TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የህፃናት አድን ድርጅት / Save the Children / በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በተሰራ ስራ 1 ሺህ 231 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ገለፀ።

አሀዱ ሬድዮ ፤ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ / Save the Children /  የትግራይ ክልል አስተተባባሪ የሆኑትን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ 1 ሺህ 218 ት/ ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን  722ቱ የሚሆኑት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት አገልግሎት አልጀመሩም።

ተማሪዎች 3 ዓመት የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን ያነሱት አስተባባሪው አሁን ላይ ለ39 ሺህ መምህራን የ3 ወር  ደሞዝ መከፈሉን አሳውቀዋል።

ት/ቤቶችን ከስጋት ነጻ ለማድረግና የተማሪዎቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በተሰራው ስራ በ1 ሺ 544 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 231  #ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸውን  ጠቁመዋል።

ድርጅቱ የተሸከርካሪ እና ሌሎችም ድጋፎችን በማድረግ በጋራ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ለ40 ሺህ ተማሪዎች በ59 ትምህርት ቤቶች ላይ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስ ለአሐዱ ገልፀዋል።

#አሐዱ #SavetheChildren

@tikvahethiopia
የሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .

" ከ60 በመቶ በላይ ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ ስለመሻሻሉ ፍቃደኛ ነው " በሚል በጥናት ተረጋግጧል ቢባልም በሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ በኩል በጥልቀት በድጋሚ እንደሚታይ ተገልጿል።

በቅርቡ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት አከናወንኩት ባለው ጥናት ከትግራይ ክልል ውጪ 60 ከመቶ በላይ የሚሆነው ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል ፍቃደኛ መሆኑን አረጋግጫለው ብሏል።

ይህን የጥናት ውጤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ምን ያህል አጋዥ ነው ?

ኮሚሽኑ ፤ የማህበረሰብ ጥያቄዎች እና አስፈላጊ ጉዳዮችን በተመለከተ በ3 መንገዶች ማለትም ከታች ወደ ላይ፤ ከላይ ወደ ታች እንዲሁም ወደ ጎን መረጃ የማሰባሰብ ስራ እንደሚያከናውን አሳውቋል።

" ከ60 በመቶ በላይ ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ ስለመሻሻሉ ፍቃደኛ ነው " በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩቱ ሰራሁት ባለው ጥናት ቢያሳውቅም በስፋት እና በጥልቀት በሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ በድጋሜ እንደሚታይ ገልጿል።

ሳይንሳዊ ምርምሮችና ጥናቶች እየተጠኑ ለማህበረሰቡ ይፋ መደረጋቸው ጠቃሚ መሆናቸው የገለፀው ኮሚሽኑ ጥናቱን እንደ ግበዓት እንደሚጠቀምበት ገልጿል።

Credit : #አሐዱ

@tikvahethiopia
" ከነበረዉ የ ' ኢህአዲግ ' ስርአት የፀዳ አሰራር አለመኖሩ ከፍተኛ ችግር ሆኗል " - ዶ/ር ራሄል ባፌ

" የስርአት ለዉጥ አለመኖሩ ፓርቲዎች በሚገባ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል "  ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ራሄል ባፌ ገለፁ።

ዶ/ር ራሄል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በፓርቲዎችና መንግስት መካከል እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ያለዉ የፖለቲካ ስርአት ያልተለወጠ  መሆኑ አዳጋች አድርጎታል  ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ተሳትፎም ይሁን በፓርቲያቸዉ የዉስጥ ጉዳይ ለመነጋገር፤ አባላትን ለማፍራትና የደጋፊዎቻቸዉን ቁጥር ለመጨመር ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ለወከባና እስር በመዳረጋቸዉ የተነሳ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

ከነበረዉ የ " ኢህአዲግ " ስርአት የፀዳ አሰራር አለመኖሩ ከፍተኛ ችግር ሆኗል ሲሉ መናገራቸውን #አሐዱ ዘግቧል።

@tikvahethiopia