#ምዕራብ_ጎንደር
በክልሉና በምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበረ ያላቸውን ሁለት ተጠርጣሪዎችን መያዙን የዞኑ ሰላምና ደህንነት ግንባታ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለኢዜአ እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው ያለውን የፀጥታ መዋቅር በማጥናት ጥቃት እንዲፈፀም ለማድረግ ተዘጋጅተው የነበሩ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ምዕራብ ጎንደር ዞን ለማምጣት በማለም ሲንቀሳቀሱ እንደነበረም ተናግረዋል።
በህብረተሰቡና በፀጥታ አካሉ ትብብር የተያዙት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸው ሌላ ተጠርጣሪ እንዳለ ግለሰቦቹ በሰጡት ጥቆማ መሰረትም ፍለጋ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ግለሰቦች በመተማ እየተንቀሳቀሱ ባለበት ወቅት በህብረተሰቡ ጥርጣሬና ጥቆማ በትናንትናው እለት መያዛቸውንም አብራርተዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን #መተማ_ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች ትገኛለች።
ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።
በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ።
በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽት ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።
የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።
መረጃ / ፎቶ፦ የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia