TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Amhara Region Report AMHARIC.pdf
#ሪፖርት

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በሕወሓት ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብትና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 21 - ነሃሴ 22 /2013 ዓ/ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት እስከ ነሃሴ 30/ 2013 ድረስ የተካሄደ ምርመራ ውጤት ሲሆን የምርመራ ቡድኑ 128 ቃለመጠይቆችን፣  ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሲቪልና የፀጥታ አካላት፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከተራድዖ ድርጅቶች ጨምሮ 21 የቡድን ውይይቶችን አድርጓል።  

በሪፖርቱ እንዳመላከተው ምርመራው ባተኮረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በተደረገው ጦርነት ቢያንስ የ184 ሲቪል ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በተለይ የሕወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር በገቡ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ሲቪል ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውንና ማቁሰላቸውን፣ ሰፊ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ሆን ብለው መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አረጋግጧል። 

እንዲሁም የሕወሓት ኃይሎች ወደ ከተሞች ከባድ መሳሪያዎችን መተኮሳቸውን፤ በሲቪል ሰዎች መኖሪያ ቤቶችና ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ምሽግ በመቆፈር እና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ሲቪል ዜጎችን በአፀፋ ለሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ማጋለጣቸውን፤ በዚህ የበርካታ ሲቪል ሰዎች ሞትና አካል ጉዳት እንዲከሰት እንዲሁም ንብረት እንዲወድም ምክንያት መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። 

በሌላ በኩል የመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት ታጣቂዎች ሲቪል ሰዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች ውስጥ ሆነው የሚፈፅሙበትን ጥቃት ለመከላከል እና ለማጥቃት ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀሙ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞትና አካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረት እንዲወድም ሆኗል።

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (UNOCHA) ወደ 40 የሚጠጉ ሰብአዊ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪኖች (ምግብን ጨምሮ) ከሰመራ ተነስተው ወደትግራይ ማቅናታቸውን አሳውቋል።

ይህ እኤአ ከጥቅምት 18 በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ያቀና የመጀመሪያው ኮንቮይ ነው።

ነዳጅ እና የህክምና ቁሳቁሶችን የያዙ የጭነት መኪናዎች ከባለስልጣናት ፈቃድ እስኪያገኙ ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

UNOCHA በትግራይ ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ ​​እየተባባሰ መምጣቱን ጠቁሞ፣ ወደ ክልሉ የሚደርሰው ሰብዓዊ ዕርዳታ መደበኛ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።

እኤአ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የተቋረጠው ወደ መቐለ ከተማ የሚደረገው በረራ ከትናንትና በስቲያ መጀመሩን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ አየር አገልግሎት (UNHAS) አስታውቋል።

በአማራ ክልል ደግሞ ከ500 የሚበልጡ የጤና ተቋማት በግጭቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል በዚህም በርካታ ሰዎች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉን UNOCHA አሳውቋል።

በአፋር እና በአማራ ክልሎች ለሚቀጥሉት 2 ወራት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናት ለማከም በቂ የስነ-ምግብ እና የመመገቢያ ቁሳቁሶች ወደ ሁለቱም ክልሎች መላካቸውን አመልክቷል።

UNOCHA የምግብ አጋሮች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በደሴና በኮምቦልቻ ከ450,000 በላይ ሰዎችን ለመርዳት የምግብ ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን ሪፖርት አድርጓል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

Afar Region | Conflict Situation

የአፋር ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህወሓት በክልሉ ላይ በፈፀመው ወረራ በ4 ዞኖች (21 ወረዳዎች) 377,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና በአሁን ሰዓት በክልሉ 1.3 ሚሊዮን ህዝብ ለችግር ተጋልጧል ሲል አሳውቋል።

- በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ376,502 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

- ከ205,178 በላይ ሰዎች ከአውሲራሱ፣ ከብላቲራሱ፣ ከፋንቲራሱ እና ከሃሪራሱ ዞኖች አዲስ ተፈናቃዮች ናቸው።

- ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ተፈናቃይ የተመዘገበው ከጭፍራ (42156)፣ አዳአር (33,696)፣ ዳዌ (30,000)፣ ሃዳሌላ (21,000)፣ ሳማሮቢ (18,000) እና ተላሌክ (23,288) ነው። (እኤአ በህዳር 2021)

- መፈናቀሉ አሁንም በአውሲራሱ፣ ቀብላቲራሱ፣ ፋንቲ ራሱ እና ሃሪራሱ ዞኖች እንደቀጠለ ነው።

- በአጠቃላይ በግጭት ምክንያት የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎች ውስጥ ወደ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ለችግር አጋልጧል።

(የአፋር የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል)

@tikvahethiopia
#ሪፖርት : Human Rights Watch !

ሂዩማን ራይትስ ዋች የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል #ጭና እና #ቆቦ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መግደላቸውን ይፋ አደረገ።

በሁለቱ ስፍራዎች ግድያው የተፈጸፀመው ከነሐሴ 25 - ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም. በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ ነው።

መጀመሪያ የህወሓት ኃይሎች ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ጭና ወደተባለችው መንደር በመግባት ከፌደራል ሠራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ቦታውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በነበሩ 5 ቀናት በ15 የተለያዩ ስፈራዎች 26 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል።

በተመሳሳይ በቆቦ ከተማ ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም በ4 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ 23 ሰዎችን እንደገደሉ የዓይን ምስክሮች ለሂዩማን ራይትስ ዋች ገልፀዋል።

ድርጅቱ 36 ሰዎች ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን 19ኙ ጭና እና ቆቦ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በአጠቃላይ 49 ሰለማዊ ሰዎችን ሲገድሉ ማየታቸውንና ከሟቾቹ የ44ቱን ሰዎች ስም ገልፀዋል፤ በተጨማሪም የሟቾቹን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ የስም ዝርዝር ማግኘቱን አመልክቷል።

የሂማን ራይትስ ዋች የቀውስና የግጭት ጉዳዮች ዳይሬክተር ላማ ፋኪህ ስለግድያዎቹ ሲናገሩ " የትግራይ ኃይሎች በጥበቃቸው ስር ያሉ ሰዎችን በመግደል ለሰው ህይወትና ለጦርነት ሕግጋት ጭካኔ የተሞላበት ግድየለሽነት አሳይተዋል" ብለዋል።

አክለው " እነዚህ በኢትዮጵያ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎች ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንደሚያስፍልግ ያመለክታሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ሙሉ ሪፖርት : www.hrw.org/news/2021/12/09/ethiopia-tigray-forces-summarily-execute-civilians

@tikvahethiopia
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
1.4 MB
#ሪፖርት

የህወሓት /TPLF/ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ጊዜያት ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ በሲቪሎች ላይ ግድያ እና የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ አካባቢዎች፤ ከጦር እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ወንጀሎችን ስለመፈጸማቸው የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መኖራቸውን አምነስቲ ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል " የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል ከተሞች የሚገኙ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን ሆነ ብለው ገድለዋል ፣ ሴቶች እና ታዳጊዎችን አስገድደው በቡድን ደፍረዋል፤ እንዲሁም የግል እና የሕዝብ ንብረት አውድመዋል " ብሏል።

የህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ያደረሱት ከነሐሴ 2013 ዓ.ም. አጋማሽ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ባሉት ጊዜያት ነው።

ታጣቂዎቹ በአካል ላይ ከሚደርሱት ጥቃቶች በተጨማሪ የግድያ ማስፈራሪያዎች፣ ብሔር ተኮር ስድቦች እና ማንቋሸሾች በተጠቂዎች ላይ ሲደርሱ ነበር።

ቆቦ ላይ ከታጣቂ ነዋሪዎች እና ከሚሊሻዎች የገጠማቸውን መገዳደር ለመበቀለ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ ሲወስዱ እንደነበር አምነስቲ ሪፖርት አድርጓል።

የህወሓት/TPLF/ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ በእንዚህ የአማራ ክልል አካባቢዎች ዓለም አቀፍ መሠረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ ሕጎችን አለማክበራቸውን ገልጿል።

(ሙሉ ሪፖርት በPDF ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#ሪፖርት

ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል (የፆታዊ ጥቃት) ፦

(ቢቢሲ)

ከሐምሌ ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጭና እና በዙሪያዋ እድሜያቸው 14 የሚሆኑ ሴት ታዳጊዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎች በርካታ ሴቶችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መድፈራቸውንና አስገድደው ምግብ እንዲያበስሉላቸው አድርገዋል።

ቃላቸውን የሰጡት 14 የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች በቡድን፤ አንዳንዶቹ ልጆቻቸው ፊት መደፈራቸውን ተናግረዋል።

አንዲት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እና 14 ዓመት ታዳጊ ከእናቷ ጋር በመኖሪያቸው ድር-ባሕር በህወሓት ታጣቂዎች መደፈሯን ተናግራለች።

ይህች ታዳጊ ፥ "ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መሳሪያ የያዙ ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታችን ሲመጡ ከእናቴ እና ከአያቴ ጋር ነበርኩ። አንደኛው የወታደር ልብስ ነው የለበሰው ሌላኛው ደግሞ የሲቪል ልብስ። ትግርኛ እና አማርኛ እየቀላቀሉ ነው የሚያወሩት። 'ቤተሰቦቻችን ተደፍረዋል አሁን እናንተን የምንደፍርበት ተራ ነው' አሉን። አንደኛው ከቤት ውጪ እኔን ደፈረኝ። ሌላኛው ደግሞ ቤት ውስጥ እናቴን ደፈረ። እናቴ አሁን ታማለች። . . . ምን እንደተፈጠረ አናወራም" ስትል ተናግራለች።

የ29 ዓመቷ ሰላም ለ15 ሰዓታት በዘለቀ ቆይታ እንዴት 4 የህወሓት ታጣቂዎች እየተፈራረቁ አስገድደው እንደደፈሯት ተናግራለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
Amnesty International & HRW .pdf
22.5 MB
#ሪፖርት

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ወቅት የፈፀሟቸው ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ወንጀሎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ሪፖርት ያቀረበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሂውማን ራይትስ ዎች ጋር በመተባበር ላለፉት 15 ወራት የሰራውን ሪፖርት ነው ይፋ ያደረገው።

ዛሬ ይፋ የሆነው ሪፖርት ፥" 'ከዚህ ምድር እናስወግዳችኋለን'፡ በሰብዓዊነት የሚፈጸም ወንጀል እና የዘር ማጽዳት በኢትዮጵያዋ ምዕራብ ትግራይ ዞን" የተሰኘ ነው።

ይህ ሪፖርት በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች ላይ ተፈፀሙ የተባሉ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፋት ይዳስሳል።

ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ የአማራ ኃይሎች እና ባለስልጣናት በምዕራብ ትግራይ ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ወንጀሎች ፈጽመዋል ብሏል ሪፖርቱ።

ሪፖርቱ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ምዕራብ ትግራይ የሚንቀሳቀሱት የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች "የዘር ማጽዳት እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን ገልጿል።

የዛሬው ሪፖርት በጦርነቱ የመጀመሪያ ጥቂት ወራት ውስጥ የተፈጸሙ ጥፋቶችን ጭምር የዳሰሰ ሲሆን የትግራይ ሚሊሻዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ ሲቪሎች በ ማይካድራ ከተማ አካባቢው ነዋሪ በሆኑ እና ለቀን ስራ በመጡ የአማራ ተወላጆች ላይ "የጦር ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን አስታውሷል።

በሌላ በኩል ሁለቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአካባቢው ያለውን አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለማስቆም በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ጠይቀዋል።

(ሙሉው 240 ገፅ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ICHREE.pdf
233.1 KB
#ሪፖርት

በኢትዮጵያ ጦርነት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ በተመድ የተቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች የባለሙያዎች ቡድን (ICHREE) 19ኝ ገፆች ያሉት የመጀመሪያ ግኝት ሪፖርት

@tikvahethiopia
FDRE Inter-Ministerial Taskforce .pdf
771.8 KB
#ሪፖርት

የኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል የወንጀል ምርመራ እና ክስ ዝግጅት ኮሚቴ በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረ ግጭት የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ወንጀሎችን በተመለከተ የተከናወኑ የወንጀል ምርመራ ስራዎች የመጀመሪያ ዙር ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል። ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ…
በጋምቤላ_ከተማ_በክልሉ_የጸጥታ_ኃይሎች፣_በኦነግ_ሸኔ_እና_የጋነግ_ታጣቂዎች_የተፈጸሙ_የሰብአዊ_መብቶች.pdf
235.3 KB
#ሪፖርት

ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል፣ ጋምቤላ ከተማ ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) በጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) መካከል የተደረገው ውጊያን ተከትሎ ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ/ም በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ታጣቂ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ የንብረት ጉዳት እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ነው።

ከሰኔ 20 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ምርመራ ያደረገው ኢሰመኮ ዛሬ ይፋ ያደረገው ባለ 13 ገጽ ሪፖርት ነው።

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
Report_of_the_Ethiopian_Human_Rights_Commission_EHRC_and_the_Office.PDF
1.6 MB
#EHRC #UN #ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ከሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም - መጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎችና ጉዳት ከደረሰባቸው ማኅበረሰቦች ጋር ባደረጉት ምክክር የተገኙ ግኝቶችን በተመለከተ ይፋ ያደረጉት ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ከላይ ባለፈው ፋይል ተያይዟል።

@tikvahethiopia
2023.pdf
3.9 MB
#ሪፖርት

የሀገራትን የረሃብ ደረጃ የሚለካው የረሀብ ኢንዴክስ (GHI) ሪፖርት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም #ኢትዮጵያ 26.2 በመቶ በማስመዝገብ ከ125 ሀገራት ከመጨረሻዎቹ 101ኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ በ2022 ለይ ከ121 ሀገራት ውስጥ በ27.6 በመቶ በማስመዝገብ 104ኛ ደረጃም ይዛ ነበር።

በ2023 ሪፖርት የረሃብ ልኬቱ ቀንሶ 26.2 በመቶ ተሰጥቷታል።

ሪፖርቱ በየዓመቱ ይፋ የሚደረግ ነው።

በዚህ ጥናት ላይ የሀገራትን ደረጃ ለመስጠት ከሚዳሰሱ ዋና ዋና መሰረታዊ የሚባሉ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ፤ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት የምግብ እጥረት ፣ ሞትና የምግብ አቅርቦት ዋነኞቹ ናቸው።

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነትና ሥጋቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱ ፦

- ከሕግ ውጭ ግድያ (በድሮን ጨምሮ) ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፤
- የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፤
- እገታ
- አስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየት
- የሀገር ውስጥ መፈናቀል ... ተዳሰዋል።

° በጸጥታ መደፍረስ፣
° ከመንግሥት አካላት ተገቢውን ምላሽና ትብብር በወቅቱ ባለማግኘት
° በሌሎች ምክንያቶች ምርመራቸውና ክትትላቸው የዘገዩና የተጓተቱ በርካታ ጉዳዮችን መኖራቸው ተገልጿል።

እነዚህን ጉዳዮች በመርመርና ክትትል በማድረግ በተገቢው ጊዜ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ የተላከለትን ዝርዝር ሪፖርት ከላይ አያይዟል፤ በጥሞና ያንብቡት።

ኢሰመኮ በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከዐውድ ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆም ይገባል ብሏል።

የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል።

#EHRC
#Ethiopia #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia