TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ለማስቻል ነው።

በታክስ ማሻሻያው መሰረት (የቤት አውቶሞቢሎች) ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶ ሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከ3 ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ነው ያጠናቀቁት " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ አላማጣ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። ያለዕረፍት በተሰራ ሥራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች…
#Update

ከአላማጣ እስከ ቆቦ የሚገኙ አካባቢዎች ዳግም #የኤሌክትሪክ_ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙት ፦

- አላማጣ፣
- ኮረም፣
- ዋጃ፣
- ጥሙጋ እና ቆቦ ከተሞች ናቸው።

ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋውን የ66 ኬ.ቪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በአካባቢው ያሉ ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ኤክሳይዝታክስ

ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማሻሻይ ተደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎች ላይም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲቀንስ ያደርጋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተሰምቷል።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

- በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤

- ከ3000 ሲሲ ባላይ  ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤

- ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ ወልዱ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ " አሁን በጣም ትኩረት የምናደርገው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ነው። ነዳጅን ለማበረታታ አይደለም (የኤክሳይዝ ታክሱ መቀነሱን ማለታቸው ነው) ግን በጣም ከፍ ያለ ከሚሆን ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ስላሉት ሲወጣ ይታያል አሁን ያለውን ከፍተኛ ሁለት መቶ አርባ አካባቢ ያለው ወደ መቶ ሃያ አካባቢ ዝቅ እንዲል ፤ በየደረጃው እንደዛ እንዲስተካከል ነው። " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ አዋጁን ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ከፍተኛ የሆነውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በመቀነስ #የኤሌክትሪክ_ተሽከርካሪዎች እና የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ መሳይ ወልዱ ፤ " ታክሱን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በተለይ የሀገር ውስጥ ገጣጣሚዎችን በማበረታታት አቅርቦትን ስለሚጨምር ፍላጎትም ይመጣል። አቅርቦትም ስለሚመጣ ዋጋ ተመጣጣኝ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ፤ ይሄ ወደ ቀረጥና ታክስ ነፃ የሚደረጉ ሩጫ ሁሉ ይቀንሰዋል፤ ይሄ ከፍተኛ መሆኑ ለዛ አንዱ ማበረታቻ ስለሚሰጥ ፤ ዋጋውን ይቀንሰዋል  በተለይ የኦውቶሞቲቭ ኢንድስትሪው የሀገር ውስጡ የራሱን ሚና ይጫወታል በማሳደግ እየተረጋጋ ይሄዳል የሚል ሃስብ ነው ያለው። " ሲሉ ገልፀዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተካተተው ሌላው ፤ 10 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸው የነበሩት የቪድዮ ካሜራ እና ቴሌቪዥን ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ተደርጓል።

አቶ መሳይ " በመጀመሪያው ማሻሻያ እራሱ ቴሌቪዥን ወደ 40 % ነበር የነበረው በጣም ተቀንሶ 10% ነው የተደረገው። የቪድዮ ካሜራም እንደዛው ፤ በጣም አስተያየት ተደርጓል የመጀመሪያው ላይ ግን የገቢ ክፍተት እንዳይፈጠር ቀስ በቀስ መውጣት ስላለብን ከ40 % ወደ 10 % ተደርጓል በተለይ ከስነ ጥበብ ከማሳደግ እና ከመደገፍ አንፃር ታይቶ ፣ ቴሌቪዥንም ህብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝበት የመንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የሚሰማበት ስለሆነ እሱ ላይም ቅናሽ ተደርጓል። በሂደት ስናየው አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ ያስፈልጋል የሚል ነው #ቴሌቪዥንና #ቪድዮ_ካሜራ በተለይ በዛ ውስጥ ባይካተቱ የሚል ሀሳብ ነው የቀረበው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ2012 ነበር ለ30 ዓመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ ያሻሻለችው ፤ አሁን ከ3 ዓመት በኃላ የሚደረገው ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር  እኩል እንድትራመድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የ " በላይነህ ክንዴ ግሩፕ "  በሲዳማ ክልል በሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክቦ በፍራፍሬ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ልማት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የእርሻ ዘርፍ አስፈጻሚ ዶ/ር አንተነህ አብዋ ለሪፖርተር ጋዜጣ  በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር አንተነህ አብዋ ምን አሉ ?

- በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክበረን 380 ሔክታር መሬት ላይ አትክልት ከማልማት አስቀድሞ የበጋ ስንዴ እያለማን እንገኛለን ፤ ምርታችንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብም አቅደናል።

- በሔክታር ከ30 እስከ 50 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውል ስንዴ ለማልማትና ከዚህም በጥቂቱ ከ11,400 በላይ ኩንታል ስንዴ ለመሰብስብ ታቅዷል። ለዚህም ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ለዘር ተጠቅመናል።

- ለስንዴና ማዳበሪያ ግዥ ከ300 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርገናል። 400 ኩንታል ኤንቲኤስ፣ እንዲሁም 400 ኩንታል ዩሪያ መሬቱን ለማሰናዳት ማዳበሪያ ተጠቅመናል።

- የእርሻ ልማቱን ለማከናወን በአጠቃላይ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፤ ከ20 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲሁም ወደ እርሻው የሚፈሰውን የወንዝ ውኃ ለመቆጣጠር 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግድብ ተገንብቷል።

-  የአባያ ሐይቅና የብላቴ ወንዝን ለእርሻው በዋነኛነት እንጠቀማለን፤ ለዚህም ዘመናዊ ፓምፖችን ለመጠቀም ተሰናድተናል።

- በአካባቢው የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ከአባያ ሐይቅ እስከ እርሻው መዳረሻ ድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በፓምፕ ስቦ ለማምጣት መሠረተ ልማት ተዘርግቷል።

- የበጋ ስንዴ ማልማቱ ሲጠናቀቅ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማቱ ይቀጥላል ፤ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓዬ ለማልማት የችግኝ ግዥ ተፈጽሞ ለመትከል ዝግጅት ላይ ነን።

- መሬቱን ከተረከብን 4 ወራት ብቻ  ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ ማልማቱንም ለማስቀጠል ከ40 ሔክታር መሬት በላይ አቮካዶ ተተክሏል። በቀሪዎቹ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንዲሁም ፓፓዬ ለማልማት ታቅዷል። በዚህ መሬት ላይ ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማሰናዳት የችግኝ ማፍላት ሥራ እየተሰራ ነው። ለጊዜው ለ200 የአካባቢው ሠራተኞች፣ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም ቁጥር ወደ 500 ለማሳደግ ታቅዷል።

በሌላ በኩል ፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በአካባቢው ለምትገኘው #መራሬ_ከተማ #የውኃ እና #የኤሌክትሪክ_ኃይል ለመዘርጋት የኮንክሪትና የእንጨት ፖል ዝርጋታ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia