TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FRANCE

በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ20,000 በልጧል። ባልፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 547 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ በፈረንሳይ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ155,000 የሚበልጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 37,409 ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#France #Ethiopia

ፈረንሳይ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ1 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ድጋፍ አደረገች።

ፈረንሳይ በኦሮሚያ ክልል በቦረና አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ሚሊዮን 76 ሺህ 687 ዩሮ ድጋፍ አድርጋለች።

እርዳታው በድርቁ ሳቢያ ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎችን ለመታደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የፈረንሳይ ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#France #Ethiopia

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ወዳጅነት ቡድን አባላት ጋር ተወያይተወል።

ውይይቱ ፍሬያማ ውይይት እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ሄኖክ ፥ ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ ይዞ ግጭቱን የጀመረው ህወሓት እንደሆነና በአማራ እና አፋር ክልሎች ባደረገው ወረራ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንደፈፀመ ገልፅዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ሃይሎች በመምራት የህወሓት ሃይሎችን እያሸነፉ እንደሆነ፤ መንግሥት የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደሚያረጋግጥና የተጀመረውን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነ አብራርተዋል።

ቨርዢኒ ዱቢ ሙለር ለፈረንሣይ ፓርላማ አባላት ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ለማድረግ እድል በመስጠታቸው አምባሳደሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#France #Ethiopia

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል፣ በሦስቱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አሳውቋን።

@tikvahethiopia
#France #Ethiopia

በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ በፈረንሳይ መንግስት የተለገሰ 6.7 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ዶዝ በኮቫክስ አማካኝነት መረከቧን በአዲስ አበባ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ዛሬ አሳውቋል።

ኤምባሲው፤ ኢትዮጵያን ከፈረንሳይ ለአፍሪካ በክትባት ልገሳ ቀዳሚ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ አድርጓታል ብሏል።

ይህ አቅርቦት ከዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ግሪክ፣ ጣሊያንና ስዊድን ጋር በዩኒሴፍ ድጋፍ 13 ሚሊዮን የክትባቶች ዓለም አቀፍ ልገሳ አካል መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ የፈረንሳይ ኤምባሲ ፥ " እንደ ቡድን አውሮፓ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ለውጥ ማምጣት እንችላለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #FRANCE

ፈረንሳይ በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ጥረቶችን እንዲሁም የታቀደውን ብሔራዊ ውይይት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንሳይ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ፍሬደሪክ ክላቪየርን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በቀጠናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያካሄደ ስላለው የሰላም ጥረት ለልዩ ልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህ ረገድ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት እና በህዝብ መካከል መግባባት ለመፍጠር ያለመ የብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን መቋቋሙን ጠቅሰዋል።

ከፍተኛ የሆኑ የፖለቲካ ሰዎች ከእስር መፈታታቸው የውይይት መድረኩን ስኬታማነት እንደሚያፋጥነው ገልፀዋል።

ምንም እንኳን መንግስት ወታደሮቹ ወደ ትግራይ እንዳይገቡ መከልከሉ የሰላሙን ጥረት እንደሚያጠናክር ቢገለፅም ህወሓት በአጎራባች ክልሎች ላይ እያደረሰ ያለው አዲስ ጥቃት የሚጠበቀውን የሰላም ጥረት እንዳይቀንስ ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው ሀገራቸው ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አሳውቀዋል።

ሀገራቸው ፤ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የታቀደውን ሁሉን አቀፍ ውይይት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#FRANCE

🗳 ማክሮን ፕሬዜዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ኢማኑኤል ማክሮን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ። ማክሮን ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

በፈረንሳይ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ቀኝ ዘመሙዋ ማሪን ለ ፐን ተፎካክረዋል።

በዛሬው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተቀናቃኛቸው ማሪን ሊ ፐንን በ58.2 % ለ 41.8 % በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን የFrance 24 ዘገባ ያስረዳል።

የማክሮንን ማሸነፍ ተከትሎ የሀገራት መሪዎች የ " እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት እያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም የደስታ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።

በሌላ በኩል ፤ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ፕሬዜዳንት ማክሮን በሚቃወሙ አካላት ተቃውሞ ተቀስቅሷል ፤ ለአብነት በፓሪስ በነበረ ተቃውሞ ማክሮንን ሊቃወሙ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአንድ ሰው ግድያ ፈረንሳይን በተቃውሞ እየናጣት ነው። በፈረንሳይ ሀገር ፓሪስ አቅራቢያ ባለፈው ማክሰኞ ዕለት አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፈረንሳይ ፖሊስ መገደሉን ከተትሎ ፈረንሳያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ። ናሄል ኤም የተሰኘው ታዳጊ በቅርብ ርቀት በፖሊስ ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን ግድያው " የትራፊክ መብራት ጥሷል " በሚል የተፈፀመ መሆኑ ተነግሯል። ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ፤…
#France

በአንድ የፖሊስ አባል በተገደለ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ ሀገራቸው በከፍተኛ ተቃውሞና አመፅ ውስጥ የምትገኘው የፈረሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የውጭ ሀገር ስብሰባቸውን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ በብራስልስ የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ እየታደሙ የነበረ ሲሆን በታዳጊው ግድያ ሀገሪቱ በተቃውሞ መናጧን ተከትሎ ስብሰባቸውን ጥለው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኃላ ከባለሥልጣኖቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።

ካሳለፏቸው ውሳኔዎች መካከልም ፤ አንዳንድ የሚከናወኑ ዝግጅቶች እንዲሰረዙ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ለዘረፋ የሚጠሩ ጥሪዎች ላይ ክትትል እንዲደርግ የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪ ፕሬዝዳንቱ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር አሁን ከተሰማሩት 40 ሺህ የፀጥታ አካላት ተጨማሪ እንደሚሰማሩ አሳውቀዋል። ወላጆች ልጆቸውን ከጎዳና ላይ አመፅ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ፕሬዜዳንት ማክሮን ፤ " በአንዳንድ ሰፈሮች የአንድ ጎረምሳ ሞት ተቀባይነት በሌለው መልኩ ለሌላ ነገር ውሏል " ሲሉ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በፈረንሳይ የአንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ አባል መገደሉን ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት በሀገሪቱ ብርቱ ተቃድሞ እና አመፅ እየተካሄደ ይገኛል። በተከሰተው አመፅ በተለያዩ ከተሞች በርካታ ተሽከርካሪዎች ጋይተዋል፣ ህንፃዎች ተቃጥለዋል፣ በፖሊስ እና በተቃውሞ አራማጆች ማካከል ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች ተጎድተዋል፤ በርካቶችም ታስረዋል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia #France

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገቡ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ ቢኤፍኤም ቲቪ

@tikvahethiopia