TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ!

ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማና ደጋሰኝን ታዳጊ ከተማ መስከረም 28 እና ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ወደ ገቢያ ሊሰራጭ የነበረ 24 ሺ 8 መቶ ባለ መቶ የሀሰተኛ የብር ኖት በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዛሬ ገልጿል፡፡

ፖሊስ በድርጊቱ ተሳትፈዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ከማቻክል ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር አምሳል ሰውነት ከብር ኖት ቅያሬው ጋር ተያይዞ በወረዳው ውስጥ የሀሰተኛ የብር ኖት እየተሰራጨ ስለሆነ ህብረተሰቡ ግብይት በሚፈጽምበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

በጎንደር ከተማ ውስጥ ከ31,000 ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር መዋሉ የ3ኛ ዋና ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የተያዙት በከተማ አስተዳደሩ በማራኪ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኮሌጅ ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች በፀጥታ ሃይል በተደረገ ክትትል ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2013 ከጧቱ 2 ስዓት ላይ መያዙ ተገልጿል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ እየተከታተላቸው መሆኑ በማወቃቸው በመታተም ላይ የነበረ ፦
• 27 ሺህ ብር አዲሱ ባለ 200 የብር ኖት
• 4 ሺህ 600 ብር ነባሩ ባለ 100 የብር ኖቶችን በባጃጅ በመጫን ከወሰዱ በኃላ ውሃ ቦይ ላይ ጥለው አምልጠዋል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎችና ተባባሪዎቻቸውም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የሞባል ካርድ በመግዛት ፣ ምግብ ቤት በመጠቀም እንዲሁም የሱቅ ሸቀጣሸቀጦችን በመግዛት እያዘረዘሩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሃሰተኛ የብር ኖት ሲያጋጥም ተጠያቂ ከመሆን በፊት ለፓሊስ ሊጠቁም እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

በህገ ወጥ መንገድ እየተመረተ ያለው ሃሰተኛ የብር ኖቶች ከአዲሱ የብር ኖቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው እና በሁሉም የብር ኖቶች ዓይነቶች ሃሰተኛ የብር ኖቶች እየተሰሩ ወደ ገበያ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይታለል መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_አዲስ_አበባ😷

በየዕለቱ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ሞት ሪፖርት እየተደረገ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ለአብነትም ፦

- ዛሬ የካቲት 11 በሀገር አቀፍ ደረጃ ሪፖርት ከተደረገው የ12 ሰዎች ሞት ፤ 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የትላንት ሪፖርት የከተማው አስተዳደር ጤና ቢሮው አላሰራጨም።

- የካቲት 9 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 14 ሞት 12ቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የካቲት 8 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 15 ሞት 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

በየዕለቱ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። እጅግ በርካታ ሰዎችም በፅኑ ታመዋል ፤ በርካቶችም የመተንፈሻ መሳሪያ ማግኘት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ስቃይ እያጋጠማቸው/ህይወታቸውንም እያጡ ነው።

ውድ አባላት በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ሳትዘናጉ እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ እንድትጠብቁልን አደራ እንላለን።

#Purpose #TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

በአዲስ አበባ ከባእድ ነገሮች ጋር ተቀላቅሎ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከ3 ሺህ 300 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ፣ 480 ኩንታል በርበሬ፣ 1 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ለቂቤ መከለሻ የሚውል የአትክልት ቅቤና የፓልም ዘይት እንዲሁም 6 መቶ ኪሎ ግራም ማር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።

በአራት ክፍለ ከተሞች (በአዲስ ከተማ ፣ ቂርቆስ ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ እና ኮልፌ ቀራንዮ) ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሲያካሂድ በነበረው ክትትል በዚህ ህገወጥ ድርጊት ላይ የተሳተፉ በ24 ድርጅቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ተሳታፊ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገልጿል።

በቁጥጥሩ ወቅት ቅቤን ለመከለስ አገልግሎት የሚውሉ የአትክልት ቅቤ፤ ፓልም ዘይት እንዲሁም በርበሬ ለመከለስ የሚሆን ከደረጃ በታች የሆነ ለሰው ምግብነት የማይውል የበርበሬ ተረፈ ምርት፤ የሻገተ በርበሬ ተገኝቷል።

በተጨማሪም ቤቶቹ ለምግብ ማምረት ስራ ፍቃድ የሌላቸው እና ከፍተኛ የሆነ የንፅህና ጉድለት ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

ህብረተሰቡ በበዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ያለው ባለስልጣኑ አጠራጣሪ ነገር ሲገጥም በነፃ የስልክ መስመር 8482 ላይ በመደወል ጥቆማ ማድረስ ይቻላል ተብሏል።

ምንጭ ፦ ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚሞቱባት ዜጎቿ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ፣ የቫይረሱ ተጋላጮችም በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6,198 የላብራቶሪ ምርመራ 1,130 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ትላንት 1,492 ሰዎች አገግመዋል። አሁን ላይ 945 ሰዎች በፀና ታመዋል።

በአጠቃላይ 256,418 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ የታየዙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3,658 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 197,916 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ሺህ ተጠግቷል።

ትላንት 946 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 198,862 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6,156 የላብራቶሪ ምርመራ 1,024 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 30 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በአጠቃላይ 257,442 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ የታየዙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3,688 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው 54,890 ሰዎች ሲሆኑ 962 ሰዎች በፀና ታመዋል።

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከወዲሁ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፤ በበዓል ግብይት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናስታውሳችኃለን።

በየትኛውም ቦታ ስትንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ የእጃችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትዘነጉ።

የበሽታው ምልክት ያለባችሁ/እራሳችሁን የምትጠራጠሩ ደግሞ ከቤታችሁ ባለመውጣት ወይም እራሳችሁን በመለየት ለሌሎች ሞት ምክንያት ላለመሆን የተቻላችሁን ሁሉ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

ከወዲሁ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦
- በጄዳ ፣
- መዲና ፣
- ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በሳዑዲ አረቢያ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በሙሉ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱን የጥንቃቄ መልዕክት #በአፅንኦት እንድትወስዱ ፣ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ፤ ጥንቃቄም እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ🚨

በሰሜን ሸዋ ዞን ውጊያ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የወዳደቁ ያልፈነዱ ጥይቶችና ፈንጆች በህጻናት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።

ሆስፒታሉ የአካባቢው ማህበረሰብና አመራር ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል፥ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢ በውጊያ መሃል ያልፈነዱ ጥይቶች በእርሻ ቦታዎች ወድቀው እየተገኙ መሆኑን ጠቁመው ከትናንት በስተያ 4 ታዳጊ ወጣቶች ማሳ ውስጥ የወደቀ ጥይት ፈንድቶባቸው እግራቸውና እጃቸው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሁለቱ በደ/ብርሃን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ ሪፈር መባላቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዛሬ ከጀቦሃ አካባቢ አንድ የ13 ዓመት ልጅ መጫወቻ መስሎት የወደቀ ጥይት አንስቶ ሲቀጠቅጥ በተከሰተ ፍንዳታ 3 ጣቶቹ ተቆርጠው በሆስፒታሉ እየተረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው ላሉ ተጎጂዎችም አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ዶ/ር አስማረ ሳሙኤል፦

• ህወሓት መሽጎባቸው የነበሩ አካባቢዎችና የወዳደቁ መኪናዎች ላይ የተለዬ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
• ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ በእርሻ ቦታዎች አርሶ አደሩ በጥንቃቄ ምርቱን ሊሰበስብ ይገባል።
• በየአካባቢው ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ህብረተሰቡን ማንቃትና አካባቢውን መፈተሽ አለባቸው።
• ወላጆች ልጆቻቸው ማንኛውንም የወደቀ ነገር አንስተው እንዳይቀጠቅቱ ሊመክሩ ይገባል።
• በአካባቢው ላይ በየማሳው የድሽቃ፣የሞርተርኛ ሌሎችም ጥይቶች የወዳደቁ በመሆኑ በባለሙያዎች ለቀማ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 5,013 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,027 የላብራቶሪ ምርመራ 5,013 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

193 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ።

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው።

ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ በዚህም የ2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ በ8 ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል።

🌊 የትላንቱ አደጋ የደረሰው የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናዱ ነው። ቦታው ከዚህ ቀደም በስጋት ቀጠና ከተለዩት አንዱ ነው።

- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች የንብረት ጎዳትና መሠረት ልማቶች ላይ፤ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ፣ የወንዝ ድጋፍ ግንባታ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና ወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia