TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከስራ ቦታ እንደወጡ ያልተመለሱት አቶ ኢብራሂም በያን !

በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ፣ ቀበሌ 04 ነዋሪ እና የሐጂ መሐመድ ሪል ስቴት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢብራሂም በያን ሠይድ መጋቢት 29/2014 ከሥራ ቦታ እንደወጡ እስከአሁን አለመመለሳቸውን ፤ የት እንዳሉም እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

በወቅቱ አቶ ኢብራሂም ከሥራ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ የስልክ ግንኙነት እንደነበራቸው የገለፁት ቤተሰቦቻቸው ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ግን የስልክ ግንኙነቱ መቋረጡን፤ የስልክ ግንኙነቱ ሲቋረጥም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው #ጀርመን_አደባባይ አካባቢ እንደነበሩን አታውሰዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ትራፊክ ጽ/ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ጠይቀውም ምንም ፍንጭ ባለማግኘታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳመለከቱ የገለጹት የአቶ ኢብራሂም ወንድም አብዱልሀዲ በያን እና የቅርብ ቤተሰባቸው ሩቅያ ሀሰን በወቅቱ ጉዳዩን መዝግቦ መርማሪ በመመደብ ተከታትሎ እንደሚያሳውቋቸው ፖሊስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ቢሆንም ግን ከመጋቢት 29 ቀን 2014 እስከ ዛሬ ምንም አይነት መፍትሄ እንዳልተገኘ አስረድተዋል።

አቶ ኢብራሂም ለረጅም ጊዜያት በመጥፋታቸውና ያሉበት ቦታ ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አሁንም ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

የኢብራሂም ቤተሰቦች አቶ ኢብራሂምን ያየ ወይንም ያሉበትን ቦታ የሚያውቅ በስልክ 0911149306፣ 0911616199 ፣ 0911438549 ላይ በመደወል እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

@tikvahethiopia