TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል።

ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር።

ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው " ተቀባይነት የሚያሳጣ " አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

#ሒሳባቸው_የጎላ_ችግር_ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት አገልግሎት
- የፌዴራል ፖሊስ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ቦሌሆራ ዩኒቨርሲቲና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አስተያየት ለመስጠት አልቻልኩባቸውም ካላቸው ተቋማት መካከል ፦
- የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል፣
- አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣
- ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣
- የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣
- የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሉበት፡፡

ከ1 ዓመት እስከ 6 ዓመት ዕድሜ ያለውና ለመንግሥት ገቢ መደረግ የነበረበት 13.4 ቢሊዮን ብር ውዝፍ የጉምሩክ #ቀረጥ እና #ታክስ ዕዳ መኖሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 👉 124 ሚሊዮን ብር፣
• የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 👉 65 ሚሊዮን ብር፣
• የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን 👉 64 ሚሊዮን ብር፣
• የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ 👉 7.9 ሚሊዮን ብር፣
• የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 👉 5.6 ሚሊዮን ብር፣
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 4.8 ሚሊዮን ብር በድምሩ 307.5 ሚሊዮን ብር የተሟላ ወጪ ሳይቀርብ በወጪ መዝግበው የተገኙ መሥሪያ ቤቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ ከደንብ እና ከመመርያ ውጪ ያላግባብ ክፍያ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ፦

- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ 👉 30 ሚሊዮን ብር፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 👉 22 ሚሊዮን ብር፣
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 👉 11.8 ሚሊዮን ብር፣
- የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን 👉 7.6 ሚሊዮን ብር፣
- የቤተ መንግሥት አስተዳደር 👉 6.5 ሚሊዮን ብር፣
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 👉 6.1 ሚሊዮን ብር በድምሩ 134.2 ሚሊዮን ብር ተጠቃሽ ሲሆን ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት የግዥ አዋጅ ደንብና መመርያ ያልተከተሉ ግዥዎችን የፈጸሙ 82 ተቋማት በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ መሥሪያ ቤቶች የተገኘው የግዥን ሕግ የጣሰ ክፍያ 592.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

ተቋማቱ ፦
> ጉምሩክ ኮሚሽን፣
> ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
> ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
> የኢንፎርሜሽን መረብና ደኅንነት አገልግሎት፣
> የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካደሚ
> ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡

" በተከፋይ ሒሳብ " ተመዝግበው የተገኙ ነገር ግን ዝርዝር ማስረጃ ባለማቅረቡ የሒሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያልተቻለባቸው ያሉ ሲሆን። ከእነዚህ ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 👉 1 ቢሊዮን ብር፣
- የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 👉 583 ሚሊዮን ብር፣
- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 👉 131.8 ሚሊዮን ብርና ጉምሩክ ኮሚሽን 96.5 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል፡፡

#ከተደለደለላቸው_በጀት_በላይ_የተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶችም በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ፦
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 358.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዲላ ዩኒቨርሲቲ👉 125 ሚሊዮን ብር፣
• ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 👉 139.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 👉 166.7 ሚሊዮን ብር፣
• አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 👉 113 ሚሊዮን ብር ናቸው፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በ2014 የተፈቀደላቸውን በጀት መጠቀም ሲገባቸው ባለመጠቀማቸው የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ቢሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በጀት ሥራ ላይ ካላዋሉ መሥሪያ ቤቶች ፦
- የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር 👉 8.9 ቢሊዮን ብር፣
- የገንዘብ ሚኒስቴር 👉 6.3 ቢሊዮን ብር፣
- የጤና ሚኒስቴር 👉 3 ቢሊዮን ብር፣
- ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 👉 1.2 ቢሊዮን ብር፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 👉 1 ቢሊዮን ብር፣
- የትምህርት ሚኒስቴር 👉 915 ሚሊዮን ብር፣
- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 👉 599 ሚሊዮን ብር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-06-29

@tikvahethiopia
#ቀረጥ_ነጻ

ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

ይኸው መመሪያ " መመሪያ ቁጥር 1023/2017 " ይሰኛል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች ?

የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡

1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-

ሀ/ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ ወይም ለህብረሰሰቡ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ :

- የትምህርት ተቋማት፣
- የጤና ተቋማት፣
- የሕጻናት፤ የሴቶች፤ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች

ለ/ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች

2. ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደአገር እንዲገቡ የተፈቀደ እቃዎች።

3. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሰረት ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት መሳሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና አክሰሰሪዎች፡፡

4. በብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች፡፡

ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች ከማህበራዊ
ቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ #አይችሉም

ሀ/ ከ8 መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎች  እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ለ/ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ሐ/ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች።


በዚህ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ እቃዎች ማስረጃዎች ማቅረብ የግድ ይላል።

ምን አይነት ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው ?

1. እቃዎቹ በእርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የእርዳታ የምስክር ወረቀት።

2. የእቃዎቹን ዝርዝር እና ዋጋ የሚያሳይ ኢንቮይስ፣

3. እቃዎቹ ለተገለጸው አላማ የሚውሉ መሆኑን እንዲሁም ስለእቃዎቹ አጠቃቃም ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑ የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው ከመንግስት መስሪያ ቤት የተጻፈ የድጋፍ ድብዳቤ።

#TikvahEthiopia #MinistryofFiance

@tikvahethiopia