ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያዘጋጀ ክፍያ ሲፈፅም የነበረ ሲሆን #ለጉልበት_ሰራተኞች አራት (4) ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ የት እንደገባ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ኮሚቴው ገልጿል።

የኦዲት ግኝቶችን በተመለከተ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ምን አሉ ?

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የኦዲት ግኝት ማሻሻያ መርሃ-ግብሩን እስከ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም እንዲያቀርብ እና መርሃ-ግብሩም ፦
- ለገንዘብ ሚኒስቴር፣
- ለፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ለሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግልባጭ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ተቋሙ የኦዲት ግኝቶችን ትኩረት ሰጥቶ ተገቢውን የእርምት ዕርምጃዎችን እየወሰደ በየ 3 ወሩ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ማቅረብ አለበት ብለዋል።

አያይዘውም ገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የዩኒቨርሲቲው #አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችን ወስዶ ሪፖርቱን በ10 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር #በወንጀለኛ እና #በፍትሃብሄር ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጉዳዮች ካሉ መርምሮ ክስ መመስረት እንዳለበት አቶ ክርስቲያን ታደለ አስረድተዋል።

አቶ ክርስትያን የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኦዲት ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ተገቢውን የቁጥጥር ስራ እንዲሰራ እና የኦዲት ግኝቶች ዩኒቨርሲቲው የእቅድ አካል አድርጎ እንዲያካትታቸው ተገቢውን አመራር  እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከስልጣኑ ውጪ ባወጣቸው ደንቦች እና መመሪያዎች የሚያደርጋቸውን ክፍያዎች እንዲያቆም እና በቀጣይም በመንግስት የፋይናንስ ህግጋት እና መመሪያዎች ተንተርሶ ብቻ መስራት እንዳለበት፤ ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎችም ተመላሽ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

#FDRE_HoPR

@tikvahethiopia