TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር 6 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሬሜዲያል ተማሪዎችን እንደማያስተናግዱ አሳወቀ።

በ2015 ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲያስተካክሉ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ፦
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ መሆኑን አሳውቋል።

Via MoE / @tikvahuniversity
#MoE

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም #አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ብሏል።

በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ያላለፉ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የሚያካሂዱት የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የሚመርጡት በዚህ ማስፈንጠሪያ (Link)
(https://exam.ethernet.edu.et)  ነው።

ስለሆነ ከጥር 08 እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በ " ቴሌ ብር " ብቻ በመክፈል መመዝገብ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል [email protected] በኩል ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የሚፈቱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚያካሂዱትና  እና የአገልግሎት ክፍያ የሚፈፅሙት በተቋማቸው በኩል መሆኑን ገልጾ አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ?

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ #ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ #በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር።

የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ እንደሚሄድ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት መግለፃቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ አይዘነጋም።

#ምንጭ@tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)

#ድብዳቤው ፦ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር : -

1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣

2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣

3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ መሰረት መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ ማዘጋጀቱን ጠቁሟል።

በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና እና የዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መቼ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የትምህርት ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ፥ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

#TikvahEthiopia

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተሰርዞ በድጋሚ ይሰጣል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ቀደም ብሎ ፈተናው ወጥቶ በወረቀት እትም እና በPDF መሰራጨቱንና ተማሪዎችም ሰርተው መግባታቸውን አመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ግን ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " ስላጋጠመው ፈተናው በድጋሜ  በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ብሏል።

ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ለፈተናው ተቀምጠው የነበሩ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተኑበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ተማሪዎች ምን አሉ ?

የጥዋቱም ይሁን የከሰዓቱ ፈተና ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ወጥቶ ተማሪዎች በበድን ሰርተውት እንደገቡ ገልጸዋል።

ሌላው ፈተናው ከብሉፕሪነቱ ጋር እንደማይጣጣም ፤ ትምህርቱንም የሚመዝን ፈተና እንዳልወጣ አመልክተዋል።

የባለፉት ፈተናዎችን እንዳዩና የዚህ አይነት ፈተና ግን እንዳልነበር ጠቁመው ፈተናው ማስተካከያ እንዲደረግበት አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ትላንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የዘንድሮው ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ብሎ ነበር።

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም፤ አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ሲል ነበር ያስረዳው።

ሚኒስቴሩ ይህን ቢልም  ፤ በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ፦
- የማኔጅመንት
- የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሜድስን
- የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ተማሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity