TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል። ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል። በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ…
#Update

የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና / CHAN AFRICA እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ብሄራዊ ቡድኑ #ከሞዛምቢክ#አልጄሪያ እና #ሊቢያ ጋር በአንድ ምድብ ነበር የተደለደለው። ከሞዛምቢክ 0 ለ 0 ሲለያይ በአልጄሪያ 1 ለ 0 ተሸንፎ ነበር።

በምድብ የመጨረሻው ጨዋታ #ከሊብያ ጋር የገጠመው ብሔራዊ ቡድናችን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከወዲሁ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ቡድኑ በውድድሩ ላይ በአጠቃላይ 4 ጎሎች ሲቆጠሩበት ማስቆጠር የቻለው አንድ ጎል ብቻ ነው።

በተመሳሳይ ምድብ ውስጥ የነበሩት አልጄሪያ እና ሞዛምቢክ ከምድቡ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና እየተካሄደ የሚገኘው በአልጄሪያ ነው።

ተጨማሪ : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x    

@tikvahethiopia