መግለጫ ፦ መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ " አገራችን ኢትዮጵያን ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል " ብለዋል።
(የፓርቲዎቹ የጋራ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
(የፓርቲዎቹ የጋራ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያሉ አባቶች የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም በቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጾሳት ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎችም በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ጥሪ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል። በትግራይ ያሉ አባቶች ከማዕከል በመነጠል " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ…
#EOTC
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-
በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።
ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#ኢትዮጵያ #ግብጽ
ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የዓረብ ሪፐብሊክ ግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል።
መሪዎቹ ባደረጉት ምክክር የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ይህ የመሪዎቹ ቁርጠኝነት በቀጠናው ሰላም እና ደኅንነትን ለማስፈን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ሀገራቱ የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ፈተናዎች ለመሻገርም ያስችላል።
ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ምክክር እልባት ያላገኘውን የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተም በተከታዮቹ ሁለት ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል።
1) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን እና የአሠራር ደንቦችን በተመለከተ በግብፅ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል የሚካሄደውን ንግግር በፍጥነት ለማስጀመር እንዲሁም ንግግሩን በአራት ወራት ውስጥ አጠናቆ ከመግባባት ላይ ለመድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል።
2) ንግግሩ በሚካሄድበት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በ2015-2016 ዓ.ም የግድቡ የውኃ ሙሌት ወቅት ግብፅ እና ሱዳን ከወንዙ በሚያገኙት የውኃ አቅርቦት ላይ የጎላ ችግር እንዳያጋጥም ለማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
(ኢዜአ)

#አቢሲንያ_ባንክ
በማንኛውም ዓይነት ስልኮች ያለ ኢንተርኔት *815# በመደወል የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። አገልግሎቱን ለማስጀመር አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ።
#BankofAbyssinia #BankingService #BankinginEthiopia #SavingAccount #815 #EducationSaving #boamobile #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

የምሥራች!
የመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት (ዋይፋይ) አገልግሎታችን ላይ እስከ 31% የሚደርስ ቅናሽ ማድረጋችንን በደስታ እንገልጻለን!
ለመኖሪያ ቤትዎ መደበኛ ኢንተርኔት ካስፈለገዎ አሁኑኑ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላችን በመሄድ በወር ከ499 ብር ጀምሮ ካቀረብናቸው አማራጮች ውስጥ እንደፍላጎትዎ መርጠው የፈጣን ኢንተርኔት ተጠቃሚ ይሁኑ!
ከ10 ሜ.ቢ/ሰከንድ በላይ ለሚገዙ ደንበኞችም በሞባይል ስልካቸው ነጻ 5 ጊ.ባ ኢንተርኔት እና 400 ደቂቃ ጥሪ ስጦታ ተዘጋጅቷል።
ለነባር ደንበኞች የፍጥነት እና የዋጋ ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን ማስተካከያውን በአጭር መልዕክት የምናሳውቅ ይሆናል።
(ኢትዮ ቴሌኮም)

#EOTC የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :- በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን…
#UPDATE
" የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ ያሉ በትግራይ የሚገኙ አባቶች ለሃምሌ 9/11/2015 ዓ.ም በርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን ለሚያካሂደው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።
በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከየሃገረስብከቱ 12 ፤ ከካሳቴ ብርሃን መንበረ ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅ 5 ታዳሚያን ተሳታፊ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን እነዚሁ በካርድ የሚመርጡ ታዳሚያን ናቸው ፤ ለኤጲስ ቆጶሳት ከሚቀርቡት እጩዎች 10 ጳጳሳት ይመረጣሉ ተብላል።
የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ለመታደም በአድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስትያን በፀሎተ ሱባኤ እንደሚገኙ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክዋስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሃምሌ 6 /2015 ዓ.ም በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ኢ-ህጋዊና ኢ-ቀኖናዊ ነው ያለው የትግራዩ የጳጳሳት ምርጫ እንዲቆም የፌደራል መንግስትና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲተባበሩ መጠየቁ ይታወሳል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ማሳሰቡ የሚዘነጋ አይደለም።

" ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ አልተወሰነም ፤ ነገር ግን ፈተናው ይሰጣል " -የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ሳንወስድ ግቢ ለቃችሁ ውጡ ተብለናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ።
ኢንስቲትዩቱ በበኩሉ ለተቋሙ የሚሆን የመውጫ ፈተና ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው፤ ለተማሪዎቹም የመውጫ ፈተና ወደፊት ይሰጣል ብሏል።
የኢንስቲትዩቱ ዕጩ ተመራቂዎች "የመውጫ ፈተና ሳንወስድ ግቢ ለቃችሁ ውጡ መባላቸውን" ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
ዕጩ ተመራቂዎቹ ላለፉት አራት ዓመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉና የማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ እንዲሁም የመመረቂያ ፕሮጀክት የሠሩ መሆናቸውን የተመራቂዎቹ ተወካዮች ነግረውናል።
በዋናው ግቢ 500 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም 1,500 የሚሆኑ የሳተላይት ካምፓሶች ዕጩ ተመራቂዎች መኖራቸውን ተወካዮቹ ገልጸዋል።
የመውጫ ፈተና ሳንወስድ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ መባሉ ተገቢ አይደለም ያሉት ዕጩ ተመራቂዎቹ፤ ጥያቄያቸውን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረባቸውን ይገልጻሉ። ምንም እንኳን በቂ ምላሽ ባያገኙም።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መኩሪያ ንጋቱ፤ ተማሪዎቹ ጥያቄያቸውን ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጭምር ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል።
"ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ወደፊት ይወስዳሉ" ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ አለመወሰኑን ተናግረዋል።
"ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመውጫ ፈተና ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን" ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠው የሙያ ስልጠና በመሆኑ ያንን ታሳቢ ያደረገ የመውጫ ፈተና ነው የሚዘጋጅ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ተከታትለው የጨረሱ መሆኑን የሚያሳውቅ ደብዳቤ ከተቋሙ ሬጅስትራር እንደሰጣቸው ለማወቅ ችለናል።
በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር የሚለውን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

#Camon20_Series
ልዮነቶን ያስፉ Camon 20ን ይያዙ!
አዲስ የሆነው የቴክኖ ሞባይል ካሞን 20 ስልክ የማጂክ ስኪን ቴክኖሎጂን በልዮ ዲዛይን ውበትን ተላብሶ ለእርሷ ቀርቧል። ቴክኖሎጂ እና ፋሽንን ያጣመረው Camon 20 Series ለእይታ ማራኪ፣ ለአያያዝ አመቺ እና ለአጠቃቀም ቀላል መሆኑ ብቸኛ ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Camon20Series #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#ዲጂታል_ዕቁብ
በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው ዲጂታል ዕቁብ አስተማማኝ፣ ተደራሽ፤ ሰፊ አማራጮች ያሉትን ዕቁቦች ይዘንሎት ስንመጣ በታላቅ ደስታ ነው።
እርስዎም አሁኑኑ የዲጂታል ዕቁብ መተግበሪያን ይጫኑ።
https://onelink.to/pm8mtg
ለነገ ህልምዎ ዛሬውኑ ዕቁብ በዲጂታል ይጀምሩ!!
ለተጨማሪ መረጃ 6091 ላይ ይደውሉ።

Photo
#Update
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ግንቦት 2015 ዓ.ም ጉባኤው ባስተላለፈው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ውሳኔ መሰረት ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ/ም የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት የአስኬማ ጸሎት ሥነሥርዓት ከቀኑ 9 ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እንደሚፈፀም ተገልጿል።
በተጨማሪም እሑድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት በዓለ ሢመት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አንብሮተ እድ ይፈጸማል ተብሏል።
በዕለቱ በሚካሄደው ስነስርዓት ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ አባሳደሮች፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችንና ምእመናን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ዕጩ ምሩቃን ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የመውጫ ፈተና ከቀናት በፊት ለጤና ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዕጩ ምሩቃን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የመውጫ ፈተናው እስከ ሐምሌ 8 /2015 ድረስ መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የፈተናው ውጤት በአጭር ጊዜ…
#Update
በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ላለፉት አምስት ቀናት ሲሰጡት የቆየው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
ከ44 የመንግሥት እና ከ161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ዕጩ ተመራቂዎች ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየውን ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል።
ከ168 ሺህ በላይ ዕጩ ተመራቂዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ መባሉ ይታወሳል።
ምን ያህል ተማሪዎች በኦንላይን የተሰጠውን ፈተና እንደወሰዱ መንግሥት በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ከሐምሌ 08/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውጤት ይገለጻል መባሉ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል ፥ የመውጫ ፈተና ከሰጡ ተቋማት አንዱ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፈተናው ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን ገልጿል።
ተቋሙ በ41 ፕሮግራሞች ካስፈተናቸው 1604 ተፈታኞች ፡-
- በ13 ፕሮግራሞች 100%
- በ7 ፕሮግራሞች ከ90-99%
- በ11 ፕሮግራሞች ከ80-89% በአጠቃላይ በ31 ፕሮግራሞች 80% እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ 81% ተማሪዎቹ ማለፋቸውን በይፋ አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 1604 ተማሪዎች 1289 ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውንም ገልጿል።
በተጨማሪ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና (EXIT EXAM) ካስፈተናቸው 1450 ተማሪዎች መካከል 78.5% ተማሪዎችን በብቃት ማሳለፍ መቻሉን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ካስፈተነባቸው 43 ፕሮግራሞች መካከል፡-
👉 100% ያሳለፉት 11 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ90% በላይ ያሳለፉ 21 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ80% በላይ ያሳለፉ 27የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ70% በላይ ያሳለፉ 32 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች መሆናቸውን ገልጿል።
የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የመውጫ ፈተና ውጤት ማምሻውን ይፋ መሆኑን ገልጾ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን እንዳረጋገጠ አሳውቋል።
በዩኒቨርሲቲ ደረጃ 80.3% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተናውን እንዳለፉ ተቋሙ ገልጿል።
" በርካታ የትምህርት ክፍሎች 100% ማሳለፍ ችለዋል " ብሏል።
More : - @tikvahuniversity
@tikvahethiopia @tikvahuniversity