This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .
የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።
አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።
ጉዞውን የጀመረው ፤ ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት (6) ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።
ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን (UAE) አቆራርጧል።
ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ ?
" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ #መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።
የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስጂድ ማየት ነበር።
ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት።
አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል።
አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው።
ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው። ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል።
ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ ፣ በፍተሻ ጣቢያ ፣ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል። አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ።
በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁ።
ምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ። ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል። "
Via BBC - Al Jazeera
@tikvahethiopia