TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወይዘሮ_እህተ_በቀለ #ዮርዳኖስ_ወሮታው👏

" አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ " - ወይዘሮ እህተ በቀለ

ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያስችል ጉዳት አለባት።

ዮርዳኖስ በእናቷ ድጋፍ ዛሬ ትምህርቷን አጠናቃ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል #በማዕረግ ተመርቃለች፡፡

እናት አህተ ፤ " አራት ዓመት ሙሉ ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ አጠናቅቄያለሁ። አራት ዓመት ለእኔ እንደ አራት ቀን ነው። ምንም አልተሰማኝም ደስ ብሎኝ አልፏል" ብለዋል።

በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዋ የሚሰጣትን ትምህርት ክፍል ውስጥ አብረዋት ቁጭ ብለው እየጻፉላት እንዳስተማሯት እናት ለኢፕድ ተናግረዋል።

" ዮርዳኖስ የማንበብ ችሎታዋን እወድላታለሁ። ያነበበችውን አለመርሳቷንና አስተዋይነቷን እወድላታለሁ፤ ልጄ ትጉህ ናት " ሲሉ ገልጸዋል።

ዮርዳኖስ እስከ 12ኛ ክፍል በሞግዚት ድጋፍ የተማረች መሆኑን ጠቅሰው እንደምትችል መታየት አለበት ብዬ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ አብሬያት ዘልቀናል ብለዋል፡፡

አትችልም የተባለች ልጅ ለዚህ በመብቃቷ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቅሰው፤ የእርስዋ ብርታት እንደ ልጃቸው ቤት ለተዘጋባቸው ልጆች አርአያ የሚሆን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

መኖሪያ ቤታቸው ከዮኒቨርሲቲው ራቅ ያለ በመሆኑ ጠዋት 12 ሰዓት ተነስተው ለአራት ዓመታት ልጃቸውን ወደ ትምህር ገበታዋ በዊልቸር በማመላለስ ለምረቃ ያበቁት እናት ዛሬ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ታይተዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia