TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል። የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።  የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ…
#Update

ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በወረቀት እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ በ @tikvahuniversity በኩል ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

አቶ ረዲ ፤ በዘንድሮው ፈተና የኢኮኖሚክስ የትምህርት አይነት እንደማይኖር የገለፁ ሲሆን የመልቀቂያ ፈተናው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ይሰጣል ብለዋል።

በተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተም ለተነሳላቸው ጥያቄ ፥ "ሁኔታው ተጠንቶ ወደ ፊት አቅጣጫ ይቀመጣል" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
 
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።

የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

#MoE

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ?

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ #ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ #በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር።

የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ እንደሚሄድ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት መግለፃቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ አይዘነጋም።

#ምንጭ@tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)

#ድብዳቤው ፦ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia