TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " - የቡሩንዲው ፕሬዜዳንት

ቡሩንዲ በሀገሯ ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳወቀች።

የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ቡሩንዲ ሀገራቸው ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በጋዜጠኞች ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከግብረሰዶም ጋር ታያይዞ " ሃያላኑ ሃገራት ለአፍሪካ ሀገራት እርዳታ እየለገሱ ለግብረሰዶማውያን መብት የመስጠት ግዴታን የሚያስቀምጡ ከሆኑ እርዳታቸውን እዛው መያዝ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግብረሰዶም በቡሩንዲ ወንጀል ነው ያሉት ፔሬዝዳንቱ ይህ ወንጀል እስከ ሁለት አመት እስር እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።

" በግሌ እንደዚህ አይነት ሰዎችን (ግብረሰዶሞችን) ቡሩንዲ ውስጥ ካየን ስታዲየም ውስጥ አስገብተን በድንጋይ መውገር አለብን ብዬ አስባለሁ፤ ይህንን ለሚያደርጉ ደግሞ ሃጢያት አይሆንም " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በአፍሪካ አህጉር ከ30 በላይ ሀገራት ይህን ድርጊት የማይቀበሉ እና ወንጀል መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማጣቀስ " አምላክ ግብረሰዶምን ይቃወማል " ብለው በሀገራቸው ድርጊቱን በፍፁም እንደማይቀበሉት አስረድተዋል።

የዚህ አይነት የድርጊት መብት እንዲከበር ከምዕራባውያን ሀገራት ግፊት የሚደረግበትን መንገድ አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ ይህንን የሚመርጡ ሰዎች ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄደው እነዚያን ልማዶች እንዲያደርጉ አስጠንቅቀው ድርጊቱ ከሀገሪቱ እና ከአህጉሪቱ ባህል እና እሴት ውጪ በመሆኑ በጭራሽ በሀገራቸው እንማይፈቀድ አስጠንቅቀዋል።

" ሰይጣንን የመረጡ እና የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " ሲሉም አክለዋል።

በግብረሰዶማዊነት ጉዳይ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተጠናከረ ህግ እያወጡ ሲሆን የጋና የፓርላማ አባላት ድርጊቱ በሶስት አመት እስራት የሚያስቀጣ ህግ እና የድርጊቱ ተከራካሪ ሆነው ዘመቻ የሚያደርጉ ሰዎችን እስከ 10 አመት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ህግ እያወጡ መሆኑ ተዘግቧል።

ኡጋንዳም ከእድሜ ይፍታህ እስራት እስከ #ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ጠንካራ ህግ ማውጣቷ የሚዘነጋ አይደለም።

Via @TikvahethMagazine