TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምረቃ

በዛሬው ዕለት የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።

- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
- መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ በየተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሀ ግብሮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

@tikvahethiopia
#የመውጫፈተና #ምረቃ

➡️ " ትምህርታችን በአግባቡ ብንጨርስም ለ8 ወራት ትዘገያላችሁ ተብለናል " - ተማሪዎች

➡️ " ይህ ውሳኔ የመጣዉ #ከትምህርት_ሚኒስቴር በመሆኑ ምንም ማድረግ አልቻልንም " -  የኮሌጅ አመራሮች

➡️ " የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሰሞኑን በርካታ #የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከምረቃ እና ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቅሬታ መልዕክቶችን ልከዋል።

ቅሬታቸውን ከላኩት መካከል በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ ደሴ እና ሌሎች ከተማ የሚገኙ የኮሌጅ  ተማሪዎች ይገኙበታል።

ተማሪዎቹ " በ4 አመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ያለብንን ትምህርታችን በአግባቡ ጨርሰን ፤ ክሊራንስም ሆነ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ክፍያ ብንፈጽምም ድንገት ለ8 ወራት መቆየት አለባችሁ ተባልን " ሲሉ  ገልጸዋል ።

ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ ፦

° ከሌሎች ተመራቂ ተማሪዎች እኩል በሚባል ደረጃ ትምህርት እንደጀመሩ፤

° መወሰድ የሚጠበቅባቸው አስፈላጊውን ኮርስ ወስደው ማጠናቀቃቸውን፤

° የመዉጫ ፈተና የማዘጋጃ ቲቶሪያል መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና " የመዉጫ ፈተናዉን ልንወስድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩን የመመረቂያ ቀናችሁ ጊዜ በሚቀጥለዉ ዓመት ጥር ላይ ነው " በማለት የመውጫ ፈተናውን መውሰድ እንደማይጠቅመን እና የሀምሌ ወር ምረቃችን መሰረዙ ተነገረን ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ " ተመሳሳይ ባች ከሆኑ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እኛ በምን ተለይተን ነው ይሄ የተደረገው ? ለምን ሌላው ሊፈተን ሲዘጋጅ እኛ ግን ' ብትፈተኑም ጥቅም የለውም ቀጣይ ዓመት ጠብቁ ' ተባልን ? ይህ በፍጹም አግባብነት የለውም ፤ መፍትሄ እንሻለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከደረሱት ብዛት ያላቸው ቅሬታዎች በመነሳት ኮሌጆችን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

ከነዚህም ውስጥ አንዱ ተማሪዎቹ የሚጠበቅባቸዉን ኮርስና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን ማጠናቀቃቸዉን ልክ እንደሆነ ገልጿል።

ይሁንና የመመረቂያ ጊዜያቸዉ የተወሰነዉ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጣ አቅጣጫ መሆኑን አስረድቷል።

ኮሌጁ ፤ ተማሪዎቹ #የተፈተኑበት_ጊዜ ምንም እንኳን 2012 ዓ/ም መሆኑን በወቅቱ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ያገኙት 'የኦንላይን ዶክሜንት' ቢያሳይም በኋላ የመጣላቸዉ ኦሪጅናል ደግሞ 2013 ዓ/ም እንደሚል ገልጿል።

ይህም ደግሞ ተማሪዎቹን ወደኋላ እንደሚያቆያቸዉና ለሚቀጥሉት ወራት የተለያዩ ትሬኒጎችና የመዉጫ ፈተና መለማመጃዎች እየሰጡ ለማቆየት መታሰቡን አስረድቷል።

በሌላ በኩል ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ አንድ ደብዳቤ ተመልክተዋል።

ደብዳቤው ፦

በ2013 ዓ/ም ሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች ለሰኔ ወር 2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እንዲደረግላቸው የጠየቁ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳሉ ያስረዳል።

ነገር ግን የትምህርት ሥልጠና ፓሊሲው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት እንደሆነ እንደሚደነግግ ይገልጻል።

አንዳንድ ተቋማት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ መጠየቃቸውን በማንሳት ይህ የሚያስጠይቅ ነገር ስለሆነ ተቋማት ተማሪዎችን በአግባቡ በማብቃት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እንዲሰሩ አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ጠይቆ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia