TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መልቀቂያ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቀዳቸው ከኃላፊነት ለመልቀቅ በመወሰን መልቀቂያ ማቅረባቸውን አሳወቁ። ብርቱካን ሚደቅሳ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት በጤና ችግር ምክንያት ነው። " ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም…
(ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ)

" የስራ ሀላፊነትን በፈቃድ ስለመልቀቅ !

በ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ስራዬን ስጀመር ተቋማችንን ተአማኒ እና ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ በማለም ነበር።

ባለፉት አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ።

ሆኖም ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ።

በሚቀረኝ ጊዜ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር የመፈፀም ሃላፊነቶችን የምወጣበት ይሆናል።

ባለፉት አራት አመት ከ6 ወራት የምርጫ ቦርድን የማስፈጸም አቅምን ለመጨመር፣ ተአማኒነቱን ለማሳደግ ከሌሎች የቦርዱ አመራር አባላትና ከቦርዱ ሰራተኞች ጋር በጋራ ለፍተናል፣ ውጤቱን የሚመለከታቸው አካላትና መራጮች የሚመዝኑት ቢሆንም፣ በእኔ በኩል የቦርዱን ተአማኒነት በማሻሻል ረገድ፣ በተቻለ አቅምም የፓለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴዎች ለማገዝ ባደረግነው ጥረት ስኬታማ ነን ብዬ አምናለሁ።

በዚህም ወቅት አብረውኝ የነበሩ የቦርድ አመራር አባላትን፣ የቦርዱን ሰራተኞች በተለይም የየቀኑ ስራዬ በንሸጣ (inspiration) የተሞላ እንዲሆን ያደረጉልኝ ታታሪ የቦርዱ ሴት ሰራተኞችን፣ የቦርዱ የረጅም አመት ሰራተኞች ሆነው ያፈሩትን ልምዳቸውን ለአዲስ ሰራተኞች በማካፈል ስራችንን ቀላል ላደረጉ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።

የፓለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችም ቦርዱን እንደ አስተዳዳሪ እና እንደተቆጣጣሪ ከማየት ይልቅ በጋራ እንደሚሰራ ቤተሰብ በመቁጠር የማያስደስታቸውን ውሳኔ በምንወስንበት ወቅትም ጭምር እምነታቸውን አልነሱንም። ለዚህም ለፓርቲዎች እና ለአመራሮቻቸው ከፍ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም ይህን ማህረሰቤን የማገልገል እድል አገኝ ዘንድ ቦርዱን በሰብሳቢነት ለመምራት በእጩነት ላቀረቡኝ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም እምነቱን ጥሎ ሀላፊነቱን ለሰጠኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

ከልብ ከመነጨ በጎ ምኞት ጋር !! "

@tikvahethiopia
#COOP

ካሰቡበት ቦታ ለመድረስ ሲሰናዱ፣ጉዞዎ ምቹ እንዲሆንልዎ የመኪና ነዳጅ መሙላት ሲፈልጉ፣ በኮፔይ ኢብር ይክፈሉ!

ቀላሉን ዘዴ በመምረጥ፣ አስደሳች ቀን ያሳልፉ!
መተግበሪያውን አውርደው ለመመዝገብ፡
https://rb.gy/mdtd3
" ከነበረዉ የ ' ኢህአዲግ ' ስርአት የፀዳ አሰራር አለመኖሩ ከፍተኛ ችግር ሆኗል " - ዶ/ር ራሄል ባፌ

" የስርአት ለዉጥ አለመኖሩ ፓርቲዎች በሚገባ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል "  ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ራሄል ባፌ ገለፁ።

ዶ/ር ራሄል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በፓርቲዎችና መንግስት መካከል እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ያለዉ የፖለቲካ ስርአት ያልተለወጠ  መሆኑ አዳጋች አድርጎታል  ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ተሳትፎም ይሁን በፓርቲያቸዉ የዉስጥ ጉዳይ ለመነጋገር፤ አባላትን ለማፍራትና የደጋፊዎቻቸዉን ቁጥር ለመጨመር ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ለወከባና እስር በመዳረጋቸዉ የተነሳ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

ከነበረዉ የ " ኢህአዲግ " ስርአት የፀዳ አሰራር አለመኖሩ ከፍተኛ ችግር ሆኗል ሲሉ መናገራቸውን #አሐዱ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና ልማት ማህበር ፤ ድጋፍ ይደረግለት ዘንድ ጥሪ አቀረበ።

ማህበሩ ለቲክቫህ በላከው ደብዳቤ ባለፉት ሶስት አመታት ከ300 በላይ በሆኑ ወረዳዎች የሚገኙ ከ330 ሺህ በላይ የቀድሞ ሰራዊር አባላት አጠቃላይ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸውን በማቀፍ እና በማሰባሰብ በልማትና ድጋፍ ልየ ልዩ ተግባራት ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ገልጿል።

" ይህ በሀገሩ ባይተዋር ተደርጎ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት በደረሰበት ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መገለል ምክንያት ከፍተኛ ችግሮች ውስጥ የሚገኝ የህብረተሰብ አካል ነው " ያለው ማህበሩ  ይህንን የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸውን ገፍቶ የነበረውን ሁኔታ በመለወጥ ሰራዊቱንና ቤተሰቦቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድቷል።

በኢኮኖሚ መስክ ጠንካራ የልማት ርብርብ ለማድረግ እንዲሁም አንገቱን ዝቅ አድርጎ የነበረውን የሀገር ባለውለታ ሠራዊት በልማቱ በሀገሩ ተሰማርቶ ለሚያከናነው ከፍተኛ አስተወፅኦ የልማት አጋር ለመሆን ድጋፍ እንዲደረግ ማህበሩ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

ድጋፉ በቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት የልማትእና የድጋፍ ማህበር ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000552221102 (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) በመጠቀም የሚደረግ ሲሆን ሁሉም ዜጋ የተቻለውን እንዳያደርግ ማህበሩ ጥሪውን አቅርቧል።

ዜጎች ለሚያደርጉት ድጋፍ ተጨማሪ ማብራሪያ በ 0921433163 እና 0911965296 በመደወል መጠይቅ ይቻሉ ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Audio
#ይደመጥ

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የ " መውጫ ፈተና " ን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል።

በዚህ ማብራሪያ ፦

- የፈተናውን አይነት

- የውጤት አገላለፅ

- የጤና ተማሪዎች ፈተና / የሙያቸው እና የመውጫው

- እንደው ተማሪዎች ፈተናውን ባያልፉ መቼ እና የት ? እስከ ስንት ጊዜ ድረስ ድጋሚ መውሰድ እንደሚችሉ

- የፈተናው ደህንነት

- የተማሪዎች ምረቃ / ውጤት ያላመጡ ምረቃ ላይ ይሳተፋሉ በሚለው ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አቋም ምን እንደሆነ
.
.
. ሌሎችንም ምላሽ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በዝርዝር ለመላው ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ለተማሪ ወላጆች፣ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስረድተዋል።

ፋይሉ 28.2 MB ነው።

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይደመጥ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የ " መውጫ ፈተና " ን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል። በዚህ ማብራሪያ ፦ - የፈተናውን አይነት - የውጤት አገላለፅ - የጤና ተማሪዎች ፈተና / የሙያቸው እና የመውጫው - እንደው ተማሪዎች ፈተናውን ባያልፉ መቼ እና የት ? እስከ ስንት ጊዜ ድረስ ድጋሚ መውሰድ እንደሚችሉ - የፈተናው…
#ExitExam

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ?

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ምን አሉ ?

- የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል።

- የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል።

- በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል።

- ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

- ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል።

- የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ።

- ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም።

- ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው።

- የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል።

- አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል።

- ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ።

- ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።

- ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው።

- የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም።

- የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገንዘብ ወደየት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ?

ከአፖሎ ዲጂታል አካውንትዎ ገንዘብ ወደ አቢሲንያ ባንክ ሂሳብዎ እንዲሁም ወደ ሌሎች የተለያዩ ባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ ለዛሬ ከአፖሎ ዲጂታል አካውንትዎ ወደ አቢሲንያ ባንክ ሂሳብዎ እንዴት ማስተላለፍ እንደሚችሉ የሚያሳየውን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #TransferToOthers #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ለፈጣሪ የመታዘዝ እና የጽኑ እምነት ምሳሌ ለሆነው ኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል ከወዲሁ እንኳን በሰላም አደረሰዎ እያልን እስከ 32% ቅናሽ ያደረግንበትን አስደሳች ልዩ የኢድ አል- አድሃ (አረፋ) የሞባይል ጥቅል አቅርበናል!

በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች ወይም *999#
የበዓሉን ጥቅል ይግዙ፤ ወዳጅ ዘመድዎን ይዘይሩ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
Preliminary_Report_by_CECOE_Referendum_rerun_in_the_Wolaita_zone.pdf
649.8 KB
#CECOE : የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጀቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) በወላይታ ዞን የተካሄደውን የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባና የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን አስመልክቶ የሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት ልኮልናል።

በዚሁ የመጀመሪያ ደረጀ ሪፖርት ላይ ከድምፅ አሰጣጹ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ ኹነቶች ተብለው የተዘረዘሩት ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ፤ በተከለከሉ ቦታዎች ላይ የተቋቋመ የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ያልተፈቀደላቸው ሰዎች በምርጫ ጣቢያዎች መገኘታቸው፣ የመራጮች ምዝገባ እና ድምፅ አሰጣት ሂደት የመቋረጥ ጉዳይ፣ የቁሳቁስ አለመሟላት የመሳሰሉት ይገኙበታል።

ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ።

@tikvahethiopia
#እንዳትደናገጡ

ነገ የሚከበረውን የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ማለዳ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia