TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደመወዝ

° " ደመወዝ በአግባቡ #እየተከፈለን_አይደለም ፤ የሚመለከተዉ አካል ካላናገረን ማስተማር አንችልም " - የከምባ ወረዳ መምህራን

° " በየሶሻል ሚዲያ ' ደመወዝ አልተከፈለንም ' እያሉ ገጽታችንን የሚያበላሹትን በህግ እንጠይቃለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ

° " ያልተከፈላቸው መምህራን
#ስራ_ስለማቆማቸው መረጃ አለኝ " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር

ከሰሞኑ በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ መምህራን " ደሞዝ በአግባቡ እየተከፈለን አይደለም " በማለት ቅሬታቸዉን አሰምተዋል።

" ዞኑ ውስጥ ካሉት ሀያ ክላስተሮች ተለይተን ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ መምህራን ስራ ማቆማቸውንና የሚመለከተው አካል ካላናገራቸው ስራ እንደማይገቡ በመግለጽ ቅሬታቸዉን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የመምህራን ጉዳይ ሰምቶ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ማለትም ፥ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበርና የዞኑን ትምህርት መምሪያ አነጋግሯል።

የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ምን አሉ ?

አቶ አማኑኤል ፥ " በዞኑ በከምባ ወረዳ #ለመምህራን እየተከፈለ ያለው ደሞዝ የተቆራረጠና አግባብ ባልሆነ መልኩ እየተፈጸመ ነው " ብለዋል።

አክለውም ፤ " በክላስተር ተቆራርጦ ከመክፈሉ ባለፈ በአንድ ትምህርት ቤት እንኳን ለጥቂት መምህራን ተከፍሎ ለአብዛኛው ደግሞ አለመከፈሉ ያበሳጫቸው መምህራን ስራ አለመግባታቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ስለመዘጋታቸው መረጃ አለን " ብለዋል።

የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊው አቶ አብርሀም አምሳሉ ምን አሉ ?

አቶ አብርሀም ፤ " ያለኝ መረጃ ለመምህራን ደመወዝ በአግባቡ እየተከፈላቸው መሆኑን እና ስራም እየተሰራ መሆኑን ነው " ብለዋል።

" ይሁንና በየሶሻል ሚዲያው ላይ የአካባቢውን ገጽታ ለማጠልሸት በማሰብ ' ደመወዝ አልተከፈለንም ' እያሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት ወሬውን እያናፈሱት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" እነዚህ አካላት በህግ እየተጠየቁ ሲሆን ወደፊትም ይጠየቃሉ " ብለዋል።

ምን አልባት ያልተከፈላቸዉ መምህራን ካሉ የዲስፕሊን እና መሰል ችግር ያለባቸው ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ አክለዋል።

በተጨማሪም በአካባቢው ላይ ትምህርት መቋረጡን የሚመለከት መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ችግር ተከስቶ ከሆነ እንደሚስተካከል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia