TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የካቲት12

#የካቲት_12 ቀን ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በጀነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዉያን የሚታሰቡበት ነዉ።

የዛሬ 85 ዓመት ግራዚያኒ የተባለዉ የጣሊያን ጀነራል ከሀገሩ ኢጣሊያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ዘንድ አንድ ልዑል መወለዱን አስመልክቶ ደስታዉን ለማክበር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በአሁኑ 6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በቀድሞዉ ገነተ ልሎል ቤተመንግሥት ሰበሰበ።

በዚህ ወቅት የፋሽሽት ኢጣሊያ ወረራ ያስቆጫቸዉ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከተሰበሰበዉ ሕዝብ መሀል ወጥተዉ ወደ ግራዚያኒ ቦንብ ወረወሩ።

በዚህም ግራዚያን እና በርካታ ባለስልጣናቱ ቆሰሉ። ይህ ያበሳጨዉ የፋሽስት ኢጣሊያ ጀነራል ግራዚያኒ ያለርህራሄ ኢትዮጵያዉያን እንዲጨፈጨፉ አዘዘ።

ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨረጨፉት በ1929 ዓ/ም የካቲት 12 ቀን ልክ የዛሬ 85 ዓመት ነበር።

ወጣት አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን ጨምሮ በሦስት ቀናት ብቻ 30 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በዕለቱ ተሰውተዋል።

የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሀውልት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ኪሎ አደባባይ ላይ ቆሟል። በሀውልቱ ሥር በየዓመቱ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የመታሰቢያ ስነስርዓት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው። የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት…
#Ethiopia

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ጸድቋል።

ስለ አዋጁ ...

➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ 

➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።

➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።

➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።

➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም  ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።

ስለ አዋጁ ምን ጥያቄ ተነሳ ?

አንድ የምክር ቤት አባል ፦

" የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉት በዓላት ለምን አልተካተተም ? ለምን ታስቦ ከሚውል ውስጥ ተካተተ ? ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች !! ታስቦ ይውላል እና ተከብሮ ይውላል የሚለው የተለያየ አጀንዳ አለው " የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር።

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበር እና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡

" ኢኮኖሚያችንስ ? " ሲሉ የጠየቁት ወ/ሮ ወርቀሰሙ " ሁል ጊዜ ስራ እየዘጋን ፤ በዓል እያከበርን መዋል በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ጫና አለ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ታስቦ የሚውል በተለያዩ ነገሮች ደምቆ የሚውል ሊሆን ይችላል በሚል ነው በታሳቢነት እንዲቀጥል የተደረገው " ሲሉ አስረድተዋል።

#ShegerFM #TikvahEthiopia #HoPR

@tikvahethiopia